Get Mystery Box with random crypto!

++/ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን 'አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠ | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ ABUNE ECHUGE YOHANNES ZTGRO GEDAM Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)

++/ምስክርነት /_++++ሰሜን ሸዋ መንዝናይፋት መዘዞ ምዕራፈ ቅዱሳን "አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ" ገዳም!
~7/11/2014 ዛሬ ለኔ የተደረገልኝ ድንቅ በጣም ያስጨነቀኝ የህክምና ውጤት ነበረኝ ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ ከቤቴ ስወጣ ለአባቴ አቡነ እጨጌ ዮሃንስ ነግሬአቸው ገድላቸውን በቦርሳየ ይዤ ወደ ህክምና ቦታ ሄድኩ ውጤቱን ማመን አልቻልኩም ደስታየ ወደር አጣ ክብር ምስጋና ለስላሶች ለድንግል ማርያም ለአቡነ እጨጌ ዮሃንስ እኔን ሀጢያተኛዋን እንደሀጢያቴ ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ተመስገንንንንን

~እንዴት ነህ ጆኒ በድጋሚ ምስክርነት ለመስጠት ነበር ባለፈው አይኔን አሞኝ በፃድቁ ምልጃ ለውጥ እንዳለ መስክሬ ነበር ዛሬ ደግሞ ድጋሚ ምርመራ አድርጌ በደንብ እንደዳነ እና የወሰዱት ናሙና ነፃ እንደሆነ ነግረውኛል ፃድቁን ለምኜ አፍሬ አላውቅም ክብር ምስጋና ይድረሳቸው ፃድቁን የሰጠን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው ሁልግዜ እምባዬን እሚያብስ የወንቅሸት ቅዱስ ገብርኤል የተመሰገነ ይሁን ቅዱስ ሚካኤ ምስጋና ይግባው ቃጥላ ማርያም ምስጋና ይድረሳት ቅዱስ ጊዮርጊስ ተክልዬ እባታችን በለተቀናቸው ታሪኬን የቀየሩ ክብር ምስጋና ይድረሳቸው እድሜ ከጤና ያድልልኝ ወንድሜ

~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። ሰላም ዩሐንስ እንዴት ነህ ምስክርነት ለመስጠት ነው አባቴ ለኔ ፈጥኖ ደራሼ ናቸው በህይወቴ በየቀኑ እጠራቸዋለሁ ልመናዬን ይሰማሉ ከብዙ መከራ አድነውኛል። እግዚአብሔር ይመስገን
1 የተጣሎ ቤተሰቦቼን አስታርቁልኝ ብዬ አስታርቀውልኛል
2,እናቴ እጆን አሟት ማሩልኝ ብዬ ጥሩ ለውጥ አለው።
3,ንስሐ እንድገባ እርዱኝ ብየ ፈጥነዉ ለንስሃ አብቅተውኛል
4,አባቴን ለደጆት አብቁኝ ብዬ ለምኛቸው ለደጃቸው አብቅተውኛል አሁንም የጠየኳቸውን ጎዶሎየን ሞልተው ስለቴን ሰምተው ለምስክርነት ያብቁኝ። አሜን

~በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አአዱ አሜን ።
በጣም ተጨንቄአለሁ ብዙ የማልናገረው እመም አለኝ አባቴ ያውቃሉ አሁን ፀበላቸውን እያጠጣው ነው አሁን ተሽሎኛል በምዕረቱ እስከ መጨረሻው ይኘሻለኛ አምናለው አባ አብነ እጬገ ዮሐንስ ዘጸገሮ ጨርሰው ይመረኝ በፀሎቱ ሀገራችንን ሰላም በረከት ያድርጉል አሜን አሜን አሜን ።

~ሰላም ወንድሜ ጆኒ ፈጣሪ በፀጋው ይጠብቅህ ባለፈውም መስክሬ ነበር ወንድሜ ታሞብኝ በጣም ተጨንቄ ነበር ለአባቴ ለእጨጌ ዬሀንስ ነግሬያቸው በምህረት ዳብሰውልኛል አሁንም ጨርሰው እንዲምሩልኝ ፀልዬልኝ ስለቴን አስገባለሁ አባቴ አሁንም ብዙ ነገር ነግሬያቸዋለሁ እንደሚፈቱልኝ አምናለሁ ምስክርነቴን አድርስልኝ አንተንም ጌታ ይባርክህ

~Selam Johnny endet neh mskr alegn abate abune echegeyohannes yaregulgn tutie lay yehone tre neger weto neber ahun gn eyetefalgn new abate hulie kenegar nachew amesgnulgn

~ሰላም ወንድሜ ጆን አደራ የ ፃድቁን ሥራ መስክርል:: 1 የ መንጃ ፈቃድ ፈተና ነበረብን ያለምንም ችግር በሰላም አስቸርሰውኛል:: 2 ለ እናቴ በጣም ቆንጆ ሥራ ሰጠዎታል :: 3 ጉንፋን አና ቁርጥማት በጣም አሞን የፃድቁን አምነት አና ፀንል ታሺቼ ወዲያው ተሺሎኛል:: 4 9ወር ልጄን ሆዶን አሞት በገድላቸው አሺቻት ወዲያው ድናለቺ የረሳሁት ካለ አባታ ማረን :: አሁን በጣም ያስቸነቀን ነገር አለና ፃድቁ ፈተውልኛ ለመመስከር ያብካ:: ክብርና ምስጋና የደካማዎን የሃትያተኛዎን ፀሎት ለተቀበለ ለአቡነ እጨግ አምላክ ለመድሃንያለም ለድንግል ማርያም አና ለፃድቁ ይሁን:: አሜን አሜን አሜን

