Get Mystery Box with random crypto!

JOSIE TECH™💡

የቴሌግራም ቻናል አርማ josie_tech — JOSIE TECH™💡 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ josie_tech — JOSIE TECH™💡
የሰርጥ አድራሻ: @josie_tech
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.91K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ JOSIE TECH በሰላም መጡ 🙏
💫አስደናቂ የሆኑ የፈጠራ ውጤቶች፣
💫የቴክኖሎጂ ትምህርቶች፣
💫የተለያዩ አዳዲስ አፖች እና
💫የቴክኖሎጂ ዜናዎች እዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ
Creator:- @josie_AI
Group @josie_tech_group

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-09 19:01:02 በአንድሮይድ ስልካችሁ ላይ ያሉ የግል ፋይሎችን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩቦት ይፈልጋሉ?

በስማርት ስልኮች ላይ ፎቶ እና ቪዲዮዎችን እንዲሁም የተለያዩ የግል ፋይሎችን እናስቀምጥበታለን።
ይህን የግል ፋይል ስልካችን የሰጣናቸው ሰዎች እንዳያይታይብን ማድረግ የሚችልባቸው ዘዴ እንጠቁማችሁ

፨መቆለፊያ /
File locker/ የፋይል መቆለፊያ / File locker/ መተግበሪያ በስልካችን ላይ የያዝናቸው መረጃዎቻችን በሌች ሰዎች በቀላሉ እንዳያዩብን ከሚያደርጉ ዘዴዎች አንዱ ነው።ይህም መተግበሪያው ባለው የፋይል ማናጀር አማካኝነት የግል ፋይሎቻችንን፣ ፎቶግራፎች ወይም ቪዲዎች ያሉበትን ፎልደር በመምረጥ በይለፍ ቃል ወይም ፓዎርድ ለመቆለፍ የሚያስችል ነው።

ይህንን መተግበሪያ ከጎግልፕሌይ / Google play store/ ዳወንሎድ በማድረግ መጠቀም የምንችል ሲሆን፥ ተጥቃሚዎች ይህንን መተግበሪያ በሚጠቀሙበት ጊዜ ልብ ሊሉት ይገባል የተባለው ነገር የምንሰጠው የይለፍ ቃል ወይም ፓስዋርድ በቀላሉ የሚያዝ መሆን አለበት ተብሏል ምክንያቱ ደግሞ የይለፍ ቃሉን አንዴ ከረሳን ፋይሎቻችንን ከፍተን ለማየት የምንችልበት አማራጭ ባለመኖሩ ነው። የምስል መደበቂያ መተግበሪያ
/Hide pictures- keep safe vault/ይህ የምስል መደበቂያ / Hide pictures- keep safe vault/ መተግበሪያ በአንድሮይድ ስልኮቻችን ላይ ያሉን ፎቶግራፍ እና የተንቀሳቃሽ ምስሎች በሌሎች ሰዎች እንዳይታዩብን ለማድረግ የሚረዳን መተግበሪያ ነው። ይህንን መተግበሪያ ለመጠቀምም እንዳይታዩብን የምንፈልጋቸውን ምስሎች ከከፈትን በኋላ ኪፕ ሴፍ/‘keep safe’/ የሚለው ላይ ሼር በማድረግ ምስሎቹን ከሌሎች ሰዎች እይታ መሰወር እንችላለን።
ይህንን መተግበሪያ ስልካችን ላይ በማውረድም በስልኮቻችን ላይ ያሉንን ግላዊ ሚስጥሮች መጠበቅ እንችላለን። lፋይሎቻችን ስም በምንሰጥበት ወቅት ከፊትለፊቱ ነጥብ (.) ማስገባት ይህ መንገድ ቀላሉ እና ሌላ ተጨማሪ መተግበሪያ ሳያስፈልገን በስልካችን አንዲሮይድ ፋይል ማናጀር በመጠቀም ፋይሎቻችንን ሌሎች ሰዎች እንዳያዩብን የሚያደርግልን ነው። ይህንን ለመጠቀምም በስልካችን ላይ ሴቭ የምናደርገውን ፋይል ስም ከመስጠታችን በፊት ከፊት ለፊቱ ነጥብ (.) አስቀድመን በማስገባት ስሙን ጽፈን ሴቭ ማድረግ ነው።
በዚህ መንገድ ሴቭ ያደረግናቸው ፋይሎች በቀላሉ ፊት ለፊት ላይ ለሌሎች ሰዎች አይታዩም። እነዚህን ፋይሎች መልሰን በራሳችን ጊዜ ከፍተን ማየት ከፈለግንም ፋይል ማናጀር ውስጥ ከገባን በኋላ ሴቲንጉን በመክፈት ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የተደበቁ ፋይሎችን ለመክፈት የሚረዳንን
/show hidden files/ ከከፈትን በኋላ በሚመጣለን ስፍራ ላይ ነጥብን በማሰቀደም የሰጠነውን ስም አስገብተን በመጻፍ መመልከት እንችላለን
ethio cyber

   |  - @JOSIE_Tech - |  
884 viewsAbela (ጠጄ), 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 18:17:08
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው አመተ ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ አረፋ ብዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
775 viewsAbela (ጠጄ), 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:01:39
ጥንቃቄ አይለያችሁ !

