Get Mystery Box with random crypto!

በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet)

የቴሌግራም ቻናል አርማ kegedilatandebet2716 — በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet)
የቴሌግራም ቻናል አርማ kegedilatandebet2716 — በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet)
የሰርጥ አድራሻ: @kegedilatandebet2716
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.19K
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ገድላት ውስጥ የተጻፉ የቅዱሳን አባቶቻችንና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድላቸውና አስገራሚ ታሪካቸው ዓመቱን ሙሉ ምንም ሳይቋረጥ በየቀኑ ይነገርበታል!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 05:23:31 Watch "ነሐሴ 21-ገድለ አቡነ አብራንዮስ ዘደብረ ጥሉል፣ ተአምር እና የዕለቱ ስንክሳር" on YouTube


767 viewsmiki2721, 02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:05:35
1.0K viewsmiki2721, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:05:32
937 viewsmiki2721, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:05:28 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 21-የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ላለማየት ሳይወለዱ በእናታቸው ማኅፀን 7 ዓመት ከ6 ወር የቆዩት አቡነ አብራኒዮስ ዘደብረ ጥሉል ዕረፍታቸው ነው። አስደናቂው ገዳማቸው ኤርትራ ውስጥ ልዩ ስሙ ድባርዋ በሚባለው ቦታ ይገኛል።
+ የንጉሥ ሉክያኖስ ልጅ የሆነችው ሰማዕቷ ቅድስት ኄራኒ ምስክር ሆና ዐረፈች፡፡ የስሟ ትርጓሜ ‹‹ሰላም ፍቅር›› ማለት ነው፡፡ ንጉሡ አባቷ ያማረ አዳራሽ በ8 መስኮቶች አስጊጦ አሠርቶላት የወርቅና የብር ሣህኖችንና ጽዋዎችንም አዘጋጀላት፡፡ ሦስት አገልጋዮችንና አንድ መምህር ሾመላት፡፡ ዕድሜዋም 7 ዓመት በሆናት ጊዜ ራእይ አየች፡፡ ያየችውም ራእይ ይህ ነው፡- በአፏ የወይራ ቅጠል የያዘች ርግብ መጥታ በማዕዷ ላይ ስታስቀምጠው አየች፡፡ ዳግመኛም ንስር መጥቶ የያዘውን አክሊል በማዕዱ ላይ ሲያስቀምጠው አየች፡፡ ዳግመኛም ቁራ መጥቶ ከእርሱ ጋር ያለውን ከይሲ በማዕዷ ላይ አስቀመጠው፡፡ እርሷም ይህን ስታይ በመደንገጥ ለመምህሯ ነገረችው፡፡ እርሱም ራእዩአን እንዲህ ብሎ ተረጎመላት፡- ‹‹ርግብ የሕግ ምልክት ናት፡፡ የዘይቱም ቅጠል የክርስትና ጥምቀት ናት፡፡ ንስርም ድል አድራጊነት ነው፡፡ አክሊልም ለሰማዕታት የሚሰጥ ክብራቸው ነው፡፡ ቁራው የንጉሥ ምሳሌ ነው፣ ከይሲውም መከራ ነው፣ አንቺም የክብር ባለቤት በሆነ ክርስቶስ ስለ ስሙ ትጋደይ ዘንድ አለሽ›› አላት፡፡

