Get Mystery Box with random crypto!

የፈላስፎች ጉባኤ 🇪🇹🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ kefilsfna_alem — የፈላስፎች ጉባኤ 🇪🇹🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ kefilsfna_alem — የፈላስፎች ጉባኤ 🇪🇹🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @kefilsfna_alem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.02K
የሰርጥ መግለጫ

👑ፍልስፍናን ከእኛ ጋር ይታደሙ 🎯
✔ለፍልስፍና ወዳዶች የተከፈተ ቻናል ነው!
📚በቻናሉ አበረታች የሆኑ ፅሁፎች ይቅርባሉ 👑
#ሶቅራጥስ
#ኦሾ
#ጲላጦስ
#ኒቼ
#ዲዮጋን
#ፑሎቶ
#አርስቶትል
#ዘርዐያዕቆብ
#ህሩይ_ወልደስላሴ
#የሁሉም_ፈላስፎች_ግኝቶችን_ይዘን_ቀርበናል
🔑ጥበብ ነከ ለሆኑ ቻናሎች cross እንሰራለን !
@Broken_heartN
13 Aug 2021🎉
#በወጣ_ይተካልኝ 🙏

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-19 14:33:14
1.9K viewsÑåŧňąëľ ꨄ︎ , 11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 14:27:09
<<ደስታን ምን እንደሚያካትት መፈለግህን ከቀጠልክ ፈጽሞ ደስተኛ አትሆንም።የሕይወትን ትርጉም እየፈለግህ ከሆነ ፈጽሞ ህይወትህን አትኖርም።>>

አልበርት ካሙ

[]

Albert Camus
1.7K viewsÑåŧňąëľ ꨄ︎ , edited  11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:27:59 እውነተኛው ጓደኛህ ማነው?
፨፨፨፨፨፨//////////፨፨፨፨፨፨
ከብዛት ጥራት በሚለው መርህ፣ የከበቡህ፣ ረጅም ጊዜ አብረውህ የሚያሳልፉ ሰዎች በሙሉ ጓደኞችህ አይደሉም። በጓደኝነት ግንኙነት ውስጥ ብዙ አይነት ጓደኝነት አለ። ነገር ግን የልብ ጓደኝነት ከየትኛውም አይነት ይበልጣል። እራሱን ለማዳን ወይም ያንተን ውድቀት ስለሚፈልግ ብቻ አንተን አሳልፎ የሚሰጥህ ጓደኛ እንደመኖሩ መጠን ላንተ ብሎ እራሱን የሚሰጥም የልብ ወዳጅ ጓደኛ አለ።
አዎ! ጀግናዬ..! እውነተኛው ጓደኛህ ማነው? በቀላሉ የሚረዳህ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ፣ ሃሳብህን፣ ህልምህን፣ ራዕይህን የሚደግፍልህ፣ ተግባርህን ለማወቅ የሚጥር፣ ያንተን ቦታ ብትሰጠው እንኳን ባንተው ስሜት ሃሳብህን የሚፈፅምልህ፣ የሚታመንልህ እርሱ ማነው? አሁን ከጎንህ አለን?

አዎ! ብዙ ሰው ብዙ ጓደኞች አሉት፤ ከብዛታቸው ያተረፈው ነገር ግን የለም። ጉዳይህ ጉዳዩ፣ እንድገትህ እድገቱ፣ ስኬትህ ስኬቱ፣ ደስታህ ደስታው ያልሆነ ሰው መቼም ጓደኛህንና የልቤ የምትለው ሰው ሊሆን አይችልም። ማንም ምንም ሊል ይችላል ጓደኛህ ግን ያንተ ጉዳይ የእርሱም ሊሆን ይገባል። ሁሉን አቀፍ የሆነ ተግባቦትና እድገት ለጓደኝነት ቁልፍ ነገር ነው። አንተ ወደህ የጀመርከውና ያስደሰተህ አዲስ ነገር እርሱንም ሊያስደስተው ይገባል።

አዎ! ጓደኝነት ሁሉም ነገር ነው። ጓደኝነት ወንድማማችነት ነው፤ እህትማማችነት ነው፤ መደጋገፍ፣ መበረታታት፣ አለኝታ መሆን ነው። በየትኛውም መመዘኛ የእድገትህ ማነቆ፣ የስኬትህ ቀበኛ፣ የለውጥህ ተግዳሮት የሆነ ጓደኛ በህይወትህ ሊኖር አይገባል። ሳትጠይቅ የሚደግፍህ የእራስ ሰው ባለበት አለም አስፈላጊነቱን ነግረሀው፣ እንዲደግፍህ ተማፅነሀው እንኳን ፊቱን የሚያዞርብህ ጭራሽ በምትኩ አንተን ጥሎህ ለማለፍ የሚሽቀዳደው ጓደኛ፣ ጓደኛ ሳይሆን ቀበኛህ ነውና ጊዜ ሳታጠፋ መንገድህን ከእርሱ ለይ። እየሳቀ ከሚጥልህ እየተቆጣ፣ እየገሰፀ የሚያስተካክልህ ሰው ላንተ ትልቅ ስፍራ አለው። የእኔ የምትለው ማንኛውም ሰው ያንተ ለመሆኑ ማረጋገጫ መስፈርትና መመዘኛ አስቀምጥ። በአፉ እየደለለ በተግባር አብሮህ ካልሆነ፣ ምርጫ በማትሰጠው ከንግግር ይልቅ ተግባር የመመዘን መርህ፣ መስፈርቱን ባለማለፉ ቢኖርም ከማይጠቅምህ፣ ቢሄድም ከማይጎዳህ ሰው መለየት ይኖርብሃል።
ራቀው፣ ሽሸው፣ መኖሩ ትርጉም ካልሰጠህ፣ ምንም ካልፈየደህ በመሄዱ መፀፀት አያስፈልግምና ዙሪያህን ማጥራት ጀምር፣ ትክክለኛና እውነተኛ በምትላቸው የልብ ሰዎች አካባቢህን ማጠር ጀምር፤ ህይወትህንም ጥራት ባላቸው ሰዎች ሙላ።
ውብ ቀን ይሁንላቹ

From:- Motivate ur mind

@Kefilsfna_alem
@Kefilsfna_alem
share"
1.5K views per~fect , 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 11:45:42 እንደገና ትበረታለህ!

ማንነትህን የሚገልፀው ፊትለፊት ያለው ስጋዊ ሁኔታህ አይደለም፤ የሰው ልጅ ስትሆን መንፈስ የሚባል ድንቅ ስጦታ ተሰጥቶሀል። መንፈስህ እስካልተሰበረ እስከ ትንፋሽህ ማብቂያ ለመደሰት ዕድሉ አለህ!

ስጋህ ቢዳከም ሁሉም ነገር የጨለመ ቢመስልህም እንኳን ጨዋታው ገና ነው ምክንያቱም ሀያሉ መንፈስህ አፈር ልሶ የመነሳት ጥበብ አለው። እንደገና ትበረታለህ፣ እንደገና ትፀናለህ፣ እንደገና ህይወትን ታታጥማለህ፤ ወዳጄ መቼም አያበቃልህም!

From:- Motivate ur mind

@Kefilsfna_alem
@Kefilsfna_alem
share"
1.8K views per~fect , 08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:55:10 " ስትናገር የምታቀውን ለመድገም ግዜ ይኖርሃል ስታደምጥ ደግሞ የማታውቀውን ለማወቅ መንገድ ይከፍትልሃል...ባለህ ላይ ለመጨመር ማድመጥን ውደድ "

/ ዳኢ ላማ /



@Kefilsfna_alem
አሁኑኑ ይ ላ ሉን
2.2K viewsÑåŧňąëľ ꨄ︎ , edited  19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 08:04:08 ትናንትን መድገም

እውነት ነው ያለፉት ጊዜያት ዛሬ የደረስክበትን ወስነዋል፤ አሁን ወሳኙ ግን ትናንትን የምታይበት መነፅር ሳይሆን ነገን አሻግረህ የምታይበት ነው። ስለ ነገ ምን እያሰብክ ነው?

ትላንት አልፏል፤ ዛሬ እጅህ ላይ ነው፤ ይሄን ካላስተዋልክ ግን ትናንትን መድገም እጣ ፈንታህ ይሆናል!።
From:- Motivate ur mind

@Kefilsfna_alem
@Kefilsfna_alem
share"
2.2K views per~fect , 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:12:40
2.5K viewsÑåŧňąëľ ꨄ︎ , 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