Get Mystery Box with random crypto!

ፆም ገባ ይሉኛል ቀኑን ሙሉ ብፆም እስኪደርቅ አንጀቴ ቅቤና ሥጋውን ባርቀው ከፊቴ ዘውትር ብሰግድ | ✞ኬብሮን

ፆም ገባ ይሉኛል

ቀኑን ሙሉ ብፆም እስኪደርቅ አንጀቴ
ቅቤና ሥጋውን ባርቀው ከፊቴ
ዘውትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
ብቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዙም ባወድስ በሚጣፍጥ ዜማ
ድርሳናት ብተርክ ሚስጥር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ግዕዝን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴf
ሀሜትና አድመኝነት ካልጠፋ ከቤቴ
እኔን ብሎ ጿሚ ከንቱ ነው ፀሎቴ
ፈጣሪ ያዝንብኛል ፍቅር በማጣቴ


ምንጭfb