*በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ *በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ *በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ *በሥጋማርያም ጌታ ተነሳ *በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ *በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ *በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል:: (መጽሐፈ ቅዳሴ) +በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው:: > =>የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን:: ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን:: =>ታሕሳስ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አማኑኤል አምላካችን 2.በዓለ ጌና ስቡሕ 3.ዕለተ ማርያም ድንግል 4."174" ሰማዕታት (የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር) =>ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱሳን (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ) 2.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ 3.ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ 4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ 5.ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ =>+"+ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:- እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል:: የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው:: +"+ (ማቴ. 1:20) > 1.5K views04:38