Get Mystery Box with random crypto!

✞ኬብሮን በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በ | ✞ኬብሮን

✞ኬብሮን

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡

በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ? ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡ በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡ በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡

በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡ በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡ ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡

በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡ በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡

ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ? መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡

መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ጌጥ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡

አምስቱ የንስሐ መንገዶች



@kebbron
@kebbron