ከዚህም በኋላ ንጉሡ አባቷ ሉክያኖስ ሊጎበኛት መጥቶ ‹‹ልጄ ሆይ ከመንግሥት ታላላቆች ለአንዱ ላጋባሽ እሻለሁ›› አላት፡፡ እርሷ ግን ‹‹አባቴ ሆይ ከልቡናዬ እስክመክር ሦስት ቀኖችን ታገሰኝ›› ብላ መለሰችለት፡፡ አባቷም በሄደ ጊዜ በጣዖታቱ መሠዊያ ፊት ቆማ ስለጋብቻ የሚሆነውን ይገልጡላት ዘንድ ብትለምናቸውም እነርሱ ግን ምንም ሊመልሱላት አልቻሉም፡፡ በመቀጠልም ዐይኖቿን ወደ ሰማይ አቅንታ ‹‹የክርስቲያን አምላክ ሆይ ወደምትፈቅደው ምራኝ›› ብላ ጸለየች፡፡ ወዲያውም የታዘዘ መልአክ መጥቶ ‹‹እነሆ ነገ ከጳውሎስ ደቀ መዛሙርት አብዱ ወደዚህች አገር ይመጣልና እርሱ የክርስትና ጥምቀትን ያጠምቅሻል›› አላት፡፡ መልአኩ እንደነገራትም በማግሥቱ ያ ሐዋርያ መጥቶ አጠመቃት፡፡
በሦስተኛው ቀን በቀጠሯቸው መሠረት አባቷና እናቷ መጡ፡፡ ቅድስት ኄራኒም ‹‹እኔ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ›› አለቻቸው፡፡ ይህንንም ሲሰማ ንጉሡ አባቷ እጅግ ተቆጣ፡፡ ወደ ከተማው መሀል አደባባይ ላይ አውጥተው እንዲጥሏትና በፈረሶች እግር እንዲረግጧት አዘዘ፡፡ ወታደሮቹም አባቷ እንዳዘዛቸው ቢያደርጉባትም በእግዚአብሔር ጥበቃ ምንም ጉዳት ሳያገኛት ቀረ፡፡ ይህንንም ያዩ ወላጆቿ በክብር ባለቤት በጌታችን አመኑ፣ መንግሥታቸውንም ትተው በቅድስት ኄራኒ አዳራሽ ገብተው ተቀመጡ፡፡ በአቅራቢያቸው ያለ ሌላ ንጉሥ ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ እነርሱ መጥቶ ወደ መንግሥታቸው እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ እነርሱም አልፈለጉም ነገር ግን እርሱ መንግሥታቸውን ያዘባቸው፡፡ ቅድስት ኄራኒንም ይዞ አሠቃያት፡፡ ለተራቡ አንበሶችና ለመርዛማ እባቦች ሰጣት ነገር ግን ምንም አልነኳትም፡፡ ሁለተኛም በመጋዝ ሰውነቷን ቆራርጦ በአንገቷ ላይ ትልቅ ድንጋይ አሥሮ ወደ ባሕር ጣላት፡፡ ጌታችንም ከዚህ ሁሉ መከራ ጠብቋት ምንም ሳትሆን በጤና አስነሣት፡፡ እርሷን ያጠመቃት ሐዋርያውም አባቷንና ሌሎች ቁጥራቸው 300 የሆኑ ሰዎችን አጠመቃቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ከሃዲው ንጉሥ ኑማርያኖስ የቅድስት ኄራኒን ዜናዋን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አስቀርቦ ቀላኒካ ወደሚባል አገር ወሰዳት፡፡ በዚያም ጽኑ ሥቃይን አሠቃያት፡፡ በበሬ አምሳል በተሠራ የነሐስ በርሜል ውስጥ ዘጋባት ነገር ግን ጌታችን ያንን በሬ ሰብሮ ሰማዕቷን ያለ ጥፋት በጤና አወጣት፡፡ ከዚያም ከሃዲው ኑማርያኖስ ሞቶ በእርሱ ፈንታ ሌላኛው ከሃዲ ሳፎር ነገሠ፡፡ እርሱም የቅድስት ኄራኒ ዜናዋን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ አቅርቦ ከእምነቷ ሊያስወጣት ቢሞክር እርሷ ግን በእምነቷ ጸናች፡፡ ብዙ ካሠቃያትም በኋላ በመጨረሻ በታላቅ ጦር ወጋትና ዐረፈች፡፡ ነገር ግን አሁንም ጌታችን ከሞት አነሣትና ፍጹም ጤነኛ ሆነች፡፡ ንጉሥ ሳፎርም ይህንን ባየ ጊዜ እጅግ ተደንቆ ሰገደላት፡፡ ‹‹በአንቺ አምላክ አምኛለሁ›› በማለትም በጌታችን አመነ፡፡ ሌሎች 31 ሺህ የሀገሩ ሰዎችም አምነው ተጠመቁ፡፡

