Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ልጅ አካል አስደናቂ እውነታዎች 1. የአንድ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ያለው ደም ክብደት ከአ | 🌎ከአለም ድንቃ ድንቅ🌍

የሰው ልጅ አካል አስደናቂ እውነታዎች

1. የአንድ ሰው በሰውነቱ ውስጥ ያለው ደም ክብደት ከአጠቃላይ ከሰውየው ክብደት 8 በመቶ ብቻ ይመዝናል፡፡
2. ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሁለት ኩላሊት ቢኖረንም በሕይወት ለመኖር አንዱ ብቻ ያስፈልገናል፡፡
3. የሰው ልጅ አፍንጫ 1 ትሪሊዮን የተለያዩ ሽታዎችን መለየት ይችላል፡፡
4. ቆዳችን ትልቁ የሰውነታችን አካል ሲሆን ከክብደታችን ውስጥ 15 በመቶውን ይይዛል፡፡
5. ልባችን በአማካኝ በሕይወት ዘመናችን ለ3ቢሊዮን ያህል ጊዜ ይመታል፡፡
6. ሳይንቲስቶች የምናዛጋበትን ትክክለኛ ምክንያት እስካሁን አልደረሱበትም፤ነገር ግን የሰውነት ሙቀትን ለማመጣጠን እንደሚረዳ ይታመናል፡፡
7. የእጃችን ጠፍር ከሞትን በኃላ አያድግም፡፡
8. የሰው ልጅ ብቸኛ አገጭ ያለው ፍጥረት ነው፡፡
9. አውራ ጣት የራሱ የሆነ ትርታ አለው፡፡
10. በሰው አፍ ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ቁጥር በዓለማችን ከሚኖረው ሕዝብ ብዛት እኩል ወይም ሊበዛ ይችላል፡፡
11. በአንድ ቀን ደማቸን 19,312 ኪሎሜትር ያህል ይሮጣል፡፡
12. የሰው ልጅ አይን 10 ሚሊዮን የተለያዩ ቀለማትን መለየት የሚችል ሲሆን፤ ነገር ግን አእምሮአችን ሁሉንም ማስታወስ አይችልም፡፡
13. አንድ ሰው በአማካኝ 35 ቶን ወይም 35,000 ኪሎግራም ክብደት ያለው ምግብ በዕድሜ ዘመኑ ይመገባል፡፡
14. በየአንዳንዱ ቀን የሰው ልጅ 1 ሚሊዮን የቆዳ ሐዋሳት (ሴል) ያጣል፡፡ ይህ ደግሞ በዓመት 2 ኪሎ ይደርሳል፡፡
15. በሰውነታችን ውስጥ ትልቁ ሕዋስ (ሴል) በሴቶች ማህፀን ውስጥ የሚገኘው እንቁላል ሲሆን የለማጉያ መነፅር እንዲሁ በአይናችን ማይት ይቻላል፡፡ በሰውነታችን ውስጥ ትንሹ ሴል ደግሞ የወንድ ዘር ፈሳሽ (ስፐርም ሴል ) ነው፡፡
https://t.me/kealemdinkadink