Get Mystery Box with random crypto!

#ችግርን_ማቃለል ~በሰዎች ህይወት በተለያዩ አጋጣሚዎች በድንገትም ይሁን ታስቦበትም በሚደረጉ ድር | Hossana Gospel movement

#ችግርን_ማቃለል

~በሰዎች ህይወት በተለያዩ አጋጣሚዎች በድንገትም ይሁን ታስቦበትም በሚደረጉ ድርጊቶች መሃከል ችግር ይፈጠራል ..
~ችግር ማለት ሰዎች በራሳቸው አቅምና ጥረት ለመፍታት ወይም ለማስተካከል ያልቻሉትን ነገር ችግር በማለት ይጠሩታል..

~ዛሬ ግን ልነግራቹ የምወደው ነገር ቢኖር ችግርን ማቃለል የምትችሉበትን መንገድ ነው...
፨በራሳቹ ባላቹ አቅም ልትወጡት ያልቻላችሁበትን ቦታ ችግር ውስጥ ነኝ ትሉታላችሁ...ስለዚህ ከችግራችሁ ውስጥ ሊያወጣቹ የሚችለው ማነው...?
፨ችግር ከብዶባችኋል ታዲያ ከዚህ ሸክም ሊያሳርፋችሁ የሚችለው ማነው...?
፨ችግራቹ አስጨንቋቿል ታዲያ ከጭንቀታችሁ የሚገላግላችሁ ማነው....?

፨ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ሁሉ ክርስቲያን መልስ አለው....ነገር ግን ክርስቲያንም በእነዚህ ችግሮች ውስጥ ሲዋኝ እንመለከታለን እንዴት...?

~ክርስቲያን በህይወት የሚፈራረቁ ችግሮችን ከራሱ አቅምና ችሎታ ጋር ማስተያየት ከጀመረ በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት ይደክማል.....ክርስቲያን ችግሮቹን ማየት ያለበት አብሮት ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ነው።

~ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ኢየሱስ እንዲህ ብሎ የተናገረው ቃል አለ . ."በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ...ነገር ግን እኔ መከራውን አሸፌፋዋለው.."
~ልብ እንድትሉ የምፈልገው ነገር ቢኖር በዓለም ሳላችሁ መከራ ፣ ችግር አለባችሁ የሚለውን ቃል ሳይሆን "እኔ መከራውን አሸንፌዋለው " የለውን ቃል ነው...ስለዚህ አስተውሉ ችግራቹን ከራሳቹ ጋር አታስተያዩ ..አብሮአቹ ካለው ጌታ ጋር አስተያዩ ያኔ ችግራቹ ሁሉ የተሸነፈ ሆኖ ታገኙታላችሁ..ሀሌሉያ!!!
~ችግር ብላትቹ የጠራቹት ከአቅማችሁ በላይ ስለሆነ ነው ነገር ግን ችግራቹ ከጌታቹ በታች ነው ...ስለዚህ ለችግራቹ እንዲህ ብላቹ ንገሩት...(ሮሜ 8፥37)
"..በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን.."
~ችግራችሁን በጌታ እበልጥሃለው በሉት...ሀሌሉያ

ክርስቲያን የማይፈራበት ምክኒያት አለው..እርሱም ጌታ አብሮት ስላለ ነው..እስቲ አንድ ነገር ላስቸግራቹ ስለችግሩ ማሰብ ትታችሁ አብሮሃቹ ስላለው ጌታ ማሰብ ጀምሩ ችግራችሁን ፈልጋችሁ አታግኙትም..።

ስለጌታ ማሰብ ስትጀምሩ ለችግራቹ ሁሉ መፍትኤ የሆኑ የጌታ ቃሎች ትዝ ይላቹ ይጀምራል...
"..እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለው.."
(ማቴ 11፥28)

"..እርሱ ስለእናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት.." (1ጴጥ 5፥7)

~በህይወታችሁ ለሚገጥሟችሁ ችግሮች መድሃኒቱ እግዚአብሔር ነው።ሀሌሉያ!!!

ክርስቶስ ኢየሱስን የህይወታችሁ መድሃኒት አድርጋችሁ ያልተቀበላችሁ በውስጥ መስመር አናሩረኝ ...

"ተባርካችኋል"

#ወንጌል_ይለውጣል