ከዚህም በኋላ በዚያች ባሰሩላት አዳራሽ ውስጥ እናትና አባቷ ዐረፉ፡፡ እርሷ ግን በአምላካዊ ኃይል በነፋስ እየተጫነች እስከ ኤፌሶን አገር ድረስ እየተጓዘች ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረገች የጌታችንን ክብር በመመስከር ብዙዎችን ወደ እውነተኛዋ ሃይማኖት መለሰቻቸው፡፡ በፋርስ ነገሥታት በመቄዶንያ በቀላኒካና በቁስጥንጥንያ ነገሥታት ፊት የጌታችንን ክብር ከመሰከረች በኋላ በዚህች ዕለት የሰማዕትነት ፍጻሜዋ ሆነና ወደ ወደደችው ክርስቶስ ሄደች፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀዳጀች፡፡ የዚኽች ታላቅ ሰማዕት የቅድስት ኄራኒ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
892 viewsmiki2721, 07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:45:50 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 20-በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ 372 ዓመታት በሞት ካንቀላፉ በኋላ ከሞት ተነሥተው ትንሣኤ ሙታንን የሰበኩት ሰባቱ ቅዱሳን ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ ሰላማ መተርጉም ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ዘረኝነትን ከአገራችን ለማጥፋት ብዙ የደከሙት እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወሩት አቡነ ክፍለ ማርያም ዘዲባጋ ልደታቸው ነው፡፡
+ አባ ሰላማ መተርጉም ዕረፍታቸው ነው፡፡ ትውልዳቸው ላዕላይ ግብፅ ነው፡፡ ግብረ ሕመማትንና መጽሐፈ ሐዊን ከዐረብኛ ቋንቋ ወደ ግእዝ ቋንቋ የተረጎሙ ሲሆን ሌሎችንም በጣም በርካታ መጻሕፍትን የተረጎሙ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ ስንክሳሩም ነሐሴ 20 ቀን በሰላም ማረፋቸውን ብቻ ይጠቅሰዋል እንጂ ዝርዝር ታሪካቸውን አይገልጸውም፡፡ የአባ ሰላማ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + + + +
ሰባቱ ቅዱሳን፡- እነዚህም ሰባቱ ደቂቅ ከኤፌሶን አገር የተገኙ ሲሆን የንጉሥ ዳኬዎስ የመዛግብቱ የበላይ ጠባቂዎች ነበሩ፡፡ ንጉሡ አምልኮ ጣዖትን ባወጀ ጊዜ ከከንቱ አምልኮው ጋር አልተባበሩም ነበርና ተይዘው ተወነጀሉ፡፡ ይዘውም አሰሯቸው፡፡ ንጉሡም ወደሌላ ቦታ ሲሄድ ‹‹ምናልባት እስክመለስ ሀሳባቸውን ይቀይራሉ›› ብሎ በማሰብ ከእስራት ፈቷቸው ሄደ፡፡ እነርሱ ግን የንጉሥ አገልጋይ መሆናቸውን ትተው ወደ አንድ ተራራ ላይ ወጥተው በዚያ በዋሻ ውስጥ ተቀመጡ፡፡ ንጉሡም ከሄደበት መመለሱን ሲሰሙ የዋሻውን በር ዘግተው ተቀመጡ፡፡ ከጭፍሮቹ ወገን የሆነ አንድ ወዳጃቸው ስለነበር ከገበያ ስንቅ ሊገዙ በየተራ ሲወጡ ያያቸው ነበርና አሁን ግን ቢጠፉበት እርሱ ወደ ዋሻቸው ሄደ፡፡ በሩ ተዘግቶ ቢያገኘው በረሃብ የሞቱ መስሎት ታላቅ ሰሌዳ አምጥቶ ገድላቸውን ጽፎ በቀዳዳው ወደ ዋሻው ውስጥ አስገባው፡፡ እነዚህም ሰባት ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት (372) ዘመናት አንቀላፉ፡፡
ዳኬዎስም ሞቶ እስከ ቴዎዶስዮስ ድረስ ብዙ ነገሥታት ነገሡ፡፡ በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ‹‹ትንሣኤ ሙታን የለም›› የሚሉ መና*ፍቃን ተነሥተው ብዙዎች ተከተሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ትንሣኤ ሙታን መኖሩን ግልጽ ያደርግ ዘንድ ቸሩ አምላካችን እነዚህን ሰባት ቅዱሳን በሞት ካረፉ ከ372 ዓመት በኋላ ከሞት አስነሣቸው፡፡ ከእነርሱም አንዱ ምግባቸውን ይገዛ የንጉሥ ዳኬዎስንም ዜማ ይሰማ ዘንድ የንጉሡን አርማ ያለበት የብር ሳንቲም ይዞ ወደ ገበያ ወጣ፡፡ በከተማዋም በር ላይ የመስቀሎችን ምልክት አየ፡፡ በቅጥሮቿም ውስጥ የጌታችን ስሙ ሲጠራ ሰማ፡፡ ‹‹ይህቺ ሀገር እውን ኤፌሶን ናትን?›› በማለት ሲጠይቅ ‹‹አዎ ኤፌሶን ናት›› አሉት፡፡ የያዘውንና የዳኬዎስ ስም የተቀረጸበትን ሳንቲም ለባለ ሱቅ ሲሰጠው ሰዎች ተሰብስበው ‹‹በአንተ ዘንድ የተሸሸገ መዝገብ አለ›› ብለው መረመሩት፡፡ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ አባ ቴዎድሮስና ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ወሰዱት፡፡ ንጉሡና ኤጲስ ቆጶሱም ‹‹ከወዴት ነህ?›› አሉት፡፡ እርሱም የንጉሡን የዳኬዎስን ባለሟልነት ትተው በዋሻ ተኝተው የኖሩ መሆናቸውንና ሲነቁም የሚመገቡት ፍለጋ እንደመጣ ነገራቸው፡፡
ንጉሡና ኤጲስ ቆጶሱም ሕዝቡ ተከትሏቸው አብረውት ወደ ዋሻው ሄዱ፡፡ ዋሻ እንደደረሱ ሌሎቹንም ስድስቱን ቅዱሳንን ተቀምጠው አገኟቸው፡፡ ታሪካቸው የታጻፈበትንም ትልቅ ሰሌዳ አገኙት፡፡ ዘመኑም 372 ዓመት እንደሆነው ዐወቁ፡፡ ንጉሡና ኤጲስ ቆጶሱም ከሕዝቡ ጋር እጅግ አድንቀው እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ‹‹ትንሣኤ ሙታን የለም›› የሚሉትም ይህንን ድንቅ ተአምር አይተው በእርግጥም ትንሣኤ ሙታን መኖሩን በግልጽ አይተው አመኑ፡፡ እነዚህንም ሰባት ቅዱሳንን በጠየቋቸው ጊዜ ከእነርሱ የሆነውን ሁሉ ነገሯቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ተኙ፣ ነፍሳቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ፡፡ ንጉሡም የወርቅ ሣጥን አሠርቶላቸው ሥጋቸውን በዚያ አኖረው፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ እነዚህም የከበሩ ቅዱሳን ስማቸው መክሲማኖስ፣ ታሙኪሮስ፣ መርዳዲሞስ፣ ዮሐንስ፣ ቆስጠንጢኖስ፣ ዲዮናስዮ እና አዝሚና ይባላል፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
