Get Mystery Box with random crypto!

JOSIE TECH™💡

የቴሌግራም ቻናል አርማ josie_tech — JOSIE TECH™💡 J
የቴሌግራም ቻናል አርማ josie_tech — JOSIE TECH™💡
የሰርጥ አድራሻ: @josie_tech
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.91K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ JOSIE TECH በሰላም መጡ 🙏
💫አስደናቂ የሆኑ የፈጠራ ውጤቶች፣
💫የቴክኖሎጂ ትምህርቶች፣
💫የተለያዩ አዳዲስ አፖች እና
💫የቴክኖሎጂ ዜናዎች እዚህ ቻናል ላይ ያገኛሉ
Creator:- @josie_AI
Group @josie_tech_group

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 19:00:19 በብሉቱዝ በኩል ከሚመጡ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነቶችን እንዴት መከላከል እንችላለን?

ብሉቱዝ በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የምናደርጋቸውን የመረጃ ልውውጦች ያለ ውጫዊ መረጃ ማስተላላፊያ ቁስ ስልካችንን ከድምጽ፣ ከማፈላለጊያ እና ኤሌክትሮኒክስ ጋር በበይነ-መረብ ቁሶች አማካኝነት የሚያገኛኝ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ብሉቱዝ ምቾት የሚሰጥ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አመቺ ቴክኖሎጂ ቢሆንም ዋና ዋና የደህንነት ሥጋቶችንም ሊያመጣ ይችላል፡፡

ከዚህ በታች ለተንቀሳቃሽ ስልክዎ የደህንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ የብሉቱዝ ተጋላጭነቶችን እና የመጠበቂያ መንገዶች አቅርበንላችኋል፡፡

• አጠቃላይ የሶፍትዌር ተጋላጭነት መከላከል።

- ብዙዎቹ በብሉቱዝ መሣሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ሶፍትዌሮች ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ አይደሉም፡፡ በብሉቱዝ አማካኝነት አዲስ እና የማይታወቅ ደህንነት ተጋላጭነት በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን አንዲሁም በሌሎች መገልገያዎቻችን ላይ ሊያጋጥም ይችላል፡፡

- ከደህንነት ስጋት ነጻ የሆነ ሶፍትዌር የሌለ በመሆኑ ሁልጊዜም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

• በስውር ማዳመጥ መከላከል።

- የብሉቱዝ ምስጠራ (encryption) ወንጀለኞች መረጃዎችን እና የስልክ ጥሪዎችን እንዳያዳምጡ ለማድረግ ያስችላል ፡፡

- ስለዚህ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የብሉቱዝ መሣሪያዎች ለደህንነት ተጋላጭ የሆኑ ክፍተቶች ሊኖራቸው ስለሚችል ወቅታዊና የዘመኑ ብሉቱዝ ምርቶችን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

• የአገልግሎት ማቋረጥ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ።

- በአጥፊ ቫይረሶች ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችንን በመጉዳት ጥሪ እንዳንቀበል እና የባትሪያችን ኃይል በማዳከም የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች ሊያስተጓጉሉን ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ብሉቱዝ በማንጠቀምበት ወቅት ብሉቱዛችንን ልንዘጋ ይገባል፡፡

• ብሉቱዝ የሚያካልለው ስፋት ታሳቢ ማድረግ።

- ብሉቱዝ ዲዛይን ሲደረግ በግል አውታረ-መረብ ስፋት ነው፡፡ ይህም ማለት ብሉቱዝ ከመሣሪያዎቻችን ጥቂት የእግር እርምጃዎች ርቀት በኋላ ተደራሽ አይሆንም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ባለንበት እና ጥቃት ሊፈፅም በሚችል ማንኛውም አጥቂ አካል መካከል ያለንን ርቀት እርግጠኛ መሆን አንችልም፡፡ ምክንያቱም ጥቃት ፈጻሚዎች ክፍት ብሉቱዝ መኖሩን ከርቀት የሚያመለክቱ መተግበሪያዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም በማንጠቀምበት ጊዜ ብሉቱዛችንን ማጥፋት ተገቢ ነው፡፡

- ብሉቱዝ የሚጠቀሙ ጆሮ ማዳመጫዎች (earphones) ላይ ጥንቃቄ ማድረግ
በርካታ ብሉቱዝ የጆሮ ማዳመጫዎች አደገኛ የደህንነት ክፍተት ማስተናገጃ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አጥቂዎች ይህን ተጋላጭነት በመጠቀም ንግግሮቻችንን ሊያዳምጡ ይችላሉ፡፡