የ " FIAS 777 " ጉዳይ ከተነሳ በኃላ በርካታ የቤተሰባችን አባላት ልክ እንደ " FIAS 777 " ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ አካላት መኖራቸውን እየጠቆሙ ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት ያለብንን የኢኮኖሚ ችግር ተገን አድርገው " በአጭር መንገድ ትርፋማ የሚሆኑበት የማለፋ ስራ " እያሉ በርካታ ወጣቶችን እየቀሰቀሱ ገንዘባቸውን ላፍ እያደረጉ ናቸው።

ውድ ቤተሰቦቻችን ተጠያቂ የምታደርጉት ሰው በሌለበት፣ ቢሮ ሆነ አድራሻ በሌላቸው ሰዎች ፣ ነገ ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን በማታውቁት ሂደት በአሰቸጋሪ ሁኔታ ደክማችሁ ለፍታችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ፣ ተበድራችሁ ያገኛችሁትን ገንዘብ ፣ ተማሪዎችም ከቤተሰብ የተቀበላችሁትን ገንዘብ ለቀማኞች እንዳታውሉት አደራ እንላለን።

ብዙሃንን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ በሚስጥር አይሰራምና ገንዘባችሁን ከሚያሳጣ ማንኛውም የአጭበርባሪዎች እንቅስቃሴ ራቁ።

ሌላው ደግሞ የስልክ ቀፎ፣ ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ... የመሳሳሉ እቃዎችን በርካሽ ከደቡብ አፍሪካ ፣ ከኬንያ በሞያሌ በኩፓ እናስመጣለን እያሉ ቅድመ ክፍያ እየተቀበሉ እብስ የሚሉ አሉና ተጠንቀቁ።

ሰዎችን ማታለያ መንገዶች አይነታቸውን እየቀያየሩ እየበዙ ነውና ህጋዊ ተጠያቂነት ያለባቸው ስራዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጉ።

ሁሌም ጥንቃቄ ማደረጋችሁን አትዘንጉ።


   |  - @JOSIE_Tech - |  
920 viewsAbela (ጠጄ), 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:00:38 ከሰሞኑን እንደተሰማዉ ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቢ ላሜ የዓለማችን ቁንጮ ቲክቶከር ሆነ
አሁን የቲክቶክን መንደር በተከታዮች ብዛት በበላይነት የሚመራው ትውልደ ሴኔጋላዊው ካቤ ላሜ ነው።

የ22 ዓመቱ ወጣት በቲክቶክ ላይ ቃል ሳያወጣ፣ በአካል እንቅስቃሴ ብቻ ትዝብቱን በማጋራት አሜሪካዊ ቲክቶከሮችን በልጦ የመተግበርያው ማማ ላይ ተቀምጧል።

ከዚህ ቀደም የአንደኝነቱ መንበር ተይዞ የነበረው በቻርሊ ዲ አሚሊዮ ነበር።

ላሜ በአሁን ሰዓት 143.8 ሚሊዮን ተከታዮች ሲኖሩት፣ ዲ አሚሊዮ ደግሞ 142.6 ሚሊዮን ተከታዮች በመያዝ ይከተላል።

በ2020 ኅዳር ላይ ዲ አሚሊዮ 100 ሚሊዮን ተከታዮችን በማስከተል የቲክቶክ መንደር አጋፋሪ ሆኖ ነበር።

ላሜ ወደ ቲክቶክ አምባ የተቀላቀለው በሚኖርባት ጣልያን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እግር ተወርች ተይዛ ማጣፍያው ባጠራት ወቅት ነበር።

በወቅቱ ዓለም ለኮሮናቫይረስ ወረርሽን እጇን ስትሰጥ ካቤ ከሥራው ተሰናበተ። እናም በሩን ዘግቶ ሞባይሉን አነሳ።

በተዘጋው የመኝታ ቤቱ ክፍል ውስጥ ቲክቶክ እጁን ዘርግቱ ተቀበለው።

ሰዎች ነገሮችን ሲያወሳስቡ ሲመለከት በቀላሉ እንዴት መከወን እንደሚቻል እጁን በመጠቆም ቃል ሳያወጣ በማሳየት ዝናን አጋበሰ።

ዛሬ የቲክቶክ መንደር ሰዎች ስሙን አንስተው የማይጠግቡት፣ የሠራው ሁሉ በአዕላፍ የሚታይለት፣ በዓለም አቀፉ ድግስ ላይ የሚጋበዝ ቱጃር ወጣት ነው።
ይህ የቲክቶክ የዓለም ፈርጥ እንደ ሌሎች ቢጤዎቹ በቲክቶክ ላይ ሲደንስ አይታይም። እንደውም ለዳንስ አካሉ እሺ ብሎ የሚታዘዝለት አይመስልም።