~ጆኒ በእናት መስክርልኝ የኔ ልዩ አባቴ አቡነ እጨጌ ያረጉልኝ ታምር እኔ ስለሳቸው ተናግሬ አያልቅም እውነት ጡቴ ስር እያመመኝ በጣም ጨነቀኝ ገድላቸው ተዳብሼ ፀቦሎትን ሶስት ቀን እጠጣለሁ አድንኑኝ ብዬ ፀሎቴን ከጨረስኩ ጀምሮ 3 ቀኔ ዛሬ ደና ነኝአባቴ ለክፉ በሽታ አሳልፈው አይሰጡኝም አምናለሁ ሽብሻቦ ማርያም ቅባ ቅዱሷን ተቀብቻለሁ አመስግኑልኝ ክብር ምስጋና ለመድሃኒያለም ለእመቤት ማርያም ለአቡነ እጨጌ
Pls pls hulunm meskerelgn

~Beside Ab Wewelid Wemenfes Kidus And Amilak Amen selam nehe John Abune echege yaderegulignin limesekir new white lije diriket yizot began tamo never gena yelena lij new enam yesachewin rebel atetichew dena home eschewing abattoir adirgo yeseten amilak yimesigen leabate led abune echege yohanis Libor yigibachew amen.
John antem zemenih yetebareke yihun

~ሰላም ዩሐንሰ እንዴት አመሸክ ልጄ እንቅልፍ አልተኛም ብሎ የፃድቁን መልዕካ ደባብሼው በሰላም ተኝቶ ነግቷል ባለቤቴም ለስራ ክፍለ ሀገር ሄዶ በሰላም ወስደዉ በሰላም መልሱት ብዬ ነበር በሰላም ለቤቱ በቅቷል ልጄን ወተት ሳጠጣዉ እያስመለሰዉ ነዉ ፃድቁ ያስተካክሉልኝ እህቴም አንድ ስራ እየሞከረች ነው ተሳክቶላት ለመመስከር ያብቁኝ ዘንድ በፀሎታች አስቡኝ ክብር ለፃድቁ ክብር ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ክብር ለአናዢጋው እግዚአብሔር አብ ክብር ለግፍት ማርያም ክብር ለሁሉም ቅዱሳን እንደየማዕረጋቸዉ የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን እመአምላክ ሰሟ የተመሰገነ ይሁን ፃድቁን አመሰግኑልኝ ያንተም የአገልግሎት ዘመንክ የተባረከ ይሁን አሜን

~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ምስክርነት ለመስጠት ነበር ። ልጆቼ በተለያየ ግዜያት ታመውብኝ የአባታችንን ገድል አሻሽቼ ፀበላቸውን አጠጥቼ ድነውልኛል። ባለቤቴም መንገድና ስራውን ባርከውልኛል እንደበደሌ ሳይሆን እንደ አምላክ ፈቃድ ብዙ ተደርጎልኛል ተሳክቶልኛል ተመስገን ፈጣሪ። አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘፀገሮ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል አሜን አገራችንን ሠላም ያድርጉልን አሜን።

~በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
አባቴ አቡነ እጨጌ ዮሀንስ ያደረጉልኝን ለመመስከር ነው:1.ሆዴን እና ጨጓራዬን በጣም አሞኝ የአቡነ እጨጌን ፀበል ከሌላ ፀበል ጋር ደባልቄ ጠጥቼ ድኛለሁ።2·በሆድ ድርቀት በጣም ተሰቃይቼ አባቴን ተማፅኜ ምረውኛል።3·እናቴ ለለቅሶ ክፍለሀገር ትሔድ ነበር እንዲሁም ወደ ገዳም ጉዞ ነበራት ሁለቱም ጋር አባቴን ሰላም አድርሰው መልሱልኝ ብዬ ነገርኳቸው ሰላም መጥታለች።3·ፔሬድ በምፈልገው ቀን እንዲመጣ ለምኛቸው መጥቷል።4·እንቅርት አንገቴ ላይ ወጥቶብኝ አባቴን ከዚ በላይ እንዳያድግ እና እንዳያስታውቅብኝ ሸፍኑልኝ ብዬ ተማፅኛቸው አባቴ ሸፍነውልኛል።ክብር ምስጋና ለመድሐኒዓለም ለወላዲት አምላክ ለአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ይሁን።

~Selam Johnny endate nek, zarem miskerenet lemestet naw kesament befet weleja neber ena hospital ena blood infection lija demo becha yemebal beseta alebachu tebelen betam techekeqe neber Enam leBaeata Mariam Alkeshe lijenem enenem endetemeren lemenekwat letsadiku tematsenekwachew Huluem Lemenayen yemetesemagn enate Embirihan Dingle Mariam