- በቫይረስ የተጠቃ መሣሪያ የሚያገኘውን መረጃ ለጥቃት ፈጻሚው ያስተላልፋል፡፡

- ይህ ለመከላከልም በቀላሉ የሚገመት የፋብሪካ ምርት ፒን ኮድን /PIN code/ ለመገመት አዳጋች በሆነ ኮድ መቀየር ጠቃሚ ነው፡፡


   |||  - @josie_Tech - |||  
846 viewsAbela (ጠጄ), 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 19:01:53 ድህረገፅ ዴቨሎፕመንት(WEBSITE DEVELOPMENT)

➲ ድረ ገጽ( WEBSITE) - የዌብ ፔጆች ስብስብ ሲሆን በአንድ ዶሜን ኔም(DOMAIN NAME) የሚጠሩና ተመሳሳይ ሰርቨር ላይ የተቀመጡ ናቸው::

➲ ዶሜን ኔም ለምሳሌ
WWW.GOOGLE.COM
WWW.FACEBOOK.COM

የድረ ገጽ አይነቶች(TYPES OF WEBSITE)

1.ስታቲክ (STATIC WEBSIRE)

- የማይቀያየር ኮንተንት ወይም ይዘት ያላቸው እንዲሁም ከHTML,CSS የተሰራ የዌብ ፔጆዎች ስብስብ ነው ሁሌም ቢሆን ተመሳሳይ ኮንተንት ያቀርባሉ ዳታ ቤዝ የላቸውም ማለትም መረጃ ከዳታቤዝ አይመጣም እንዲሁም ወደ ዳታቤዝ መረጃን አያስገባም ሰርች ማደርግ አንችልም፡፡

2.ዳይናሚክ ድረ ገጽ(DYNAMIC WEBSITE)

- ተለዋዋጭ መረጃዎችን የያዘ ከዳታ ቤዝ ጋር የተሳሰረ ማለትም መረጃዎችን ከዳታቤዝ የሚመጣ እንዲሁም ወደ ዳታ ቤዝ የሚልክ በሰርቨር ሳይድ የኮንፒተር ቋንቋ የተሰራ ሲሆን ለምሳሌ PHP,ASP.NET, Python, Ruby, C#, and NodeJS ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡

ስልዌብሳይት ይህን ካልን ስታቲክ ድረ ገጽ( (STATIC WEBSIRE) ለመስራት ምን ያሰፈልገናል ?

- ቴክስት ኢደተር እንደ ኖት ፓድ,እንዲሁም የሰራነውን የምናይበት ዌብ ብራውዘር ያስፈልገናል

- ስታቲክ (STATIC WEBSITE) ምሳሌ



JOSIE TECH


JOSIE TECH





አዲስ ኖትፓድ ከፍተን ሴቭ ስናደርግ ለምሳሌ TEST.HTML ሆኖም TEST ቦታ የፈለግነውን ስም መስጠት ይቻላል ግን

HTML ግዴታ ነው ፡፡ የኮድ ማብራራያ
ህግ 1
- HTML መክፈቻ ታግ
- ርዕስ የሚቀመጥበት ታግ መክፈቻ
- ርዕስ JOSIE TECH
- ርዕስ የሚቀመጥበት ታግ መዝግያ
- ሃተታ የዌብሳይቱ ዋና አካል መክፈቻ

JOSIE TECH


- ሃተታ የዌብሳይቱ ዋና አካል መዝግያ
- ውጤት JOSIE TECH

   |||  -
@josie_Tech - |||  
873 viewsAbela (ጠጄ), 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 19:00:08 የጠፋብዎትን የሞባይል ስልክ ፓስዎርድ ለመክፈት የሚጠቅም መንገድ ።


➲ 1. በቅድ
ሚያ ቀፎው ላይ ያሉ ሁሉም መረጃዎች የሚጠፉ መሆኑን መረዳት አለብዎት

➲ 2. መጀመሪያ ስልኮን ሙሉ በሙሉ ያጥፉት

➲ 3. ከዚያ የስልኮን የድምጽ መጨመሪያ ቁልፍ፣ የስልኮን
ማጥፊያ እና የመሰላል ቁልፍ ሶስቱንም ባንዴ ተጭነው
ለተወሰነ ጊዜ ይቆዩ

➲ 4. የተወሰኑ ስልኮች በድምፅ መጨመሪያ እና ስልክ
ማጥፊያ ቁልፎችን በመጫን ብቻ ይሰራሉ፡፡

➲ 5. የአንድሮይድ ምስሏ አልያም የስልኮ ብራንድ ስም
ሲመጣ ሁሉንም ቁልፎች ይልቀቁና በድምጽ መቀነሻው
ቁልፍ ወደታች ያሉትን አማራጮች (wip data/factory
reset) ይምረጡ፡፡

➲ 6. ከዚያ ስምንተኛ ተራ ቁጥር ላይ ያለችውን አማራጭ
ይጫኑ (yes delete all user data)

