Get Mystery Box with random crypto!

ጉዞ ንግስ /መስከረም 20/21 ግፍት ቅድስት ማርያም እና ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል / ንግስ ጉዞ ~መስ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ Johnny aleme

ጉዞ ንግስ /መስከረም 20/21 ግፍት ቅድስት ማርያም እና ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል /
ንግስ ጉዞ ~መስከም 20/21
መነሻ~መስከረም 20 ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል ገብተን ግፍት ቅድስት ማርያም አድረን በ21 አንግሰን መመለስ።

ጉዞ ይዘጋጃል።
1/0911190212
2/0911481388
3/0979986969

++++++ መንዝ በ14ክ/ዘመን የተመሰረተው ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም!
++ይህ ገዳም በዋሻ ውስጥ ሲሆን በዋሻው ውስጥም አፅመቅዱሳን የሚገኝበት ገዳም ነው።

++ይህ ገዳም በቅድስቱና በመቅደሱ ውስጥ የሚፈስ ፀበል ሲኖረው ፀበሉ የሚፈሰው እንደጠብታ ከዋሻው ውስጥ ሲሆን ፀበሉም ጠብታም እንደ እንስራ ያለ ማጠራቀሚያ ጋን ውስጥ ይጠራቀማል የሚገርመው ግን ጋኑ ሲሞላ ወደምድር አይፈስም። ጋኑ ቢሞላ ከጋኑ አይፈስም አይጎልም።

++የቅዱስ ሚካኤል ፀበልም ከድንጋይ ውስጥ የሚወጣ ፀበሉ የሚመጣበት ወይም ፀበሉ የሚፈልቅበት ቦታ አይታወቅም

+++እንዲሁም በዚህ ገዳም የቅድስት አርሴማ ፀበል ሲኖር ብዙ አይነስውራን አብርቷል

ይህን ገዳም የሰው ልጅ ባየው ብየ የተመኝሁት ቦታ ነው። ገዳሙን ሲረግጡ በሐሴት በደስታ የምንሞላበት ገዳም ነው።

++ይህ ገዳም እርዳታ ያስፈልገዋል

-ገዳሙ ግርግዳው በአፈር እና በድንጋይ የተሰራ ነው እንዲሁም ወለሉ አፈር ነው።

-መቅደሱም ቅድስቱም በድንጋይና በአፈር ውስጡም ወለሉ አፈር የተስራ ነው።

-በዋሻው አናት ላይ ፀበል እየፈሰሰ ዋሻው መግቢያን እየፈሰሰበት እየሸረሸረው ነው መግቢያው በድንጋይና በጭቃ ስለተሰራ ነው።

-ካህናቱ ደሞዝ የላቸውም ደሞዝ እንዲያገኙ እናድርግ

ስለዚህ ሁላችንም እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ ቤቱን እንስራ እላለሁ።
የገዳሙ ሂሳብ ቁጥር/አካውንት/

Account no~1000338199965
Account name ~ጠምሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን
SWIFT CODE-CBETETAA
Commercial Bank of Ethiopia /ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/

፩/ሲሚንቶ 400ኩንታል
፪/አሸዋ 4ቢያጆ
፫/ጠጠር 3ቢያጆ
፬/ቀለም 40ጋሎን

፭/ፊሮ ብረት
-ባለ 12 ብዛት 400
-ባለ 14 ብዛት 234
-ባለ 10 ብዛት 387
-ባለ 8 ብዛት 240


ለበለጠ መረጃ፦
_0911190212
_0911481388
_0979986969
_0901002929

ይህንን ገዳም ለመርገጠ ያብቃችሁ በረከቱ ይደርባችሁ። ቅዱስ ሚካኤል በያላችሁበት ጤናችሁን ይስጧችሁ!ይጠቃችሁ!ሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ፍቅር አንድነትን ይስጠን! አሜን!

ቦታው~ መንዝናይፋት መዘዞ ከመዘዞ ከተማ 10ኪሜ እንደተጓዝ የ25ደቂቃ የእግር መንገድ ነው።

++++++++/ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ/
¶¶¶ጉዞ መስከረም 28 ተኪዶ አድረን
በ29 በአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ 500ዓመት የያዙት መስቀልና መቋሚያ ተባርከን ተጠምቀን ተባርከን መመለስ።

ለበለጠ መረጃ የገዳሙ ኮሚቴ~
ሀ/0911190212
ለ/0911481388
ሐ/0979986969
መ/0901002929

++ ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ወራዊ በዓል!
++++ ወር በገባ 29
++++ልደታችሁ ህዳር 29
++++እረፍታችሁ ሐምሌ 29
++++ፍልሰት አጽማቸው መጋቢት 18
ሐገራችን ኢትዮጵያ ሰላም ፍቅር አንድነትን ይሰጡን ።አሜን!

አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ምስክርነት እና ጉዞ ለመከታተል Share like like like

+++Fb Page~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny
aleme
https://www.facebook.com/profile.php?id=100044612041431

+++Telgeram~አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ+Johnny aleme +251911190212
https://t.me/JOHNNYALEME

+++Youtube-አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ +Johnny aleme

+++Fb~Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)
https://www.facebook.com/johnny.aleme.5

+++Instagram~Johnny aleme
https://www.instagram.com/p/CTIw18KoGAM/?utm_medium=copy_

[ቦታው] ፦ከአ/አ ሰሜን ሸዋ ጣርማበር 180ኪሜ እንደደረስን ወደ ግራ ጻድቃኔ ማርያም ሲሆን ፤ቀጥታ አስፓልቱን ወደ ደሴ የሚወስደውን ትተን፤ ወደ ቀኝ ወደ መንዝ መንገድ 15ኪሜ /መዘዞ ከተማ/ ወይም ወደ ዘብር ገብርኤል አርባሐራ መድሃኒዓለም መንገድ ላይ መዘዞ ከተማ 195ኪሜ ከመዘዞ ከተማ እንደደረስን የ1ሰዓት የእግር መንገድ ስንመለስ 2ሰዓት የእግር መንገድ ጠገሮ አቡነ
እጨጌ ዮሐንስ ዘጸገሮ ገዳም ያስኪዳል።በረከታቸው የደርባችሁ!ለደጃቸው ያብቃችሁ!አሜን!