Get Mystery Box with random crypto!

ለዓመታት በልጅ እጦት የተፈተኑ ቤተሰቦች በአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ምልጃ የሆዳቸውን ፍሬ እያገኙ ነው | ከ

ለዓመታት በልጅ እጦት የተፈተኑ ቤተሰቦች በአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ ምልጃ የሆዳቸውን ፍሬ እያገኙ ነው.......
~~~~~

ይህኝ ጥንዶች ትዳር ከመሰረቱ በኃላ ለሰባት ዓመታት የሆዳቸውን ፍሬ ፣የአይናቸውን ማረፍያ የሚሆን ልጅ ፍለጋ ለማግኘት በብዙ ተፈትነዋል።

ከዘመናዊ ህክምና እስከ ወዳጅ ዘመድ ምክር ፈጻሚነት ድረስ እየከወኑ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆኑ እንቦቅቅላ ልጃቸውን ለማግኘት ደክመዋል።

ነገር ግን አንዳች ጠብ ያለላቸው መፍትሄ አተው ለሰባት ዓመት ዘለቁ።ሁሉም መፍቴሄዎች ከድካም በቀር አንድ በጎ ነገር ታጣበት።

በስተመጨረሻ የቤቱ ራስ የሆነው ባል ወደ አርባ ምንጭ ዝጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በመምጣት ጸበላቸውን በመጸበል ፆም ጸሎት በመያዝ ጻዲቁን በሱባኤ አናገራቸው።

የለመኑትን በጎ ነገር ቸል የማይለው የአርባምንጩ ዝጊቲ አቦ አነሆ በምልጃ ረድኤታቸው ደርሰውለት ከዓመታት በኅላ እቅፋቸው በልጅ ጠረን ይረሰርስ ዘንድ ቅዱስ እግዚአብሔር ፈቀደ።

"ጻድቁን ልጅ ለምኜ ሰጥተህኛል እና እነሆ የአንተ የሆነውን ልጄን አንተው ውሰደው " ሲሉ የህፃኑ ቤተሰብ ሐብተወልድ ስመ ክርስትና በአርባምንጭ ዝጊቲ አቦ አስነስተው በሐዘን እና በተሰበረ ልብ ወደ አጥቢያው የመጣ ቤተሰብ በፍሰሐ እግር ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ።

እግዚአብሔር ይመስገን !

ዝጊቲ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን - አርባምንጭ

@yeemariyaam21
@yeemariyaam21
@yeemariyaam21