Get Mystery Box with random crypto!

✞ኬብሮን

የቴሌግራም ቻናል አርማ kebbron — ✞ኬብሮን
የቴሌግራም ቻናል አርማ kebbron — ✞ኬብሮን
የሰርጥ አድራሻ: @kebbron
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.89K
የሰርጥ መግለጫ

👉በዚህ ቻናል
📖የተመረጡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
✍ተከታታይ ታሪኮች
✍ ወግ
✍ ብሂላተ አበው
✍የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ
✍ከተለያዩ መፃህፍት እና ንግግሮች የተመረጡ ፅሁፎችን
" ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤"
(1ኛቆሮ 8:2)
💚💛❤️ማንኛውምንም ጠቃሚና አስተማሪ ፅሁፍ ካሎት @Teshubotላይ ይላኩልን*

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-06 06:59:18 መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖ እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖ ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖ የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖ ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እእንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡
❖ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨
❖ ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
“በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖ እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
❖ “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
703 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 06:59:18
#ይነበብ

ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡
_________
662 views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 09:36:50 ✞ኬብሮን

⨳የታመሙ ባንቺ ይፈወሳሉ፣የቆሰሉም ባንቺ ይድናሉ።


⨳እመቤቴ ማርያም ሆይ፥ጌጤ ሽልማቴ ሆይ፥ክብሬ ገናንቴ ለችግሬ ሀብት ባለፀግነት ለልምሾነቴም ብርታት ነሽ።

፦አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


@kebbron
@kebbron
677 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-28 11:08:34 ✞ኬብሮን

ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ወጋገን
ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ወጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሐን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጲያዬን

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድን



@kebbron
@kebbron
766 viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 07:35:59 ✞ኬብሮን


መስከረም 12
ቅዱስ ሚካኤል

መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

በዚችም ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ላከው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው። ንጉሱም ሚስት አግብቶ ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
ለንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገለት ተአምር


ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ዳዊት በኋላ በእስራኤል እንደ ሕዝቅያስ ያለ ሌላ ጻድቅ ንጉሥ አልተነሣም፡፡ ከሕዝቅያስ በኋላ የተነሡት ሁሉም ጣዖትን አምልከዋል፣ ለጣዖታቱም የሚሆን መሠዊያ ሠርተዋል፡፡ ንጉሡ ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ግን ጣዖታትን ሰባብሯቸዋል፣ የእስራኤል ልጆች ያመልኩት የነበረውን የነሐስ እባብ ቆራርጦታል፡፡ እግዚአብሔርንም በማመኑ መንግሥቱ እጅግ ሰምሮለታል፡፡ እግዚአብሔርም ያሳጣው በጎ ነገርም የለም፡፡

ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዘመን የፋርሱ ነጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ኢየሩሳሌምን ከበባት፡፡ ይህም ሰናክሬም በወቅቱ እንደ እርሱ ያለ ኃይለኛ የለም ነበርና ሁሉም የምድር ነገሥታት ይፈሩትና ይገዙለት ነበር፡፡ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም ግርማና የጦሩ ብዛት የተነሣ ፈርቶ ኢየሩሳሌምን እንዳያጠፋት ብዙ ወርቅና ብር እጅ መንሻ ቢልክለትም ሰናክሬም ግን እጅ መንሻውን አልቀበልም ብሎ ኢየሩሳሌምን ያጠፋ ዘንድ ተነሣ፡፡ ለሕዝቅያስም ‹‹አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእኔ እጅ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም›› የሚል የስድብን ቃል ላከለት

