Get Mystery Box with random crypto!

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~ ክፍል 4 'እኔም በጣም አፈቅርሻለሁ! ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባ | ከመፃሕፍት ጥግ

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~

ክፍል 4

"እኔም በጣም አፈቅርሻለሁ! ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባል ሰው አይደለሁም ግን አብረን ላሳለፍናቸው እናዛ ምርጥ የፍቅር አመታት እና ለወደፊት አብረን ስንኖር ምርጡ እና ጥሩ የሚባል ባልሽ ለመሆን ግን እየሞከርኩኝ ነው" ብዬ እንባ ባራሰው ፊቴ ደስተኛ ለመምሰል ፈገግ አልኩኝ።
በዚሁ ወሬ ከቀጠልን የቀኑ የእንባ ስሜቶች መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ወሬ ለመቀየርም በማሰብ ስለ ስራ ማውራት ጀመርኩኝ። እሷም ለአዲስ ስራ በጣም ታዋቂ ከሆነ ድርጅት እሷ ብቻ ተለይታ እንደጠሯት እና እዚህ ካለው ስራዋ አንፃር የተሻለ ድርጅት እንደሆነ ነገረቺኝ። ነገር ግን አሁን ያለችበትን ድርጅት ስራው አላለቀም ግን በእሷ በኩል የሚጠበቀውን ስራዋን የግድ ቶሎ መጨረስ እንዳለባት እና አለቃዋ ደግሞ በጣም ተጨቃጫቂ ሀይለኛ መሆኑ ስራውን ለመልቀቅ ነገሮችን እንዳሰበችው እንደማይሄድ ነገረቺኝ። ነገም አለቃዋን ማሳመን ካልቻለች ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ደግሞ የአዲሱ ድርጅት ስልጠና እንደሚጀምር እዛም ጠዋት በሰዓቱ ካልደረሰች እንደሚያመልጣት ነገረቺኝ። እኔም አዲሱን ድርጅት በጣም የምትፈልጊው ከሆነ በጣም መጣር እንዳለባት ነግሬያት እኔም አሁን ያለችበት ድርጅት በቅርብ ብትገባም አዲሱ ድርጅት ደግሞ የተሻለ ከሆነ በዚህ ሀሳቧ እንደምስማማ ነገርኳት። ማድረግ የቻልነውን ሁሉ እንደምናደርግ እና እግዚአብሔርም እንደሚረዳን ነግሬያት ነገስ ወደ ሆለታ ለመሄድ ስንት ሰዓት ነው ምትነሺው አልኳት እሷም 12 ሰዓት ቀደም ብላ እንደምትነሳ እና ሻርፕ 1 ሰዓት ሜክሲኮ ጋር መገኘት እንዳለባት እና የድርጅታቸው መኪና ወደ ሆለታ ለመሄድ በሰዓቱ መድረስ እንዳለባት ነገረቺን። እኔ ምንም እንዳትይኝ ጠዋት በለሊት መጥቼ ከቤቷ ሜክሲኮ እንደማደርሳት ነገርኳት። እኔን እንደዛ ማስቸገር እንደማትፈልግ ባውቅም ከናፍቆታችን አንፃር 1 ደቂቃ ለኛ ጋር ዋጋ አላትና እንቢ እንዳትል ተጭኛት ሂሳባችንን ከፍለን ወደ ቤቷ አደረስኳት። ሰፈሯም እንደደረስን ለመሰናበትም ተቃቅፈን ከተሳሳምን በኃላ የግቢዋ በር እስኪከፈትላት ሁሌም እንደማደርገው ቆሜ በዓይኔ እጠብቃታለሁ። እሷም በሩ እንደተከፈተላት እንድሄድ በእጇ ምልክት እየሰጠቺኝ በአይኗ ሸኘችኝ። እኔም ወደ ቤቴ ስመለስ መኪናዬ ውስጥ የተከፈተውን የዳዊት ፅጌን ሙዚቃን ድምፁን ከፍ አደረኩት መንገዱ ከወትሮ በተለየ በጣም እረዝሞብኛል።
አይኔ እንባ እንዳቀረረ ነው እስክገባ በጣም ቸኩያለሁ። ከአሰልቺ ጉዞ በኃላ ሰፈር እንደደረስኩኝ መኬናዬን ፓርክ አድርጌ ቤቴ ገባሁ እና ስልኬን አውጠቼ ፍቅር ጋር ደወልኩላት በሰላም መግባቴን እና ጠዋት በጠዋት እንደምመጣ ደግሞም በጣም እንደማፈቅራት ነግሬያት ተሰነባብተን ስልኩን ዘጋነው። ልብሴን ቀያየርኩኝ እና አልጋዬ ከላይ ላይ ጋደም አልኩኝ። ጭር ባለው ዝምታ ላይ ስለ ፍቅር በተደጋጋሚ ውስጤ እያሰበ ነው ሳላስበው እንባዬ በጉንጮቼ ላይ ወደ ጆሮዬ መፍሰስ ጀመሩ... ድምፅ የሌለው የማያቆም የወንድ ልጅ እንባ....አየር የሚያሳጥር ህመም ያለው እንባ.... ከሰዎች ሁሉ አስበልጬ የማከብራት፣ ከብዙ የህይወት አሰልቺ ጊዜያት በኃላ በንፁህ ፍቅር የማፈቅራት፣ ፈጣሪ ነው እሷን የሰጠኝ ብዬ ያመንኩባትን ፍቅረኛዬ ከኔ ልትለይ መሆኑን ውስጤ ሲያስብ ይበልጥ እንባዬ ይፈስ ጀመረ። ከእሷ ጋር ሆኜ ቀንሙሉ ያፈንኩትን ስሜቶቼን ሁሉ በእንባ መልክ መውጣት ጀመሩ እንባዬን ማቆም አቃተኝ...አብረን ያሳለፍናቸው የሚገርሙ እና የተለየ አክብሮት ያለባቸው የፍቅር ጊዜያት ሳስብ ይበልጥ መቆጣጠር አቃተኝ..... ልብ የሚወጋ የወንድ ልጅ የሲቃ እንባ.... አሁን ይሄን ስሜት ከፈጠረኝ ፈጣሪ እና ከትራሴ በቀር ማን አየ...? ማንስ ተረዳው...? ከልቡ ያፈቀረ ያውቀዋል። ከብዙ ህመም ካላቸው እንባዎች ጋር ብዙ ሰዓታት አለፉ። እንደምንም ለራሴ እንዲህ አልኩት "መጠንከር አለብኝ" እሷን ከሰጠኝ ከ እግዚአብሔር ጋር ነገሮችን መቀየር እንደምችል ለራሴ ነገርኩት። አዎ ከዚህ በኃላ እሷን ከኔ ተለይታ ማሰብ በፍፁም አልፈልግም! ስለዚህ "ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ" ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ። ከነገ ጀምሮ ማድረግ ያሉብኝን ሁሉ ማሰብ ጀመርኩኝ 1ኛ) አልኩኝ......

#ይቀጥላል

ነቢያት ሙሉጌታ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....