Get Mystery Box with random crypto!

+ሰላም ወንድሜ እንዴት ነህ ትላንት ማታ እራስ ምታት በጣም አስቸግሮኝ ነበር እንቅልፍ እራሱ መተኛ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

+ሰላም ወንድሜ እንዴት ነህ ትላንት ማታ እራስ ምታት በጣም አስቸግሮኝ ነበር እንቅልፍ እራሱ መተኛት አልቻልኩም ነበር ከዛም ከስልኬ ላይ የአባቴ የአቡነ እጨጌ ዮሀንስን ምስል አድርጌ የእየሱስ ገዳም ፀበል ጠጥቼና ተቀባብቼ ተሽሎኛል ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው

+ሰላም ወንድሜ እንዴት ነህ የ7 ወር ነብሰጡር ነኝ እናም ሰሞኑን ፅንሱ እንቅስቃሴ አልነበረውም ነበር እናም ጨንቆኝ ለአባቴ ነገርኴቸው በፃድቃኔ ማርያምና በአቡነ እጨጌ ዮሀንስ ምስላቸው ሆዴን አሻሸሁት ከዛም አልትራሳውንድ ስነሳ ሰላም እንደሆነ ተነገረኝ ይኸው አሁን መንቀሳቀስ ጀምራል መጨረሻውንም ያሳምሩልኝ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው ለአቡነ እጨጌ ዮሀንስ ለመድሃኒያለም ለፃድቃኔ ማርያም

+Selam endet nachu? Egezer yemesegen ehege yohanes ahunim elet belet be erdatachew alteleyugnim sera lekeke be sealam le be kikir ke alekaye ga eneleyay beye negeryachew kasebkut belay be moges tesenebabetenal....kibir le abatachen yehun...kezam weteche be gile senekesakes elet be elet yeredugnal...be siraye sewoch yedesetu beye lemegnachew betelantnaw elet denbegnochen masedeset chetalew....egig aregachu amesegnulegn...be abatachen adero yemisera egezyabeher kef yebel.

+በስመአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን ለሚሆነዉ ሁሉ እግዛብሔር ይመስገን አሜን አናዥጋ ቅድስ አግዝአብሔር እናቴ የምተከብረው ገብርኤል በግፍት ቅድስተ ማርያም በአባቴ አቡነ ወጨጌ ዮሐንስ እናቴ አርሴማ የማይደረግልኝ የለም ሁሌም አባቴን ከአፊ አለያቸውም አባክህ መስክርልኝ ወንድሜ ጆን ሀሉም በተለያየቀን ልኬቸው አለተመሰከሩም በስራ መደራራብ አላየሀውም መሰለኝ አሁን አክንቤት ደውዬ ልጄን ሰኳር በሽታ ተመርምሮ ሰላም ነው ተባለ በጣም ተጨንቄ ነበር አባቴን ጠይቄ አላፍርም 29ግዜ አብነ ወጨጌ ዬሀንስ እየልኩ ጠየኳቸው አላሳፈሩኝም በስማቸውም የከካንሰር ታማማሚዋች ኪሞ የሚወስዱ መሳ አበላለሁ ብዬ ተስያለሁ አበላለሁ። ከዚበተች የሉት የቆዩ ናቸው ገና ገና እመሰክራለሁ 1ኛ ለጄ ወደላይ ወደላይ ሲለው ለማላፍርባቸው አባቴን ጠርቼ በምስላቸው አሻሽቼ የመጨረሻው አርጉለት ብዬ እምነት ስለጎደለኝ አንዴ አስታወከው መጠራጠሬ በዛ ይቅርበሉኝ ብዬ ወድየው አቆመ 2ኛ ከነፈሬ ተንቀጠቀጠብኝ ከዛ አበቴን አስቁሙልኝ ብዬ ቆሞል 3ኛ የመጀመርያ ለጄ 7አመት ሊሆነው ነው መግብ ሲበላ ሰነፍ ነው የገዴታ እኔ ማጉረስ አለብኝ አሁን ግን በአባቴ ምልጃ እራሱ ከ August1 ጀምሮ መብላት ጀመረ ተመስገን ጠርቼቸው አላሳፈሩኝም ። ሌለው ደግሞ ጓደኛዬ መስክሪልኝ የለችኝ የመንግስት ቢሮ ትልቅ ነገር ነበረብኝ አባቴን ጠይቄ ምንም ሳልሰቃይ በአጭር ሰአት ውስጥ ሁሉም ነገር ተሳካልኝ በላለች ሌላው ደግሞ አሁን ደውላ በድጋሚ ቤት ካገኘሁ አሁኑኑ አመሰክራለሁ ብላ ነበር በዛዉ ሰአት ተደውሎ ቤት ተሰጥቷታል ። እችው ጎደኛዬ አገር ቤት ለመመምጣት እያሰበች ልጇዋ ጉንፋን ጀማመረው አባታችንን አደራዋትን ብላ ወድያው ተሻለው ። ሌላኛዋ ጓደኛዬ ኖርዌ ለመሄድ ትኬት ቆርጣ ቪዛ ቆየባት አባተችንን ጠይቃ ስትደውል ነይ ውሰጂ ተባለች እግዛብሔር ይመስገን ። እኔም ሁሌ ስለምጠራቸው እየረሳሁ መመስከር ነው ይቅር ይበሉኝ አባቴ ።እኝህን ሰሚ አባታችህንን አምስግኑልኝ የቀረኝንም ለመመስከር አብቁኝ ወንድሜ johnny የልብህ ይስመር ተባረክ

