Get Mystery Box with random crypto!

፨ሰላም ዩሐንሰ እንዴት አመሸክ * ማታ ሆዴን በጣም አሞኝ ነበር በተነሳው ቁጥር ሰዉ እየረበሽኩ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ገዳም ሚዲያ ፨ ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ የገዳሙ ሶሻል ሚዲያ Johnny aleme

፨ሰላም ዩሐንሰ እንዴት አመሸክ
* ማታ ሆዴን በጣም አሞኝ ነበር በተነሳው ቁጥር ሰዉ እየረበሽኩ ነበር ፃድቁን እስከጠዋት ሰዉ አረብሽ ብያቸው በሰላም ተኝቻለሁ ጨርሰዉ እንዲምሩኝ በፀሎታችሁ አስቡኝ የሰጡኝን ፍሬ ይጠብቁልኝ ለቤታቸው ያብቁን
*ልጄን ድርቀት አስቸግሮት የፃድቁን መልዕካ ደባብሼው ደህና ሆኖ ነበር ባለመመስከሬ ድጋሚ ድርቀት ይዞታል ፃድቁ ይቅር ይበሉኝ
* ልጄ ክትባት ነበረዉ የፃድቁን መልዕካ ደባብሼው ደህና ነው አዳሩን በሰላም ያሳድሩልኝ
* ልጄ ድርቀት ይዞት የሆነ መድዓኒት ታዞለት ፃድቁ አልሰጠው እርሶ ዳብሱት ብዬ ገላግለውታል ማታም በጣም እያለቀሰ አስቸግሮ የፃድቁን ፀበል በክዳን አፉ ላይ ጠብ አድርጌ የሰላም እንቅልፍ ተኝቷል በየቀኑ ሲያስቸግር አፍ ላይ ፀበል ጠብ አደርግለታለው ፃድቁ ሰላም ያድርጉት ለኔም በእንጥልጥል የቀረ የትምህርት ውጤት አለ ፃድቁ እንዲረዱኝ በፀሎታችሁ አስቡኝ ሙሉ የትምህርት ዶክመንቴ ጠፍቶብኛል ፃድቁ ያስገኙልኝ በዚህ ዓመት ትምህርት መማር አስቤሃለው እንዲሳካልኝ ጸልዩልኝ በየደቂቃው ሰለምጠራቸው የረሳውት ብዙ ይኖራል ፃድቁ ይቅር ይበሉኝ ክብር ለፃድቁ ክብር ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ክብር ለአናዢጋው እግዚአብሔር አብ ክብር ለግፍት ማርያም ክብር ለሁሉም ቅዱሳን እንደየማዕረጋቸዉ የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን እመአምላክ ሰሟ የተመሰገነ ይሁን ፃድቁን አመሰግኑልኝ ያንተም የአገልግሎት ዘመንክ የተባረከ ይሁን አሜን

፨ሰሜንሸዋ መንዝ መዘዞ(ጠገሮ)+++(አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+++
መነሻ፦ጥቅምት12 ቅዳሜ
መመለሻ፦ጥቅምት13 እሁድ በጻድቁ 500ዓመት በያዙት በመስቀላቸው በመቋሚያቸው ተባርከን መመለስ።

ለበለጠ መረጃ፦
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969