Get Mystery Box with random crypto!

በህንድ ሀገር የተሰማው አነጋጋሪ ዜና በህንድ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር የሄደችበት ባል በበቀል ያ | 🌎ከአለም ድንቃ ድንቅ🌍

በህንድ ሀገር የተሰማው አነጋጋሪ ዜና

በህንድ ሚስቱ ከሌላ ወንድ ጋር የሄደችበት ባል በበቀል ያፈቀረችውን ሰው ሚስት አገባ

በህንድ ቢሃር ግዛት ኔራጅ እና ሩቢ ዴቪ የተባሉ ጥንዶች እ.ኤ.አ በ2009 ጋብቻቸውን ፈፅመው አራት ልጆችን ወልደው ለመሳም በቅተዋል። በጊዜ ሂደት ግን የኔራጅ ሚስቱ ሙከሽ ከሚባል ሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት ትጀምራለች። ይህንን ግንኙነት ለመቁረጥ የከበዳት ሩቢ ባሏን ትታ ከሙከሽ ጋር ለመኖር ትወስናለች።

ኔራጅ ሽማግሌዎችን ልኮ ባለቤቱን እና ሙከሽ ቢያስመክርም ፍቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም።ኔራጅ ለፖሊስ ክስ ቢመሰርትም ወዳና ፈቅዳ ወደ ሙከሽ ቤት መግባቷን ትናገርና ክሱ ውድቅ ይሆናል።

ኔራጅ ጥላው የሄደችው ሚስቱ ያገባት ግለሰብ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት መሆኑን እንደ ጥረ አጋጣሚ ይወስደዋል።ሚስቱ ወደ ቤት የመመለስ ፍላጎት እንደሌላት ካየ በኋላ የሙኬሽን ሚስት እንድታገባው ይጠይቃታል። እሷም በጥያቄው ተደስታ ጥንዶቹ ባለፈው ወር ጋብቻቸውን ፈፅመዋል።አስገራሚው የፍቅር ታሪክ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በካጋሪያ አውራጃ ውስጥ የከተማው መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ሁሉም ልጆች ወደ እናቶቻች በሚል ስምምነት ፈፅመዋል።https://t.me/kealemdinkadink