Get Mystery Box with random crypto!

✞ኬብሮን ብሂላተ አበው እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ | ✞ኬብሮን

✞ኬብሮን

ብሂላተ አበው


እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ ›› አባ እንጦንስ

ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል›› ቅዱስ አትናቴዎስ

ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስን ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢአተኞች የሚገቡበት የገሃነም እሳት ግን ለዘላለም እንዲሁ ይኖራል፡፡›› ቅዱስ ሚናስ

በማንም ላይ ክፋትን አትሥሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› ታላቁ አባ መቃርስ

ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› ቅዱስ አርሳንዮስ

ቤተክርስቲያን መጠሪያችን ነች ፤ ቤተ ክርስቲያን የኖኅ መርከብ ነች ፤ በውስጧ እንጠለላለን ከውጪው ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› ቅዱስ እንድርያስ

?? ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ
??
ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከሆነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሞላን እንሆናለን ›› አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን

የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› ብፁዑ አቡነ ጎርጎሪዮ ካልዕ

ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊትን በሙሉ ስትጸልይ እደር›› ቅዱስ ይስሐቅ ሶሪያዊ



እራ?ራስህን በሐሰት አትውቀስ፤ ራስን መክሰስ ትህትና አይደልም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው›› ቅዱስ ስራፕዋን

አንደበቱን ከቧልት ፣ ከሐሜት፣ ያየውንም ምሥጢር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከሃልዮ ኃጢአት ያርቀዋል፡፡›› አርጋዊ መንፈሳዊ



?‹ ጸጋ ሲሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ›› ማር ይስሐቅ

@kebbron
.