Get Mystery Box with random crypto!

ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡ ፡ ❖ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” | "ቃለ እግዚአብሔር "

ነጥቀው በገነት

በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡



❖ ወዲያውኑ “ወአምጽኡ ሎቱ ማዕጠንተ ወርቅ” ይላል የወርቅ ማዕጠንት ለዮሐንስ አምጥተውለት፤ “ወዕጥን ሥጋሃ ለማርያም መዓልተ ወሌሊተ” ይላል የቅድስት ድንግል የከበረ ሥጋዋን በመዓልትና በሌሊት ዕጠን አሉት፤ ዮሐንስም ይኽነን ክብር በመቀበሉ ደስ ብሎት ሥጋዋን እያጠነ “ወፍና ሠርክ ያመጽዕ ሎቱ ራጉኤል መልአክ ኅብስተ ሰማይ” ይላል ሰርክ ሲኾን ራጉኤል መልአክ ሰማያዊ ኅብስት ሰማያዊ መጠጥ እያመጣለት ያን እየተመገበ በገነት ቆይቷል፡፡

❖ ኋላም በጌታ ፈቃድ ከተቀሩት ሐዋርያት ጋር ተገናኘ፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን ነገር እንደምን እንደኾነ ሲጠይቁት ርሱም በገነት ያየውን ነገር ነገራቸው፤ እነሱም ይኽነን ታላቅ ምስጢር ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ሱባኤ ነሐሴ 1 ዠመሩ ነሐሴ 14 ቀን በኹለተኛው ሱባኤ ጌታ የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡

❖ በተወደደች ዕለት ነሐሴ 16 “ወአዘዞሙ እግዚእነ ለሰብአቱ ሊቃነ መላእክት ከመ ይጸውዕዋ ለምድር” (ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ምድርን ይጠሯት ዘንድ አዘዛቸው) እነርሱም ምድርን “ይኤዝዘኪ እግዚእነ ከመ ታውጽኢ ሥጋሃ ለእሙ ቅድስት” (ጌታችን የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ ያዝሻል) አሏት፤ ያን ጊዜ ልጇ “ንዒ ኀቤየ ወላዲትየ ከመ አዕርጊ ውስተ መንግሥተ ሰማያት” (ወደ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ እናቴ ወደኔ ነዪ) አላት፤ ያን ጊዜ በልጇ ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሐዱ፤ ነሐሴ 16 ዕለትም ከሞት ተነሣች፡፡

❖ ያን ጊዜ “ወረዱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት” ይላል ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ በታላቅ ግርማ ወረዱ፤ ነቢዩ ዳዊትም “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ” (ንግሥቲቱ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ደርባ ደራርባ በቀኝኽ ትቆማለች) እያለ ይዘምርላት ነበር፤ አየሩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመላ፤ እጅግ የሚያስደንቅ መዐዛ አካባቢን ዐወደው፡፡

❖ ስለ አካላዊ ዕርገቷ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ ፹፪ ላይ፡-
“አመ ነሥኡኪ እምኤዶም አዕላፈ ማሕሌት ጾታ
እንዘ ይጼልሉኪ ድንግል በአክናፈ መባርቅት ከመ ወልታ
ሰራዊተ ሰማይ ይቤሉ ለክብረ ፍልሰትኪ ግርማ ትርሲታ
መኑ ይእቲ ዛቲ ዘገዳመ ጽጌ ዕጥነታ
ወከመ ሠርጸ ጢስ ዘስኂን ይምዕዝ ዕጥነታ”

(ድንግል ወገኖች አመስጋኞች መላእክት በየነገድ በየነገድ ኾነው በመባርቅት ክንፎች እንደ ጋሻ ጋርደው ከኤዶም ገነት በተቀበሉሽ ጊዜ የሚያስደንቅ ክብር ለተገለጸባት ለዕርገትሽ የሰማይ ሰራዊት አበባ ካለበት በረሓ የምትወጣ መዐዛዋም ከነጭ ዕጣን ይልቅ የሚሸትት አወጣጧም እንደ ጢስ አወጣጥ የኾነችይኽቺ ማናት? ይኽቺ ማን ናት ይላሉ (መሓ ፫፥፲፮)) በማለት በአስደናቂ መልኩ ዕርገቷን ገልጸዋል፡፡

❖ ቅዱስ ያሬድም በዝማሬው ላይ “ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ” (እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ) ይለዋል፡፡

❖ ያን ጊዜ በታላቅ ክብር በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ሰማዩ ኹሉ በቅዱሳን መላእክት ተመልቶ የአምላክ እናት በክብር ስታርግ ተመለከተ፤ ያን ጊዜ ነገሩ ረቆበት ምን ይኾን እያለ ሲል ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችን ዕርገት እንደኾነና እጅ እንዲነሣ ነገሩት፡፡

❖ ርሱም “ከቶ ምን አርጌ ይኾን፤ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ ቀረኊ ዛሬ ደግሞ የርሷን ትንሣኤ ሳላይ ልቅር” ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ይላል ተበጻብጾ ሊወድቅ ወደደ፤ እመቤታችንም “አይዞኽ አትዘን እነሱ ሞቴን አይተዋል እንጂ ዕርገቴን አላዩም አኹንም እመቤታችን ተነሣች ዐረገች ብለኽ ንገራቸው” ብላ ለበረከት ሰበኗን ሰጠችው፡፡