ሁለተኛም በልዑል እግዚአብሔር
ላይ የስድብን ቃል ጽፎ ደብዳቤ ላከለት፡፡ ሕዝቅያስም ይህን ሲሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ አለቀሰ፡፡ ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ የሰናክሬምን ድፍረትና በኢየሩሳሌምና በሕዝቧ ላይ ሊያደርስ ያሰበውንም ጥፋት ወደ እግዚአብሔር አሳሰበ፡፡ ቀጥሎም ሕዝቅያስ ሰናክሬም የተናገረውን ይነግሩት ዘንድ ስለ ሕዝቡም እንዲጸልይ ለነቢዩ ኢሳይያስ መልእክት ላከበት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር አመለከተ፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ስለ ንጉሡ ለነቢዩ መልእክትን አመጣለት፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም የመጣለትን መልስ እንዲህ ብሎ ለሕዝቅያስ ላከለት፡- ‹‹ልብህን አጽና፣ አትፍራ፡፡ በዓለሙ ሁሉ እንደ እርሱ ያለ ያልተሰማ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ሥራ በሰናክሬም ላይ እግዚአብሔር ይሠራል›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ 185,000 (መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ) የፋርስ ሠራዊቶችን በአንድ ሌሊት ገደላቸው፡፡ 2ኛ ነገ 17፣19፡፡

የለኪሶ ሰዎችም ሲነጋ በተነሡ ጊዜ ምድሪቱን በ ሬሳ ተሞልታ ስላገኟት በድንጋጤና በፍርሃት ከንጉሣ ጋር ሸሽተው ነነዌ አገር ገቡ፡፡

ንጉሡ ሰናክሬምም ወደ አምላኩ ወደ ጣዖቱ ቤት ገብቶ ሲጸልይ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ መትተው ገደሉትና ወደ አራራት ኩበለሉ፡፡2ኛ ነገ ምዕራፍ 19፡፡ ንጉሥ ሕዝቅያስም ከሰናክሬም እጅ ያዳነውን እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡

ከዚህም በኋላ ሕዝቅያስ ታሞ ለሞት በደረሰ ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹እግዚአብሔር ‹ትሞታለህ እንጂ አትድንም› ብሎሃል›› አለው፡፡ ነገር ግን ሕዝቅያስ አሁንም ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ ጸሎቱን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ቅዱስ ሚካኤል እግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ መጥቶ ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ሄዶ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት እንደተጨመረለት እንዲነግረው ያዘዘው፡፡

መልአኩ እንዳዘዘው ነቢዩ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን "እግዚአብሔር የአባትህ የዳዊት አምላክ ጸሎትህን ሰማሁ፣ ዕንባህንም አየሁ፣ እነሆ እኔ አድንሃለሁ፡፡ በዘመኖችህም 15 ዓመት ጨምሬልሃለሁ፡፡ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ፡፡ ይህችን አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ›› ብሎሃል ብሎ የተላከውን ነገረው፡፡ ከዚህም በኃላ ንጉሥ ሕዝቅያስ የእግዚአብሔር ኃይል ስላደረበት የምድር ነገሥታት ሁሉ ፈርተውት እየተገዙለት እጅ መንሻን ያገቡለት ጀመር፡፡ ንጉሡም ዕድሜው ከተጨመረለት በኃላ ሚስት አግብቶ ምናሴን እስኪወልድ ድረስ ቆየ፡፡ በመንበረ መንግሥቱም 29 ዓመት ነግሦ ከኖረ በኋላ እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም ዐረፈ፡፡
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን




@kebbron
@kebbron
872 views04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 07:24:48
664 views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 16:53:46 ✞ኬብሮን


እንደው በቸርነቱ እሱ ይቅር ባይለን
ምን እንኖለን ብለን ግን አስበን እናውቃለን
በተለይ እንደኔ እየኖረ ቤቱ ትዕዛዙን ተዳፍሮ
ለክፍት ለስህተት በቂ ጊዜ ኖሮ
ለንስሀ ሲሆን ሚያበዛ ቀጠሮ!!!!


