Get Mystery Box with random crypto!

+በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም: +ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል: +በዙፋን ላይ የኢትዮዽ | ✞ገድለ ቅዱሳን✞

+በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም:
+ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል:
+በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ ነበር:
+ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት የእንጀራውን ቅርፍት (ጠርዝ) ብቻ ነበር::

+በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል:
+በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን (ላስታን) ገንብቷል:
+ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች ናቸው::

+ሥራውን ከፈጸመ በሁዋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ: በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ አርፏል:: ጌታችን ስምህን ያከበረ: ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን: ከርስተ መንግስተ ሰማያት አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል:: ይህቺ ዕለት ቅዱሱ ንጉሥ የተወለደባት ናት::

=>እኛን ስለ ወደደ ሰው የሆነ ጌታ ፍቅሩን ይሳልብን:: ከድንግል እናቱና ከልደቱ በረከትም ያሣትፈን::

=>ታሕሳስ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ልደተ ክርስቶስ ስቡሕ
2.ታኦዶኮስ (ድንግል ማርያም)
3.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ (ልደቱ)
4.ቅዱስ ላሊበላ (ልደቱ)
5.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ልደታቸው)
6.ጻድቅ አቃርዮስ (ንጉሠ ሮሃ)
7.ቅዱስ ቆሪል ገመላዊ
8.ሰብአ ሰገል
9.ዮሴፍና ሰሎሜ
10.ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
2.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
3.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
4.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
5.ቅድስት አርሴማ ድንግል

=>"+"+" እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ:: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት: እርሱም ክርስቶስ: ጌታ የሆነ ተወልዶላቹሃልና:: "+"+" (ሉቃ. 2:10)

 
   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>