Get Mystery Box with random crypto!

inspire-youth

የቴሌግራም ቻናል አርማ kakuinspire — inspire-youth I
የቴሌግራም ቻናል አርማ kakuinspire — inspire-youth
የሰርጥ አድራሻ: @kakuinspire
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.04K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ወጣቶችን የሚያበረታታ .
ለነጋችን ምን ማድረግ እንዳለብን ?
አሁን ላይ ያለውን መጥፎ ባህሪይ.
ሊያስተካክል,ወጣቶችን ሚያነሳሱ ምን ማድረግ እንዳለብን ትምርት ሚሰጥ ቻነል ነው፡፡
የተለየ ምክር ከፈለጉ በግል እናማክራለን

------------------------

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-14 19:54:17 ትልቅ ራዕይ አለኝ!
=======

ትልቅ ራዕይ እንዳላችሁ ይሰማችኋል? እንደዚያ ካሰባችሁ ይህ ጽሑፍ ለእናንተ ነውና ማንበብን ቀጥሉ፡፡

አንድን ማድረግ የምትፈልጉትን መልካምና ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ የሆነን ራእይ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጋችሁ ትልቅ ብር፣ የትልቅ ሰው ድጋፍ፣ ትልቅ እውቅና፣ ትልቅ ስም እና የመሳሰሉት ነገሮች እንዳልሆኑ ላስታውሳችሁ፡፡ እነዚህና መሰል ሁኔታዎች በጊዜያቸው አስፈላጊ የመሆናቸውን እውነታ በፍጹም አንዘነጋውም፡፡ ሆኖም፣ የመነሻው ነጥብ ግን እነሱ አይደሉም፡፡ እነዚህን “ትልልቅ” ነገሮች ይዘው ከትንሽነትና ከተራ አመለካት ያልወጡና ጊዜያቸውንና ያላቸውን ትልቅ ነገር በከንቱ የሚያባክኑ ብዙዎች እንዳሉ አትዘንጉት፡፡

ትልልቅ ክንዋኔዎች የሚጀመሩት በትልቅ ልብና በትንንሽ ተግባራዊ እርመጃዎች ነው፡፡ ስለዚህም፣ ትንንሽ ነገሮችን ትልቅ የሚያደርጋቸው የልብና የአመለካከት ትልቅነት እንደሆነ ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡

የነበራችሁን ትልቅ ራእይ እውን የማድረጊያው ጊዜ እያለፈባችሁ እንደሆነ የምታስቡ ከሆነ ትንሽ መለስ በማለት አመለካከታችሁ ላይ ለመስራት ሞክሩ፡፡ ትልቅ ራእይ የሚፈልገው ትልቅ አመለካከትንና ትልቅ ልብን ነው፡፡

“ትልቅ ነገር ካላደረኩኝ” በማለት ቁጭ ብሎ ዘመኑን ከሚያሳልፍ ሰው ይልቅ በእጁ ያለችውን ትንሽ ዘር በትልቅ ልብ የሚዘራ ሰው የላቀ ስኬታማ ነው፡፡
58 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 07:02:06
101 views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 07:02:06
97 views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 07:01:58
96 views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 07:01:55
92 views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 06:13:01 የምናወጣው ቃል !

ዝም ማለት ያለማወቅ ምልክት አይደለም ወይም ስለተናገርን ጠንቅቀን አውቀናል ማለትም አይደለም ነገር ግን የምንናገራቸውን ነገሮች ጠንቅቀን መለየት መቻል አዋቂነት ነው !

" እያንዳንዱ ከእኛ የሚወጣ ቃል ሌሎች ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም እና ልንጠነቀቅለት ይገባናል !"

መልካም ቀን ተመኘኝ
98 views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 21:52:01 እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።

በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።

አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።

በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ  መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።

በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ  ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል።  ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።

በኖረበት  ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።

አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።

ይህ ታሪክ ለአብዛኞቻችን አስተማሪ ይመስለናል ።
በውስጣችን አዳፍነነው ያስቀመጥነው ተሰጥኦ እንዳለ እናምናለን ።

ይህን ተሰጥኦ ከውስጣችን ጎትቶ የሚያወጣልን ውጫዊ አካል አንጠብቅ ።

የተሰጠን ቀን ዛሬ ነውና ለማናውቀው ነገ ቀጠሮ አንስጥ ።

ስለ ነገ ማንም አያውቅም። የተሰጠን ዛሬ እንደሆነ አውቀን የተዳፈነውን ችሎታችንን አውጥተን ለሌሎች የብርሃን ችቦን እንለኩስ።

159 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-10 22:59:13 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው

1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ አላማና ህልም ያለው አገልጋይ ትሆናለህ፤

2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤

3. የመጣህበትን አትርሳ ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን!

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ
180 views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 12:24:14 ቀስት ወደ ፊት ሊስፈነጠር የሚችለው ወደ ኋላ በተለጠጠበት መጠን ነው።


ችግር ሲያጋጥምህ ደስ ይበልህ ከበፊቱ ወደ ተሻለው ልትስፈነጠር ነውና።ሁሌም ኢላማህን በመልካሙና በተሻለው ነገር ላይ ያነጣጥር!በፍጥነትም ትደርሳለህ።

መልካም የመስፈጠር ና የስኬት ቀን ይሁንልን ኪያ ነኝ ስኬት ማማ ላይ እንገናኝ
216 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 23:28:27
211 views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