+ + +
አቡነ ክፍለ ማርያም ዘዲጋባ፡- እኚኽም ቅዱስ ትውልዳቸው እንደርታ ሲሆን በ14 ዓመታቸው መንኩሰው መንነው በቅተው ሲኖሩ በአንድ ወቅት ወደ አክሱም ሄዱና ወላጆቻቸው ካሉበት ደረሱ፡፡ ከቅዳሴ በኋላ መበለት ቆርሰው ሲያድሉ ወላጅ እናታቸው ከስተውና ጠቁረው ስላዩአቸው ለእናታቸው አዳልተው በብዙ ሰጧቸው፡፡ እናትየው ግን ጻድቁ የሠሩትን አያውቁም ነበር፡፡ ጻድቁ ከብቃታቸው የተነሳ መና ከሰማይ እየወረደላቸው ከዓለትም ላይ ውኃ እያፈለቁ ይጠጡ ነበር፡፡ አድሎ ስላደረጉ ግን በዚህ ድርጊታቸው እግዚአብሔር ተቆጥቷቸው የሰጣቸውን ይህን ጸጋቸውን ነሳቸው፡፡ አቡነ ክፍለ ማርያምም ይህን ባወቁ ጊዜ ‹‹ወዮልኝ ወዮታ አለብኝ›› ብለው ከሰው ሳይገናኙ ዋሻ ገብተው ድፍን 11 ዓመት በለቅሶና በዋይታ እግዚአብሔርን ለመኑት፡፡ በኋላም እግዚአብሔር ይቅር እንዳላቸው ነገራቸውና የቀደመ ጸጋቸውና ክብራቸው መለሰላቸው፡፡ ስለ ዘረኝነት አስከፊነትም በብዛት አስተማሩ፡፡ ከዛ በኋላ ውኃ ከደረቅ ጭንጫ ላይ እያፈለቁ አሕዛብን ሁሉ እያስተማሩ ያጠምቁ ጀመር፡፡ ኅብስትም ከሰማይ እየወረደላቸው ሕዝቡን ያቆርቡ ጀመር፡፡ ጻድቁ በመጨረሻ በየካቲት 20 ቀን እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ዐርገዋል እንጂ በምድር ሞትን አልቀመሱም፡፡ ትልቅና አስደናቂ ገዳማቸው በአክሱም ይገኛል፡፡ የአቡነ ክፍለ ማርያም ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
871 viewsmiki2721, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:04:33
1.1K viewsmiki2721, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:04:28 ኦርቶዶክሳውያኑ ወንድማማቾች ድጋሚ እርስ በእርሳቸው እንዲጫረሱ ሁኔታዎችን አመቻችተው ጥሩምባውን ነፍተው የሞት ድግሱን ደግሰውላቸዋል።
የቅዱሳኑን አባቶቻችን አምላክ በቃችሁ ይበለን እንጂ ምድራዊ መፍትሔም ያለው አይመስልም።

የእኔ ምኞት፦ የአኵሱም ጽዮን ልጆች ከግሸን ማርያም ልጆች ጋር ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታቸው ብለው መስማማት ቢጀምሩ፤ የደብረ ዳሞው ጻድቅ የአቡነ አረጋዊ ልጆች እና የቅዱስ ላሊበላ ልጆች የሚለያያቸውን ምድራዊ ርካሽ ፖለቲካ ወደጎን ብለው አንድ ስለሚያደርጋቸው ሰማያዊ መንግሥት ብለው ሰላምና እርቅ አውርደው እርስ በእርሳቸው የሚያባሏቸውን ደማቸውን በከንቱ የሚያፋስሱትንና በሞታቸው የሚነግዱባቸውን ወያኔንና ብአዴን/ብልግናን