Get Mystery Box with random crypto!

Journalist Netsanet Getachew🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ journalistnetsanetgetachew — Journalist Netsanet Getachew🇪🇹 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ journalistnetsanetgetachew — Journalist Netsanet Getachew🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @journalistnetsanetgetachew
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 790
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለሁላችሁም በዚህ ቻናል የተለያዩ ዎቅታዊ እና እውነተኛ መረጃዎችን ታገኛላችሁ።
We are here to deliver updated News, Exclusive programs, Interviews, Entertainment and more Reliable and Updated Information about Ethiopia

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 16:47:01
መላው የሰቆጣ ነዋሪዎች በአሉባልት እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ሳይደናገሩ አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮምቦልቻ

ዛሬ በኮምቦልቻ ከከተማው የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ በከተማው ከሚታወቁ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጎ ነበር።

በዚህም መድረክ ፤ የተለያዩ ሀሰተኛ አሉባልታዎች በመንዛት ህዝቡን ለማሸበር የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸው ተገልጾ መላው ነዋሪ ተረጋግቶ በንቃት አካባቢውን በመጠበቅ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በከተማዋ እስከሁን ባለው ከ400 በላይ ባጃጆች እና 80 ሞተሮች በህግ ቁጥጥር ስር ገብተው ማጣራት ተደርጎ ወደየመጡበት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሁሉም ነዋሪ በቀበሌና ቀጠና ብሎክ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበትና በእቃ ዋጋ ላይ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ይደረግ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ደሴ

ዛሬ በደሴ ከአምስቱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ተደርጎ የነበረ ሲሆን በዚሁ መድረክ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎችን በማሰራጨት ህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ለማሳደር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም የከተማው ወጣት በሙሉ በሀሰተኛ ወሬ እና በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ሳይረበሽ ከመላው የከተማው ነዋሪ ጋር በመሆን አካባቢውን እና የከተማውን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል።

በከተማው የፀጥታ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ተነግሯል።

#ወልድያ

ወልዲያ ከተማ አዳሯ ሰላም የነበረ ሲሆን የዛሬ ውሎዋም ሰላም ነው። አሁንም ቢሆን መላው ነዋሪ ተረጋግቶ አካባቢውን በመጠብቅ የከተማዋን ሰላም ሊያረጋግጥ ይገባል ተብሏል። https://t.me/JournalistNetsanetGetachew
80 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:49:49

76 views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:26:43
Heaven When I Held You Again
91 views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:04:15
Kate Winslet Titanic Rose1996 https://t.me/JournalistNetsanetGetachew
84 viewsedited  11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:19:08
ሩሲያ በዋና የጋዝ ማስተላለፊያ መስመሯ ወደ አውሮፓ የምትልከውን የጋዝ አቅርቦት ለሦስት ቀናት ማቋረጧን አስታወቀች፡፡
እንደ ጋዝፕሮም መረጃ የጋዝ አቅርቦቱ የተቋረጠው “በኖርድ ስትሪም1” የጋዝ ማስተላለፊያ መሥመር ላይ ጥገና በማስፈለጉ ነው፡፡
ሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚሄደውን የጋዝ አቅርቦት ያቋረጠችው ምዕራባውያን በጣሉባት ማዕቀብ ሀገራቱን ለመቅጣት በመፈለጓ ነው የሚለውን ውንጀላ ግን “ጋዝ ፕሮም” አጣጥሎታል፡፡
የጋዝ ማስተላለፊያ መሥመሩ ባሳለፍነው ሐምሌ ወርም እንዲሁ ለጥገና በሚል ለ10 ቀናት መዘጋቱ ይታወሳል፡፡
ከዚያ ወዲህ ከሙሉ ዐቅሙ 20 በመቶ ያኅሉን ብቻ በመጠቀም ለአውሮፓ ገበያ ጋዝ ሲያቀርብ እንደነበር አር ቲ ዘግቧል፡፡
የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ሩሲያ አሁን ላይ በ400 በመቶ የተወደደው የነዳጅ ዋጋ ይብሱኑ ለማናር የወሰደችው እርምጃ ነው በሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
”ኖርድ ስትሪም 1” በሴንት ፒተርስበርግ አቅራቢያ ከሚገኘው የሩሲያ የባሕር ዳርቻ ተነስቶ በባልቲክ ባሕር ስር እስከ ሰሜን ምሥራቅ ጀርመን የሚዘልቅ የ 1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ መሥመር ነው። https://t.me/JournalistNetsanetGetachew
118 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:21:45
በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው " - የቆቦ ነዋሪ

