Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲ | ከ

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጭሮ ከተማ ከፖሊስ ጋር በተደረገው ውይይት ሕዝቡ ወደ ቤቱ እንዲመለስ በከተማው የመጣ እንግዳ የለም የሚል ከፖሊሶቹ ሃሳብ የቀረበ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች ሕገ ወጦቹ ግለሰቦች በአንድ ሆቴል ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስና ከአባቶቻችን በተሰጠን መመሪያ መሠረት ግቢያችን ውስጥ ሆነን እየዘመርን እና ወንጌል እየተማርን ቤተ ክርስቲያናችን እንጠብቃለን፡፡

ሀገረ ስብከቱና የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት የመጡት ሕገ ወጥ ግለሰቦች ወደ መጡበት ቦታ ካልተመለሱ ሕዝቡን ማሰናበት አንችልም፣ ሕዝቡም እሺ አይለንም በሚል ለመንግሥት የጸጥታ አካላት ሃሳባቸውን ገልጸዋል፡፡

ከመንግሥት የመጡ አካላትም ሕዝቡ ከስሜተኝነት እንዲወጣ የሃይማኖት አባቶች እንዲያረጋጉት መመሪያ ሰጥተው መመለሳቸውን ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በንቃት ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቀ በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ የማረጋጊያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል።

#ምንጭ ምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
#ሐረር

@KeAbawandebet