ከላያቸው ላይ አራግፈው ጥለው ሁለቱ ቁጭ ብለው ቢመክሩ ያንጊዜ 3 ሰዓታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሞት ነጋዴው ጩጬው ፓስተር ወደ ዐረብ ሀገር ይፈረጥጥ ነበር፤ ኦህዴድም ከኦነግ ወደ ኤርትራ በረሐ ይገባ ነበር። ይህ ቢሆን የኢትዮጵያም ትንሣኤ ያንጊዜ ይመጣ ይመስለኛል። ነገር ግን በሰው ሰውኛ ካሰብነው ከንቱ ምኞት ነው። አምላከ ቅዱሳን የአኵሱሞችንና የጎንደሮችን ምሕላና ጸሎት ተቀብሎ ይታረቀን እንጂ ምድራዊ መፍትሔ የለውም። ሁለቱም ኦርቶዶክሳውያን ዛሬ በ"በለው" መፈክር ደንዝዘው ኦርቶዶክሳውያኑ እርስ በእርሳቸው ሲጫረሱ ሰሜን ላይ የሚነደውን እሳት ኦነጋውያን ከዳር ተቀምጠው ይሞቁታል። ከትናንቱ ስሕተታቸው መማር ያልፈለጉን እነዚህን ነው ለካ ሰውየው "ጅል፣ ጅላጅል እና ጅላንፎ" እያለ አስቀድሞ ልክ ልካቸውን የነገራቸው።
1.0K viewsmiki2721, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:04:12
788 viewsmiki2721, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:04:08 አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ነሐሴ 19-ከሰማንያ ዓመታት በላይ በበርሃ ጽኑ ተጋድሎን የተጋደሉትና በግብጽ በገደሙት ገዳማቸው በአስቄጥስ ከ50,000 በላይ መነኮሳትን የመሩት የአባ መቃርስ የሥጋቸው ፍልሰት የተከናወነበት ዕለት ነው፡፡ ይኸውም የመነኮሳት ሁሉ አለቃ የሆኑት የአባ መቃርስ የሥጋቸው ፍልሰት በዚኽች ዕለት የተከናወነው ሳስዊር ከሚባል አገር ወደ አስቄጥስ ገዳም ነው፡፡ ከከበረች ዕረፍቱ በኋላ ከሀገሩ ከሳስዊር ሰዎች መጥተው ሥጋውን በድብቅ ወስደውት ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ከዚያ አኖሩት፡፡ ነገር ግን እስላሞች ነግሠው በክርስቲያኖች ላይ ስደት ስላመጡ የአባ መቃርስን ሥጋ ወስደው በድጋሚ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት የቅዱሱን ሥጋ ከዚያ አኖሩት፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ስለ አባ መቃርስ ሥጋ እያለቀሰ እግዚአብሔርን ለመነ፡፡ የአስቄጥስ ገዳም አረጋዊያን መነኮሳትንም አስከትሎ የአባ መቃርስ ዐፅም ወዳለበት ሄዱ፡፡ ነገር ግን የአገሩ ሰዎች መኮንናቸውን አስቀድመው ሰይፋቸውን መዘው በመጠበቅ የአባ መቃርስ ዐፅም ከለከሏቸው፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱና መነኮሳቱም አዝነው ፈጽመው እያዘኑ አደሩ፡፡ ነገር ግን አባ መቃርስ በዚያች ሌሊት ለመኮንኑ በራእይ ተገለጠለትና ‹‹ከልጆቼ ጋር መሄድን ለምን ትከለክለኛለህ? እንግዲህስ ከልጆቼ ጋር ወደ ቦታዬ ልሄድ›› አለው፡፡ መኮንኑም በጠዋት ተነሥቶ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ አረጋውያን መነኮሳቱን ጠርቶ የከበረ የአባ መቃርስን ሥጋ ሰጣቸው፡፡