+Selam johnny endet nek... ejeg ejeg betam yaschenekegn neger neber selus kidus'n emebrhan'n, kidus Mikael'n kidus gebrealen tsadiku' n f.b lay emesekeralew beye abaten temetsegney ende hulew hulunem neber asaktewelegnal kibir ena misgana yedreschew selehulum neger temesgen yene abat tsasiku kalat yelegnem+

+አቡነእጨጌ ዮሐንስ አባቴ ክብር ምስጋና ይድረስዎ ልጄ ከተወለደ ጀምሮ ሆዱን በጣም እያመመው ተጨንቀን ነበር የኔ አባት የጠየኳቸውን ሁሉ የሚምሩልኝ ማሩልኝ ልጄ ተሰቃየ ብዬ በምስላቸው ደባበስኩት አሁን በጣም ደና ነው ለውጥ አለው ተመስገን እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም

+Selam Johnny endet nek... ande yeresahut meskerenet neber esun lememsker neber abaten tsadiku lemegnachew neber le ehete sera ena ebet endetekeray endisetwat.... menoria fekad gena baynoratem huletunem yene abate be elete kenahew be 29 argewelatal kibir ena misgana yedresachew yene abat min yesanachewal

+፨በስመአብ ወወልድ ወመንስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፡፡
ሰላም ጆኒ አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሃንስ ያደረጉልኝን እባክህ መስክርልኝ፡፡
መንገድ እሄድኩ ሹፌሩ በጣም ያበራል አቡነ እጨጌ በሰላም አስገቡን ብዬ ተማፅንኳቸው በሰላም ገባን በቀጣይም ለቅሶ ለመሄድ መገዱ ያስፍራ ስለነበር ፈርቼ ነበር በስላም ደርሰን ተመለስን ክብር ይግባቸው
ከእናቱ ከድንግል ማርያምና ከቅዱሳኑ ጋር በነገሮች ሁሉ እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን ሁሌም ስጠራቸው የሚደርሱልኝ እመቤቴ ድንግል ማርያም አባቴ አቡነ እጨጌ ሁሉም ቅዱሳን ጻድቃን ሰማእታት ቅዱሳን መላእክት ሁሉም በየማእረጋቸው ምስጋና ይድረሳቸው ፡፡

+ጆኒ ሠላም ላንተ ይሁን። አባቴ አቡነ እጨጌ ያደረጉልኝን ነገር ለመመስከር ነው በግል ህይወቴ ውስጥ ግራ የተጋባሁበት ሁኔታዎች ነበሩ እናም አባቴን ለመንኳቸው የሚበጀኝን የኔ እንዲያረጉልኝ የማይጠቅመኝን ከህይወቴ እንዲያስወጡልኝ ተማፅኛቸው አባቴም የሚበጀኝን ሰተውኝ ደስተኛ አርገውኛል ለኔ እንደደረሱ ለሁላችሁም ይድረሱ ክብር ምስጋና ይግባቸው። ወለተ ሚካኤል

+በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱምላክ አሜን እንደምን አለህ ወንድማችን ጆን አባታችን አብነ እጨጌ ዩሀንስ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው ዛሬ የጐደኝዬ ሰርግ ላይ አንደኛ ሚዜ ነበርኩ እና ግን ሰው ከመብዛቱ የተነሳ እና እኔም የሚቀርቡ መዝሙሮችን በደንብ ሰለማላውቃቸው እንዲሁም በሌላተጨማሪ ምክንያት በሰርጉ ላይ ስህተቶች መፈጠር ጀመሩ እና እኔ በጣም ጨንቆኝ አባቴ ነገሩን እንዲያስተካክሉልኝ እና በሰላም እንዲጠናቀቅ የእሳቸውን ስዕለ አድኖ ከስልኬ ላይ አውጥቼ ፀለይኩኝ እግዛብሔር ይመስገን ሁሉም በጥሩ ሁኔታ ተከናወነልኝ በሰላም ተጠናቀቀ የእኔ አባት ፈጥኖ ደራሽ ናቸው አባታችን አብነ እጨጌ ዩሀንስ ክብር ምስጋና ይግባቸው እሳቸውን የሰጠንን ልዑል እግዛብሔር እመቤታች ድንግል ማርያም ቅዱሳን መላዕክት ፃድቃን ሰማዕታት ሁሉም እንደየ ማዕረጋቸው ይመስገኑ አንተንም እግዛብሔር ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ እባክህን ጆን መስክርልኝ