Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ! የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው የበጀት የተለያዩ አይነቶች | ከፍታ ፖርታል KEFTA Portal

ኢንተርፕራይዞችን የሚያሳትፍ ጨረታ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለው የበጀት የተለያዩ አይነቶች የICT እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

•ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታው የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ

•በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት

•የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል መግቢያ ቅፅ
•የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሠርተፍኬት
•የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት
•በ2014/2015 የታደሰ የንግድ ፍቃድ

1 ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡

2 አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለክፍያ በነጻ ይሠጣቸዋል።

3. የጨረታው ሰነድ የሚላከው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት)፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 6164 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ወይም ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር (ዋናው መ/ቤት) ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡

4. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ መስከረም 04 ቀን 2015 ዓ.ም. በ4:00 ሰዓት ጠዋት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ማስገት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) አያይዘው ያቀርባሉ::

5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡
ጨረታው መስከረም 04 ቀን 2015 ዓ.ም. በ4:10 ሰዓት ጠዋት ይከፈታል ::

6.ሀ/ ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ (ዋናው መ/ቤት) ቁጥር 9
ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 9
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ +251-111-553-400

ለበለጠ መረጃ 6131 ይደውሉ ወይም https://tender.2merkato.com/tenders/630cbdc84e36341cd43079f9?lang=am ይመልከቱ።

ሌሎች በየቀኑ የሚወጡ ጨረታዎችን ለመከታተል ለኢንተርፕራይዞች በተዘጋጀው ልዩ ፓኬጅ https://kefta.2merkato.com/special-enterprise-package/ በመግባት ይመዝገቡ ወይም 6131 ይደውሉ።

ከፍታ - በ2merkato.com (http://2merkato.com/) የተሠራ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች የገበያ መረጃ በማግኘት ሥራቸውን እንዲያሳድጉ እና ቢዝነሳቸውን እንዲያሰፉ የሚረዳ የመረጃ ማዕከል ነው።

ከፍታ ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን የሚያሳትፉ ጨረታዎች፣ ድርጅቶችን እና ገዥዎችን የሚያገናኝ መድረክ፣ የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ የሚያቀርብ እና ድጋፍ እና መረጃ የሚሰጥ ማዕከል ነው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ድረ ገጻችንን www.kefta.net ን ይጎብኙ አልያም በጥሪ ማዕከላችን 6131 ላይ ይደውሉ።