Get Mystery Box with random crypto!

✞ኬብሮን: #ያቺ_ሰአት ።እጅግ ወኔ የተሞላው እና የሚነሽጥ ለሊት ነበር ንጉሱ ባስነገሩት አዋጅ | ✞ኬብሮን

✞ኬብሮን:
#ያቺ_ሰአት

።እጅግ ወኔ የተሞላው እና የሚነሽጥ ለሊት ነበር ንጉሱ ባስነገሩት አዋጅ መሠረት ማንም ከቀየው የቀረ ያለ አይመስልም የወራት የመንገዱ ጉዞ ሣይበግራቸው ሁሉም ቦታቦታውን ይዞል:ካህናቱ በተተከለው ድንኳን ውስጥ ጽላቱን ይዘው ማህሌቱን ተያይዘውታል በሌላ ወገንም ቅኔው እንደጉድ ይዘረፋል:: ህዝቡም ቢሆን "በእውነት ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላል" የሚለውን ቅዱስ ቃል በመቀበል ሀገራቸውን ሊበትን ሀይማኖትን ሊያጠፍ የመጣውን ጠላት ለመመከት በንቃት ቆመዋል::
አንዳንዱ እንደመነሸጥ ሲያደርገው ከወደ ጥግ ወደ መሀል እየመጣ "ጦርሜዳ ላይ ጀርባዬን ተመትቼ ካገኘህኝ አንስተህ እንዳትቀብረኝ አሞራ ይብላኝ ፈርቼ ስሸሽ ነው እና ለፈሪ ሚገባው ይሄ ነው,: ግንባሬን ተመትቼ ካገኘህኝ ግን በክብር ቅበረኝ " ይላል
* ሰአቱ አልደርስያላቸውም ይቁጠነጠናሉ ግማሹ ጎራዴውን ይሞርዳል ግማሹ ጦሩን ይቀጠቅጣል ፈረሶቹም ቢሆን የበኩላቸውን ለመወጣት የቸኮሉ በሚመስል ሁኔታ ጭራቸውን እያወዛወዙ አለውልህ ይሉታል ጌታቸውን ባለፈረሱም ወገባቸውን መታመታ እያደረገ እንግዴ ፈረሴ አደራህን እንደ ይሁዳ በመጨረሻው ሰአት እንዳከዳኝ ባይሆን እንደ ሠማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጩፈረስ በርትተህ አበርታኝ ብሎ እንደወዳጁ ግንባሩን ሣም ያደርገዋል::
ፉከራው እና ሸለልቶው ደርቶል
+መሣርያውን ታጠቅ ሁሉም ይሠናዳ(2)
+ልክ ማስገባት ነው ይሄን ወራዳ አረጎራው አረጎራው
ስትል አንዶ
ባለገር አይዞሽ እያለች ገብታ
በሚሸንጥ ቅላጼ
+ በለው በለው እና አሣጣው መድረሻ (2)
+የሠውልክ አያቅም ባለጌ እና ውሻ ሀሀሀሀሀ
!ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
!ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
!አባሮ ገዳይ
አይዞህ
!ቆንጥር ለቆንጥር
ዘራፍ
!በሀገር ለመጣ
ዘራፍ
የማይበገር በለው አስኪ አንተዬ አረ በለው እያለች አንዶም ትገባና
+ያሣደግነው ጥጃ ለምለም ሣር አስግጠን(2)
+ፈርገጥ ፈርገጥ አለ እኛኑ ሊረግጠን.........አረጎራው አረጎራው

ሀገሬን ሀገሬን ሀገሬን እላለው
ኢትየጵያን ለጠላት እንዴት እሰጣለው
,

አረስጡኝ እማ ዝናር ጥይቴን(2)
ገፍቶ ለመጣ ሰው መመከቻዬን,,,አረጎራው አረጎራው

አሁን ወሣኞ ሠአት ደርሳለች ሠማዩላይ ያለው ጭለማ ባታውን ለብርሀን ለመስጠጥ እየተንጎራደደ ነው አብዛኛው ጦረኛ ዳዊቱን ገልጦ የመጨረሻውን ፀሎት እያደረገ ነው ካህናቱም ወደ ቅዳሴ ለመግባት መዘጋጀት ጀምረዋል ያለውን ድባብ ግን ተውት ያቺ ነጫጭባ በእግሮ ፈርጥጣ ሮም ካልገባች ምን አለ በሉኝ በዚ መሀል ወደ አስር ሰአት ገደማ የጠለት ጦር መንቀሳቀሱን የሠሙት አጼውና ንግስቲቱ እንዲሁም መኳንቱ ሰራዊቱን ማንቀሳቀስ ጀመሩ እንግዴ የተናቀው አቢሲኒያው ህዝብ ማንነቱን ለማሳየት ከፈጣሪው ጋር መጋዝ ጀመር ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,



እንበለው እና ጉልበት ጉልበቱን
እያፎቀቀ ይውጣው ዳገቱን

በሉ እንግዴ ብእሬን ከትቼ ከአባቶቼጋ በመንፈስ ወደ ፍልሚያው ልግባ።


"አድዋ የሁላችንም ታሪክ"


ተጻፈ የካቲት 2012

@kebbron
@kebbron