ወ/ገብርኤል
10/2014



@kebbron
@kebbron
6.2K viewsedited  13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-15 15:19:18 ✞ኬብሮን


ሰላም

❖ መቼም በዚች ምድር ስንኖር የጎደሉን ብዙ ነገሮች ይኖራሉ ሰለነሱ ግን ምንያህል አስበን እናውቃለን አስተውሉ ለምሳሌ እኔ አይናፍር ነኝ ልበል ይሄም በመሆኑና ብዙ ነገሮችን አጥቻለው ብዬ ላስብ ብዙ እንስቶች በተለያየ መንገድም ቀረቡኝ ልቤ የሚያስበው ሌላ ነገር ነው ግን አይናፋርነቴ በልቤ ያለው ሸፈነው አስበው ከነበረው ሴሰኝነት ባንድም በሌላም መንገድ አገደኝ ይሄን ባሕሪ ፈጣሪ ሰቶኝ ቢሆን ምንአልባትም ከባድ የሚባለው ዝሙት እፈፅም ነበር። ለምሳሌ ይሄን አቀረብኩ እንጂ ሁላችንም የጎደለን አስበን ያ የጎደለን ነገር ቢኖርስ ብለን እስኪ እናስብ ተረቱም ሳይደግስ አይጣልም አይደል የሚለው።

ፈፀምኩ መልካሙ ሁሉ ይግጠማችው



@kebbron
@kebbron
775 viewsedited  12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 12:49:15 ኬብሮን