➲ 7. ይህን እንዳደረጉ ስልኮን “reboot” በሚለው
አማራጭ አጥፍተው ያስነሱ፡፡

➲ 8. የስልክዎን ፓስወርድ በሚገባ
አጥፍተዋል ማለት ነው፡፡ next የሚለውን በመንካት መከተል ነው። wifi ከጠየቀ ኢንተርኔት ጋር ማገናኘትና email በመሙላት መጨረስ።
አሁን ስልክዎን ከፍተዉ እንደፈለጉ መጠቀም ይችላሉ::

   |||
  - @josie_Tech - |||  
901 viewsAbela (ጠጄ), 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:08:46
463 viewsAbela (ጠጄ), 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:01:54 ላፕቶፓችን ያለኛ ፍቃድ ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ማድረግ እንዴት እንደ ሚቻል ላሳያችሁ።

ፍላሽ ዲሰክ ፋይሎችን የምናስቀምጥበትና በቀላሉ ይዘነው የምንቀሳቀሰውማሽን ነው፡፡ በስራ ምክንያትም ይሁን በሌላ ፋይሎችን ላማስተላለፍና ኮፒ ለማድረግ ሰዎች የሚጠቀሙበት ፍላሽ ዲሰኮች ላፕቶፓችን ላይ እንሰካል፡፡

ላፕቶፓችን ላይ ያገኘነውን ፍላሽ ዲሰክ የምንሰካ ከሆነ ደሞ ላፕቶፓችን አደጋ ውስጥ ይገባል፡፡
ምክንያቱም ፍለሽ ዲሰክ ፋይሎችን ብቻ ሳይሆን ቫይረሶችንም ስለሚያስቀምጥ ያገኘነውን ፍላሽ ላፕቶፓችን ላይ የምንሰካ ከሆነ በፍላሽ ዲሰኮች አማካኝነት ቫይረሶች ወደ ኮፒውተራችን በመግባት ላፕቶፓችን ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላል፡፡

ከኛ ፍቃድም ውጪ ሳናውቀው አንድ ሰው ተደብቆ ላፕቶፓችን ላይ ፍለሽ ዲሰክ በመሰካት ላፕቶፓችንን ክጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ስለዚህ በተለይ ያለኛ ፍቃድና እውቀት ላፕቶፓችን ፍላሽ ዲሰክ እንዳይቀበል ለማድረግ የሚከተሉትን ስቴፖች መከተል ነው፡፡

1ኛ፡-መጀመሪያ Start በተንን ክሊክ እናደርግና gpedit.msc ብለን እንፅፍና ኢንተር እንጫናል፣

2ኘ፡- የተለያዩ አማራጮች የያዘ ሊስት ይመጣል፤ ሊስቱ ውስጥ “Local Group Policy Editor” የሚለውን ምረጡ፣

3ኛ፡-ከዚያ የሚከተለውን መንግድ ተከተሉ ፤ computer configuration>administrative templates>system>Removable storage access

4ኛ፡-አሁን በቀኝ በኩል ከሚመጡ አማራጮች ውስጥ “All Removable Storage Classes: Deny all access” የሚለውን ክሊክ ማድረግ፣

5ኛ፡- “Enable” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

አለቀ፡፡ ካሁን በኋላ ማንም ሰው ፍላሽ ዲስኩን ላፕቶፓችሁ ላይ መሰካት አይችልም፡፡

ምናልባት ይህንን የከለከላችሁትን አክሰስ መመለስ ስትፈልግ ከላይ ከ1 እስከ 4 ስቴፖችን እንዳሉ ተከተሉ እና፣

5ኛ፡- “Not Configure” የሚል አለ እሱን መምረጥ፣

6ኛ፡- “Apply”> “Ok” ሁለቱንም ተራ በተራ ክሊክ ማድረግ፡፡

   |  - @JOSIE_Tech - |  
739 viewsAbela (ጠጄ), 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:00:17 "ልጄ አሁን 4 ዓመቱ ነው ቀኑን ሙሉ ቴሌቭዥን እና ሞባይል ላይ ነው የሚውለው። አፉንም አልፈታም የተወሰኑ ቃላቶችን ብቻ ነው የሚናገረው። መፍትሄው ምንድነው?"