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉ ያልተረጋገጡ መረጃዎችና ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች መሬት ላይ ያለውን እና ቀጥተኛ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ የሆነውን ማህበረሰብ እየጎዳ ነው።

አንድ ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ ከቆቦ ደሴ ተፈናቅለው የገቡ የቆቦ ነዋሪ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚሰራጨው መረጃ መሬት ላይ ካለው ሀቅ እንደማይገናኝ ገልፀዋል።

" በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚታየው የፉክክር ጉዳይ ነው የሚመስለው " ያሉ ሲሆን ለአብነት ቆቦ ተለቀቀች ተብሎ የሚሰራጨው ሀሰት እንደሆነና የህወሓት ታጣቂዎች በከተማው እንዳሉ ይህን እዛው ካሉ ቤተሰቦቻቸው እንደተገለፀላቸው አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት ወቅትም የፉክክር እና የውድድር ነገር ነው ያለው በሰው ሀብት፣ በሰው ነፍስ፣ በሰው ንብረት ጨዋታ የተያዘ ነው የሚመስለው ሲሉ የማህበራዊ ሚዲያውን ሁኔታ ገልፀዋል።

እኚሁ የቆቦ ነዋሪ በ2 ጎን ፅንፍ ተይዞ እየተደረገ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ ጦርነት በጣም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው ፤ ለአብነት ቆቦ በመንግስት ኃይል ስር ገብታለች ተብሎ ከተነገረበት ሰዓት ጀምሮ ብዙ ተፈናቃይ ወገኖች እንመለስ የሚል የእግር ጉዞ ጀምሮ ነበር ብለዋል።

የማህበራዊ ሚዲያ ትክክለኛ መረጃ እንዳይገኝ እና ህዝቡ እራሱን እንዳያደራጅ እያደረገው ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
https://t.me/JournalistNetsanetGetachew
141 views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:44:26
#በፀጥታ_ስጋት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ባደረባቸው በስጋት ምክንያት ግቢያቸውን ለቀው የወጡ ተማሪዎችን በሚመለከት ውሳኔ አሳለፈ።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በ22/12/2014 ዓ.ም ባደረባቸው ስጋት ምክንያት የተነሳ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

በዚህ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1ኛ. የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ #በቀጣይ_ዓመት ጥሪ በሚደረግበት ጊዜ ይሆናል።

2ኛ. የክረምት መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ የተጀመረውን ትምህርትና ፈተና ለማጠናቀቅ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሻ ጊዜ መስከረም 03/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። መረጃው የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ነው https://t.me/EthiopianEducationalTelevision
148 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:30:25

250 views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:06:04

228 views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:01:18
የኢትዮጵያ መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለስልጣናት ሁለት ጊዜ ፊትለፊት ተገናኝተዉ ተነጋግረዋል ተባለ፡፡


የኢትዮጵያ መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ባለስልጣናት ሁለት ጊዜ ፊትለፊት ተገናኝተዉ መነጋገራቸዉን የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አስታዉቀዋል።

ዶ/ር ደብረ ፂዮን አዲሱ ዉጊያ ከመጀመሩ በፊት ባለፈዉ ማክሰኞ ለዓለም መሪዎች ባሰራጩት ደብዳቤ እንዳሉት፣ የመንግስትና የቡድናቸዉ ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቢል ባለስልጣናት በሚስጥር ግን ፊት ለፊት ተገናኝተዉ ተወያይተዋል።

የመንግስትና የሕወሓት መሪዎች በሚስጥር ተወያይተዋል የሚባለዉን ዘገባ ሁለቱም ወገኖች በተደጋጋሚ ሲያስተባብሉ ነበር።

ቢቢሲ የሕወሓቱን መሪ ደብዳቤ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ግን የተፋላሚ ኃይላት መሪዎች በሚስጥር ባደረጉት ዉይይት ዉጊያ ለማቆምና በትግራይ ላይ የተጣለዉን እገዳ ለማንሳት ተግባብተዋል።

ድርድሩ የተደረገበት ጊዜና ሥፍራ አልተጠቀሰም።
ይሁንና ደክተር ደብረፂዮን «በትግራይ ላይ ያንዣበበ» ያሉትን ጦርነት ለማስቀረት ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብም ሆነ የአፍሪቃ ሕብረት የወሰዱት ርምጃ የለም በማለት ወቅሰዋል።

ዘገባዉ የዶቸቬሌ ነዉ፡፡
https://t.me/JournalistNetsanetGetachew
203 viewsedited  04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