Get Mystery Box with random crypto!

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~ ክፍል 2 ...ምንም ሳናወራ በዝምታዎች እጇን እጄ ላይ እንደተቆላ | ከመፃሕፍት ጥግ

~የሆለታው የምሽት ጉዞ~

ክፍል 2

...ምንም ሳናወራ በዝምታዎች እጇን እጄ ላይ እንደተቆላለፍን መኪናውን አስነስቼ እየነዳሁ ከሰፈሯ ወጣን።
እረዘም ላለ ደቂቃዎች በዝምታዎች ውስጥ ነን በሁለታችንም አይኖች ውስጥ የእውነተኛ ፍቅር በግፅ ይነበባል። በመሀል ዝምታውን የሰበረ ቃል ከልቤ ወጣ "አፈቅርሻለሁ" አልኳት እሷም የተናገርኩትን ሳልጨርስ "እኔ በጣም አፈቅርሀለሁ" አለቺን እጃችን በመሀል ማርሽ ለመቀየር ብቻ እየተላቀቅን እና መልሰን እያቆላለፍን ጉዛችንን ወደ መሀል መንገድ ስንደርስ "ወዴት እንሂድ?" አልኳት እሷም "አንተ ደስ ወዳለህ ቦታ ውሰደኝ" አለቺኝ እኔም ብቻችንን እንድንሆን ፈልጌ ነፋሻማ አየር ወዳለበት ወደ አዲሱ ገበያ የሚገኘው መለስ ፋውንዴሽን አደረኩኝ። የሚገርመው ከናፍቆቴ የተነሳ አለባበሷን እንኳን ልብ ብዬ አላስተዋልኩትም ነበር በተተኮሰው ፀጉሯ ላይ ቢጫ ቲሸርት ከ ግሬይ ቱታ ሱሪ ጋር ነው ያደረገችው። እንደዚህ ለብሳ የማያት ሳታስበው ሰፈሯ መጥቼ ድንገት ውጪ ስላት ብቻ ነበር። ሰፈሯ አካባቢ እሷም መጀመሪያ አካባቢ የማታውቀው እኔም ባጋጣሚ እስኪ ልየው ብዬ ያየሁት እኔና እሷ ብቻ የምንሆንበት አዲስ አበባን በደንብ ማየት የሚቻልበት ቦታ አለ አብዛኛውን ጊዜ ስትናፍቀኝ እና ለስራ ከመጣሁ ብዙም ከሰፈሯ ቦታው ስለማይርቅ እንደዛ ለብሳ የምትወጣው እንጂ ሁሌም በአለባበሷ የምትገርም እና ሁሌም ቀሚስ ብቻ የምታደርገው። እንደዚህ ለብሳ ከሰፈር እርቀን ስንሄድ ስለማላያት በሱ እየቀለድኩባት ጉዞአችንን ቀጠልን። ፀሀዩ ከረር ያለ ነበርና ፀሀይ እንዳይሆንባት በማሰብ ወደኃላ ወንበር ቦታ እንድትቀይር አድርጌያት እግሮቿን የኋላው ወንበር ላይ ዘርግታ ረጭ ባለው በዊንጌት መንገድ ላይ የንዋይ ደበበን "አሜን" ሚለውን ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርጌ በውስጠኛው እስፖኪዮ ደጋግሜ በየቀቂቃው እያየኋት ከሙዚቃው አብሬው እዘፈንኩ ከቦታው ደረስን። የመለስ ፋውንዴሽን ውስጡ ዝግ ስለነበር እዛው አካባቢ ጥላ ስር አቁመን ውስጥ ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን። እዛው ከኃላ ወንበር እንደተቀመጠች አይናችንን ከአይናችን ሳናላቅ ወሬያችንን ጀመርን። ለምን ሳልነገራት ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደሄድኩኝ እና የገጠመን ችግር ስለጨነቀኝ የፈጠረኝ አምላክ መፍትሄ ይሰጠናል ብሎ ልቤ ስላመነ ድንገት ተነስቼ እንደሄድኩኝ እና በዛም ደግሞ ሳልነግራት ስልኬን ዘግቼ ስላስጨነኳት በድጋሚ ይቅርታ ጠይቄ በሷ በኩል ምን እንደተፈጠረ፣ በጣም የባህሪ መለወጥ ስላየሁብሽ እና አንቺም የእኔን ማዘን እና ስብራት ላለማየት ብለሽ ልትነግሪኝ ባለመቻልሽ ሁኔታው በጣም ሲጨንቀኝ እህትሽን እንዳናገርኳት እና እሷም ሁሉንም ነገር እንደነገረቺኝ ነግሬያት በእህቷ በኩል የተነገረኝ ነገር እውነት እንደሆነ እና ስለተፈጠረው ነገር በደንብ እንድታብራራልኝ ጠየኳት። እሷም ከብዙ ዝምታ እና እንባ ካዘለው ዓይኖቿ በኃላ በመስታወቱ ወደ ውጪ እያየች "አዎ እውነት ነው" አለቺኝ። ነገር ግን ከሱ ቃላት ውጪ ከእንባ በስተቀር ምንም ልትነግረኝ አልቻለችም። እኔ ወደ ውጭ የመሄድ ሀሳብ ያላት የማስተርስ ትምህርቷን በጣም መማር ስለምትፈልግ ለትምህርት እንደምትሄድ ብቻ ነበር የማውቀው እህቷም ያኔ ወደ ውጪ ልትሄድ እንደሆነ እንጂ በምን ምክንያት እንደሆነ የነገረቺኝ ነገር አልነበረም። እሷ ግን ከእንባ በስተቀር አሁንም በዝምታ ውስጥ ናት። አዎ መሀከላችን ጋፕ ቢፈጠርም የእሷ ማደግና መማር ለወደ ፊት ህይወታችን የሚጠቅመን እና ለተሻለ የተሻለ አስተሳሰብ፣ የተሻለ ኑሮ እንዲኖረን የሚጠቅመን ነገር ነውና እንደዚህ እንዲሰማት እንደማልፈልግ ደግሞ መልሰን እንደምንገናኝ ብቻ ሳይሆን አንቺ ፍቃደኛ ከሆንሽ ሁሌም እንደምልሽ በነገው እለት የህግ አካል ጋር ቀርበን አንቺን ለመጋባት እኔ ፍቃደኛ እንደሆንኩ በስረግጬ ነገርኳት። አንቺም እዛ ትምህርትሽን እስክትጨርሺ ድረስ እኔ እዚ ነገሪችን በተሻለ መልኩ አመቻችቼ እንደምጠብቃት ነገርኳት። ነገር ግን እንባዋ ይበልጥ ይፈስ ጀመር.....

#ይቀጥላል

ነቢያት ሙሉጌታ

=========//////=========

ግሩፕፓችንን እና ቻናላችንን join አድርጉ

@kemtshafet_teg_group
2,900 በላይ አባል ያለው

@kemtshafet_teg
250 በላይ ሰብስክራይብ ያለው

======== **** ========

የፈለጉትን መፅሐፍት በቤቶ ሆነው ይዘዙን!
"ኤግላ የመፅሐፍት ዲሊቨሪ"
@Egla_Book_Delivery

ኤግላ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ጠቅላላ የፊኒሺንግ ስራ ተቋራጭ በቅርብ ቀን.....