እነርሱም እጅግ ደስ ብሏቸው የአባ መቃርስን ሥጋ ይዘው በመርከብ በመሳፈር ተርኑጥ የምትባል አገር አድረው በማግሥቱ ወደ ገዳማቸው አስቄጥስ ለመድረስ በረሃውን ሲያቋርጡ ጥቂት ሊያርፉ ወደዱ፡፡ ነገር ግን አባ ሚካኤል ‹‹የቅዱስ አባታችንን ሥጋ የምናሳርፍበትን ቦታ እግዚአብሔር ካልገለጠልን በቀር አናርፍም›› አላቸው፡፡ ወዲያውም የአባ መቃርስን ሥጋ የተሸከመው ግመል ወደ አንድ ቦታ ደርሶ በዚያ በርከክ ብሎ የአባ መቃርስ ሥጋ ያለበትን ሣጥን ራሱ ይጥል ዘንድ ወዲያና ወዲህ ሲዟዟር አዩት፡፡ መነኮሳቱም እግዚአብሔር የፈቀደው ቦታ መሆኑን ዐውቀው ደስ ተሰኙ፡፡ ያም ቦታ እስከዛሬም ድረስ እንደታወቀ አለ፡፡ ከዚህም በኋላ መነኮሳቱ የአባ መቃርስ ሥጋ ይዘው ወደ አስቄጥስ ገዳም በደረሱ ጊዜ የገዳሙ መነኮሳት ሁሉም ወጥተው ወንጌልና መስቀሎችን ይዘው እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡት፡፡ ከአባ መቃርስም ሥጋ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡

በገዳም ለሚፈጸም ተጋድሎ ፋና የሆኑ በአስቄጥስ ገዳም ለሚኖሩ መነኮሳት ሁሉ አባት የሆኑት የከበሩ ታላቁ አባ መቃርስ፡- መቃርስ (መቃርዮስ) ማለት ‹‹ቅዱሱ ለእግዚአብሔር›› ማለት ነው፡፡ ከደቡባዊ ግብፅ ከተወደዱ ደጋግ ክርስቲኖች የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ሣራ ይባላሉ፡፡ እነርሱም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳሉት እንደ አብርሃምና ሣራ እጅግ ደጎች ነበሩ፡፡ ልጅ ግን አልነበራቸውምና በስለት መቃርስን ወለዱ፡፡ ሲያድጉም በግድ ያለፈቃዳቸው ሚስት አጋቧቸው፡፡ አባ መቃርስ ግን ወደ ሙሽራይቱ በገቡ ጊዜ ዐውቀው እንደታመሙ ሆነው ተኙ፡፡ ‹‹ከበሽታዬ ለጥቂት ጊዜ ጤና ባገኝ ወደ ገዳም ልሂድ›› ብለው ወደ አስቄጥስ በረሃ ሄዱ፡፡ መልአክም ተገልጦ ‹‹ይህች አስቄጥስ የአንተና የልጆችህ ርስት ናት›› አላቸው፡፡ ወደ ቤተሰባቸውም በተመለሱ ጊዜ ሙሽራ እጮኛቸው በድንግልና እንዳለች ሞታ ደረሱ፡፡ ከጥቂት ቀንም በኋላ እናትና አባታቸውም ዐረፉ፡፡ እርሳቸውም ንብረታቸውን ሁሉ ለድሆች መጽውተው ገዳም ገቡ፡፡ ሕዝቡም ደግነታቸውንና እውነተኛነታቸውን አይተው ትንሽ ማረፊያ ሠርተው ሌሎች እንዲያገለግሏቸው አደረጉ፡፡

ከዕለታትም በአንድ ቀን አንዲት ሴት ልጅ ከጎረምሳ አርግዛ ሳለ ጎረምሳው ‹‹አባትሽ ሲጠይቅሽ ከአባ መቃርስ አረገዝኩ በይ›› ብሎ መከራትና ለአባቷ እንደተባለችው ተናገረች፡፡ ‹‹አባ መቃርስ በግድ ደፍረውኝ አረገዝኩ›› አለች፡፡ የከተማው ሰውም አባ መቃርስን ከበዓታቸው አውጥተው ለሞት እስኪደርሱ ድረስ ደበደቧቸው፡፡ መላእክትም በሰው አምሳል ተገልጠው ዋስ ሆነው ለልጅቷም ምግቧን ሊሰጡ ተስማምተው ወደ በዓታቸው መለሷቸው፡፡ አባ መቃርስም ለራሳቸው ‹‹መቃርስ ሆይ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባለ ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃል›› እያሉ ቅርጫቶችን እየሠፉ ለሚያገለግላቸው ልጅ እየሰጡት እርሱ ሸጦ እያመጣ ብዙውን ለዚያች በዝሙት ጸንሳ በሳቸው ላሳበበች ሴት ይሰጡ ጀመር፡፡ መውለጃዋም በደረሰ ጊዜ እስከ 4 ቀን ድረስ በጽኑ ሥቃይ ቆየች፡፡ እውነቱንም ተናግራ ንስሓ በገባች ጊዜ ወደ አባ መቃርስ ዘንድ አደረሷት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ‹‹አባታችን ይቅር በሉን›› ብለው ከእግራቸው ላይ ሲወድቁ ይቅር ብለዋቸው ቀድሰው አቆረቧቸው፡፡

ከዚህ በኋላ መልአኩ ወስዶ አስቄጥስ ገዳም አደረሳቸው፡፡ የቅዱሳኑ የመክሲሞስና የዱማቴዎስ በዓት ወደ ሆነች ቦታም አስገብቶ በዚያ በልጆቻቸው ቦታ ላይ በዓታቸውን እንዲያጸኑ ነገራቸው፡፡ አባ መቃርስ ወደ አባ እንጦንስ ዘንድም በመሄድ በረከታቸውንና ምክራቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ ሰይጣናትም በእርሳቸው ላይ የሚያደርሱትን ክፉ ነገር ሲመካከሩ ይሰሟቸው ነበር፡፡ በእሳት እያቃጠሉ ፈተኗቸው፣ የዝሙት መንፈስ እያመጡም ፈተኗቸው፣ በዚህም ትዕግስትን ቢያደርጉ በሌላም ዓለማዊ ክብርን መውድን፣ ትዕቢትን፣ መመካትን፣ ታካችነትን፣ ስድብን፣ ሃይማኖት ማጣትን፣ ተስፋ መቁረጥን በልባቸው አሳደሩባቸው፡፡ በአጋንንት ምክንያት ይህም እንደሚመጣባቸው አባ እንጦንስ አስቀድመው ነግረዋቸው ነበር፡፡ ወደ አባ እንጦንም በመሄድ በአጋንንቱ የደረሰባቸውን ፈተናና ጾር ነገሯቸው፡፡ አባ እንጦንስም አመንኩሰው እንዲጸኑ በመምከር ወደ በዓታቸው ሸኟቸው፡፡ አንድ እርኩስ መንፈስ ያደረበት ባሕታዊ አግኝቶ ትንሣኤ ሙታንን አላምንም ቢላቸው ሙት አስነሥትው አሳይተው አሳምነውታል፡፡ ሙቱንም አጥምቀው አምነኩሰውት 7 ዓመት በተጋድሎ ኖሮ በሰላም ዐረፈ፡፡

አባ መቃርስ በበረሃ ውስጥ ራቁታቸውን ጌታችን ከብርዱም ሆነ ከሙቀቱ እየጠበቃቸው 40 ዘመን የኖሩ ጻድቃንን አገኟቸውና ‹‹እንደ እናንተ እንድሆን ምን ላድርግ?›› ቢሏቸው ‹‹ወደ በዓትህ ተመልሰህ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ አንተም እንደ እኛ ትሆናልህ›› አሏቸው፡፡ አባ መቃርስም የጻድቃኑን በረከታቸውን ተቀብለው ወደ በዓታቸው ተመልሰው ማልቀስ ጀመሩ፡፡ ጻዲቁ በመጨረሻ ነፍሳቸውን መላእክት ሲያሳርጓት ይፈትኗቸው የነበሩ አጋንንት ‹‹መቃርስ ሆይ አመለጥከን አሸነፍከን…›› እያሉ ሲጮኩ አባ መቃርስም ‹‹እስከ ዛሬ ገና ነኝ፣ በጌታዬ በቀኙ ልቁም በግራው አላወኩምና›› ብለው በትሕትና መለሱላቸው፡፡ የአባ መቃርስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞
766 viewsmiki2721, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:03:45
561 viewsmiki2721, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