“እናንተ እምነት የጎደላችሁ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ”
(የብጹዕ አቡነ ሽኖዳ አባታዊ ምክር)
እኛ ከእግዚአብሔር እድንርቅ ካደረጉን ነገሮች አንደኛው ጭንቀት ነው ። ጭንቀት
ማለት ስለተከሰቱና ይከሰታሉ ተብለው ስለሚታሰቡ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ
ጉዳዮች አብዝቶ በማሰብ በስጋት ተውጦ መረበሽ ማለት ነው። ዓለም በብዙ
አስጭናቂ ጉዳዮች በመሞላቷና ሰውም የሚኖረው ዓለም ላይ እንደመሆኑ
አብዛኛው ሰው ሊጨነቅ ይችላል። “ጭንቀትን የተመላ ይህ ዓለም ያልፍ ዘንድ
ይቸኩላል” ዕዝ.ሱቱ 2፥27 እንዳለ ዕዝራ። ኦክስፎርድ ጭንቀት የሚለውን
ሲተረጉመው " ከቁሣዊ ነገሮች ፍላጎት የሚመጣ ግፊት ወይም ውጥረት
ይለዋል " የተሻለው ትርጉሙ ግን አላስፈላጊ ነገሮችን ከመፈለግ የተነሣ
የአእምሮ ወይም የስሜት ድካም ፤ ውጥረት ፤ ወይም ሕመም ማለት ነው ።
ጭንቀት ለሕይወታችን ከምንፈልጋቸው ወይም አላስፈላጊ
ከሆኑ ነገሮች ፍላጎት የሚመጣ ግፊት ወይም ውጥረት ነው ። ስለሆነም
የጭንቀት መንስኤው ምንድን ነው ? ስንል # ተስፈኝነት ሆኖ እናገኝዋለን ።
በአጠገባችን ካሉ ሰዎች ቃል ከገቡልን ፤ ከሚቀርቡን ፤ ከቤተሰቦቻችን ወዘተ
የምንጠብቀው አለ ። ተስፈኝነት በሁለት መንገዶች ሊመጣ
ይችላል ። የመጀመሪያው ስለ ሰዎች ያለን ተስፈኝነት አለ ። ሌላውኛው ሰዎች
ስለ እኛ አላቸው ብለን የምናስበው ነው ።
በማንኛውም መንገድ የተጨነቀ ሰው ከገጠማችሁ ከሁለቱ በአንዱ ምክንያት
እነደሆነ ታረጋግጣላችሁ ። ሌላ ሰው ለእኛ ዝቅተኛ ግምት ሠጥቶን ሊሆን
ይችላል ። ወይም እኛ
ራሳችንን ዝቅ አድርገነው ሊሆን ይችላል ። ወይም እግዚአብሔር እንደተወን
አድርገን ልንወስድ እንችላለን ። ወይም ከእግዚአብሔር እንደራቅን ሊሠማን
ይችላል ። ጭንቀት ከእነዚህ የአንዱ ስሜት ውጤት ነው ። የቁስ እቃ ፍላጎት
እንድንጨነቅ ያደርጋል ። ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም አንዳንድ ጊዜ
አወንታዊ በሆነ መልኩ ለስሜቱ ምላሽ እንሰጣለን ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ
አሉታዊ መልስ እንሰጣለን ። ሌላ ጊዜ ደግሞ አወንታዊም አሉታዊም ሳይሆን
ይቀራል ።
ከጭንቀት ለመላቀቅ የሚረዳ ዋነኛው ዘዴ ተፈጥሮአዊ ማንነታችንን ማሰብ ነው
። ቁሣዊ ሆነን
አልተፈጠርንም ። የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አርአያ እና አምሳል ነው ።
መቅደሱ ሆነን ነው የተፈጠርነው ።
ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ነው የተፈጠርነው ። ግፊቱም ፤ ጭንቀቱም
፤ሕመሙና ፤ውጥረቱ ፤ በመጣ ጊዜ ለእግዚአብሔር አሳልፈን መስጠት
ይኖርብናል ። ከእግዚአብሔር ኃይል በላይ የሆነ ግፊት ወይም ውጥረት የለም ።
ስለሆነም እኔ ተሸክሜ ከምጨነቅ እግዚአብሔር እኔን ሆኖ እንዲሸከም
አደርጋለሁ ። እርሱ ጫናወቻችንን ያቀላል ።
ዮሴፍ በብዙ ጫናወች ውሰጥ ይኖር ነበር ። ወድሞቹ ጉድጓድ ላይ ሲጥሉት
ምናልባት መረዳት በማይችልበት በሕፃንነቱ ጊዜ ነበረ ። እንደገናም ለባርነት
ሸጡት ። ከቤተሰቡም ጋር ተለይቶ መኖር ጀመረ ። የንጉሱ የፈርኦን ሚስት
በሐሰት ከሰሰችው ። በዚህም የተነሳ እስር ቤት ተጣለ። በእስር ቤት እያለ
ማንም የሚያስታውሰው አልነበረም ። ይህ እንግዲህ መጠነ ሰፊ ወደ ሆነ ጫና
ውስጥ ያመጣዋል ። ሆኖም ግን ዮሴፍ እነዴት ለመፍታት ሞከረ ? ችግሩን
እነዴት ተቋቋመው ? በእያንዳንዱ ሁኔታ ዮሴፍ ራሱ ዮሴፍ ነበረ ።
አልተለወጠም ። በሁሉምሁኔታዎች ተመሣሣይ ፤ ማንነት ፤ ፍቅር ፤ እምነት ፤
ነበረው ። እግዚአብሔርን አዘውትሮ ይጠራ እና ይለምን ነበረ ። እግዚአብሔርም
ሁል ጊዜ አጠገቡ ነበረ ።
ቦኑ እንከ ኢይከውነነ ናብእ መሥዋዕተ ስብሐት በኩሉ ጊዜ ለእግዚአብሔር ፍሬ
ከናፍሪነ ከመ ነእመን በስሙ
‹‹እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ
የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ ለእርሱ እናቅርብለት።›› ዕብ 13፡15

share ydrg
@kebbron
@kebbron
962 viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-01 08:23:16 ​​#ነሐሴ_26
#አቡነ_ሃብተ_ማርያም_ጻድቅ

እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው:: "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው:: ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል::

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች:: በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ ምጽዋትን ወዳጅ ቡርክት ሴት ነበረች:: እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር::

ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች:: ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች::

ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ:: ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር::

የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል:: ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ:: ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል:: የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል::

ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል:: በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም::

ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ::
በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ:: (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው)
በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ::
ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው::
በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ:: (ካህን ናቸውና)
ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ::
በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን መከፋትን አላሳደሩም::

በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር:: ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው::

"1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ
2.ስለ ምናኔሕ
3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ
4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ
5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ
6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ
7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::"

"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው::

ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: በዝማሬም ወሰዷት::

አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
1.1K views05:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