❖ ርሱም በደስታ ተመልቶ ሐዋርያት ያሉበት በመኼድ የእመቤታችን ነገር እንደምን ኾነ ብሎ ጠየቃቸው፤ እመቤታችን ሞተች ቀበርናት አሉት፤ “መቼ ሞተች?” አላቸው በጥር አሉት፤ “መቼ ቀበራችኋት?” አላቸው በነሐሴ አሉ፤ ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተዉ ይኽ ነገር እንዴት ይኾናል አላቸው፤ ቅዱስ ጴጥሮስም ቶማስን ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ አላምን ብለኽ የጌታን ጐን የዳሰሰ እጅኽ ተቃጥሎ ነበር፤ አኹን ደግሞ እኛ ብንነግርኽ አላምን ትላለኽ ብሎ፤ “ወነሥአ መክርየ” ይላል መቆፈሪያ ይዞ ኼዶ ይቆፍር ጀመር።

❖ ርሱም የያዘውን ይዟልና ጸጥ ብሎ ይሰማቸዋል፤ ቈፍረው ሲያጧት ደነገጡ፤ ቶማስም አይዟችኊ አትደንግጡ እመቤታችን እኮ በመላእክት ምስጋና ወደ ሰማይ አረገች ብሎ ሰበኑን አሳያቸው፤ እነርሱም ለበረከት ሰበኑን ተካፍለውታል፡፡ ዛሬም ሐዋርያዊት የኾነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ይኽነን በማሰብ በመስቀል ሥር የሰበኗ ምሳሌ የሚኾን ሰፊ ጨርቅ ታደርጋለች፡፡

❖ ባመቱ ቶማስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በድጋሚ ሐዋርያት ሱባኤ ሲገቡ ክብር ይግባውና ጌታችን በደመና ነጥቆ ወስዶ ሥርዓተ ቊርባንን ፈጽሞላቸው፤ ስለ እናቱ ዕርገት በዓለሙ ኹሉ ዙረው እንዲያስተምሩ አዝዟቸዋል፡፡ እነርሱም ዓለምን ዞረው ወንጌልን ሲያስተምሩ የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገት ሰብከዋል አስተምረዋል፡፡

❖ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ ወደ ምጡቅ ሰማይ ስለተደረገው ዕርገቷ ፡-
“እንዘ ይፀውረኪ በሐቂፍ ወይስዕመኪ በአፍ
አመ አፍለሰኪ ወልድ ውስተ የማኑ ለዐሪፍ
ጽጌ ዕፀ ገነት ማርያም ዘትጼንዊ ለአንፍ
እንዘ ይትጓድዑ አክናፈ በክንፍ
ለቀበላኪ ወረዱ አእላፍ”

(ለአፍንጫ መዐዛን የምትሰጪ የገነት ዛፍ ማርያም ሆይ፤ ልጅሽ በክንዱ ዐቅፎ በአፉ እየሳመ በቀኙ ሊያሳርፍሽ ባሳረገሽ ጊዜ፤ አንቺን ለመቀበል ክንፍ ለክንፍ እየተጋጩ እልፍ አእላፋት መላእክት ወረዱ) በማለት አስተምረዋል፡፡

❖ በተመሳሳይ መልኩ ዳግመኛ አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው በቊ፹፬ ላይ፡-
“ትእምርተ ፍልሰትኪ እምድረ ጽጌ ድንግል በክልኤ
በደመና ሰማይ አርአየ ዘሐዋርያት ጉባኤ
ወእለ ሞቱ አንቅሐ እምከርሠ መቃብር ቀርነ ጽዋዔ
ለነሰ እንዘ ይብሉ ሶበ ሰማዕነ ውዋዔ
መሰለነ ዘበጽሐ ትንሣኤ”

(በኹለት ወገን ድንግል የኾንሽ ማርያም ሆይ አበባ ካለበት ምድር ወደ ሰማይ የማረግሽ ተአምር በሰማይ ደመና የሐዋርያት ጉባኤን አሳየ፤ የሞቱትንም ከመቃብር ውስጥ በተአምር ነጋሪት ድምፅ አስነሣ፤ ለእኛስ የምስጋና ከፍተኛ ድምፅን በሰማን ጊዜ የሙታን መነሣት የደረሰ መሰለን እስኪሉ ድረስ) በማለት ሐዋርያትን ተሰብስበው ሳሉ ዕርገቷን እንዲያዩ እንዳደረጋቸው ጽፈዋል፡፡

❖ ልጇ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር ዐድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ሞትን ድል ነሥቶ እንደተነሣ አማናዊት ታቦቱ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም በልጇ ሥልጣን ርሷ በሦስተኛው ቀን ተነሥታ ከልጇ ከንጉሡ ቀኝ በክብር ቆማለች (መዝ ፵፬፥፱)፡፡

❖ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በነሐሴ ፲፮ የቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል ብሔራዊ በዓል ተደርጎ በተለያዩ ሀገራት ሲከበር ዕርገቷ ይታሰብባቸው ከነበሩ ሀገራት ውስጥም ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ አንዶራ፣ ቺሊ፣ ኮሎምቢያ፣ ክሮሺያ፣ ኢኳዶር፣ ፈረንሳይ፣ግሪክ፣ ሊባኖስ፣ጣሊያን፣ ማልታ፣ ስሎቬኒያ፣ ፖላንድ፣ፖርቹጋል፣ሩማኒያ፣ ቺሊ፣ ሳይፕረስ፣ ሀይቲ፣ ሴኔጋል፣ ስሎቬኒያ፣ ስፔን፣ ካሜሩን፣ጋቦን፣ ሩዋንዳ፣ብሩንዲ፣ ሴኔጋል፣ቶጎ፣ኮትዲቭዋር፣ማዳጋስካር እና ሌሎች በርካቶች የዓለም ሀገራት