Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4457 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች የኮሮና | ቃና ዜና ቅምሻ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4457 የላብራቶሪ ምርመራ ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4532 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (5 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ከአንድ የ75 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ከዚህ በተጨማሪ በለይቶ በህክምና ማዕክል ውስጠ ክትትል ላይ የነበረች የ34 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቷ ያለፈ ሲሆን በጠቅላላ ሁለት ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አራት (74) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና አንድ (91) ሰዎች (67 ከአዲስ አበባ፣ 16 ከሶማሊ ክልል፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1213 ነው።