አይዘፍንም፤ ቃለ ተውኔት ጽፎ በመተወን የሌሎችን ቀልብ ለመሳብም አይጥርም።

የሌሎችን ድምጽና ትወና ለማስመሰል ደፋ ቀና ሲል አይታይም።

ዝም ብሎ የሰው ልጅን ውስብስብ ተግባራት ይተቻል፤ እንደ ዘበት።

በቲክቶክ ላይ የሚለጥፋቸው ቪዲዮዎች ቀላል እና አጭር ናቸው።

የእርሱ ትችቶች በንግግር የተደገፉ አይደሉም፤ በቀላል ድርጊት የታጀቡ አንጂ።

ውስብስብ በሆነ መንገድ ቀላል ነገርን የሚከውኑ ሰዎችን ቪዲዮ በማሳየት፣ እርሱ ያንኑ ተግባር ቀላልና ግልፅ በሆነ መልኩ ያሳየዋል።

ከዚያን እጁን በማወናጨፍ እና አንገቱን በመነቅነቅ ያበቃል።
ይህ በዓለም ላይ ዝነኛ የሆነው ቲክቶከር ማን ነው? ለምን ዝነኛ ሆነ?
ካቢ ላሜ በምዕራብ አፍሪካዋ አገር ሴነጋል ነው የተወለደው። አሁን ግን የሚኖረው ጣሊያን ነው።

የ22 ዓመቱ ወጣት ካቢ ቲክቶክን መጠቀም የጀመረው በመጋቢት ወር 2020 ነው፤ ኮሮናቫይረስ ዓለምን በተዋወቀበት ጊዜ እርሱ ቲክቶክን ተዋወቀ።

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ክፉኛ በደቆሰበት ወቅት እርሱም ከሚሠራበት ፋብሪካ ተሰናበተ። ካቢ በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቹ አመራ።

ሌላ ሥራ ይፈልጋል ተብሎ ሲጠበቅ እርሱ ግን በየቀኑ ቲክቶክ ላይ ቪዲዮዎችን መለጠፍ ጀመረ።

ታዲያ ያኔ የቲክቶክ አካውንቱ ላይ ፈገግ የሚያሰኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ሲያጋራ እንዲህ በአንድ ጊዜ ስሜ በመላው ዓለም ይናኛል፤ ተግባሬ ብዙዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሎ ያሰበ አይመስልም።

ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ የሚያተኩሩት እንዴት ሰዎች ያለምንም ተጨባጭ ምክንያት ነገሮችን እንደሚያወሳስቡ በማሳየት ነው።

እርሱ እንደሚለው በመላው ዓለም የሚገኙ ሰዎች የእርሱን ቪዲዮዎች የወደዱት ሳቅን በሚያጭረው የፊት ገጽታው የተነሳ ስለሚያስቃቸው ነው።

ሌላው ደግሞ የእርሱን ሐሳብ ለመረዳት ቋንቋ ማወቅ ወይንም መናገር ፈጽሞ አለመጠየቁ እንደሆነ ያስረዳል።

ካቢ የእግር ኳስ አድናቂ ሲሆን በቪዲዮዎቹ ላይ የስፖርት ክለብ ቲሸርቶችን ለብሶ ይታያል።

የጁቬንተስ ደጋፊ የሆነው ካቢ፣ ኤዲ መርፊ እና ዊል ስሚዝም ከሚያደንቃቸው የሆሊውድ ከዋክብት መካከል ናቸው።

ምንጭ፦ BBC Amaharic

   |  - @JOSIE_Tech - |  
880 viewsAbela (ጠጄ), 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:09:34
815 viewsAbela (ጠጄ), edited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:00:23
945 viewsAbela (ጠጄ), 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 19:01:53
#IBM

እአአ በ1980 የአለማችን የመጀመሪያውን Hard Drive አምራች የነበረው #IBM በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን 1GB Hard Drive የሚሸጠው በ40,000$ ነበር።

በተጨማሪም 550 ፓውንድ ይመዝንም ነበር (መለስተኛ ፍሪጅ በሉት )

ምስሉን #ብቻ ብናሳያችሁ ምንድነው ብላችሁ ትገምቱ ነበር?

   |  - @JOSIE_Tech - |  
1.0K viewsAbela (ጠጄ), 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