አሁን አሁን በጣም ብዙ ህፃናት በሞባይል እና በቴሌቭዠን ላይ የሚያሳልፉት ሰአት በጣም እየጨመረ ነው በተቃራኒው ደሞ የቋንቋ፣ የንግግር እና የትምህርት ብቃታቸው በእጅጉ እየቀነሰ እየመጣ ነው።

በሚገርም ሁኔታ ስልኮቻችን ላይ ያሉትን ነገሮች ከኛ ይልቅ ልጆቻችን አብጠርጥረው ያቃሉ ሆኖም ሁሉም ላይጠቅማቸው ይችላል።

► አንድ አሜሪካ ዉስጥ የተጠና ጥናት እንደሚጠቁመው ህፃናት በሞባይል እና በቴሌቭዠን ላይ የሚያሳልፉት ሰአት በ 30 ደቂቃ በጨመረ ቁጥር የቋንቋ እና የንግግር ብቃታቸው በ49% (በግማሽ) ይቀንሳል።

እድሜያቸው ከ 1 አመት በታች ያሉ ህፃናት በቀን ከ 1 ሰአት በላይ TV የሚያዩ ከሆነ የቋንቋ እና የንግግር እክሎች በ 6 እጥፍ ሊገኝባቸው ይችላል።

ህፃናት ረጅም ሰዓት ቴሌቭዠን እና ሞባይል (prolonged screen time) ሲኖራቸው ምን ምን አይነት ጉዳት ሊያመጣ ይችላል?

- የጨረር አይን ጉዳት (corneal dryness, macular degeneration etc...)
- የቋንቋ እና የንግግር መዘግየት (speech and language delay)
- አላስፈላጊ ባህሪዎች (ከፊልም/ ቪዲዮ ላይ...)
- ከሰዎች ወይም ከሌሎች ልጆች ጋር ለመግባባት መቸገረ (Poor social and emotional development)
- ስሜትን እና ራስን ለመቆጣጠር መቸገር (poor self regulation)
- የእንቅልፍ ሰአት መዛባት
- አንዳንድ ህፃናት ዝቅተኛ የትምህርት አቀባበል
- ያለልክ መብላት እና ሃይለኛ ውፍረት ወይም ምግብ ያለመብላት እና መክሳት።

ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?

- በቋሚነት የልጆች ስክሪን ጊዜ ወይም የቲቪ መመልከቻ ገደቦች/ ሕጎችን ማውጣት
- ወላጆች አርአያ መሆን አለባችሁ (ልጆች ፊት ረጅም ሰአት ስልክ አለመጠቀም)
- የሰውነት እንቅስቃሴ የሚጠይቁ ጨዋታዎችን ግቢ ዉስጥ ከወላጆች ጋር መጫወት
- መፅሐፍ አብሮ ማንበብ ወይም ስእል መሳል
- የአይምሮ እድገት የሚጨምሩ የቤት ዉስጥ መጫወቻዎችን መስጠት እና አብሮ መጫወት።

ገደቦች የሚከተሉት ናቸው፦

- እድሜያቸው ከ 2 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ምንም አይነት screen ያለውን ነገር መጠቀም የለባቸውም።

- እድሜያቸው ከ 2-5 አመት ለሆኑ ህፃናት በ ቀን ከ1 ሰአት በላይ መጠቀም የለባቸውም።

እነዚህ መመሪያዎች በዓለም ዙሪያ የ አለም የጤና ድርጅት (WHO) እና የአሜሪካ የህፃናት ሕክምና አካዳሚ (AAP) የወጡ ገደቦች ናቸው።
ethio cyber

   |  - @JOSIE_Tech - |  
722 viewsAbela (ጠጄ), 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:55:36
እንዴት?
598 views𝐉𝐨𝐬𝐢𝐞_𝐀𝐈, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:43:57
Elon Musk #ትዊተርን ለመግዛት የነበረውን ስምምነት አፈረሰ።

ይህም የሆነበትን ምክንያት ሲጠየቅ ትዊተር ያሉትን Spam Users (ፌክ አካውንቶችን) ብዛት በትክክል ባለማሳወቁና በሌሎችም ምክንያቶች ነው ብሏል።

ትዊተርም በበኩሉ ይህን ጉዳይ በህግ እንደሚያየው አሳውቋል።

የ YouTube ቻናሌን #Subscribe በማድረግ ገንዘብ #መስረቅ ትችላላችሁ

https://youtube.com/channel/UCgn5-VyBQAHDHFHGhSdwbhQ?sub_confirmation=1

   |  - @Abela_Tech - |  
710 viewsAbela (ጠጄ), 10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 16:04:18
803 viewsAbela (ጠጄ), 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 08:39:06
ይቺን ስልክ ላስተዋውቃችሁ

ZANCO TINY T1 ትሰኛለች። በአለማችን ትንሿ ስልክ ናት። ነገር ግን ሚሴጅ ትላካለች፣ ትቀበላለት , ስልክ ትደውላለች እንዲሁም ጌምም አላት

@JOSIE_TECH ....የእናንተው
859 views𝐉𝐨𝐬𝐢𝐞_𝐀𝐈, 05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