Get Mystery Box with random crypto!

+++[አፍቀራ ቅድስት ስላሴ ]!ሚስጥራዊ ቦታ /ሰሜን ሸዋ መንዝ ላሎምድር /መንዝ አፍቀራ ቅድስት | አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዘጠገሮ ገዳም ፨ ABUNE ECHUGE YOHANNES ZTGRO GEDAM Johnny aleme(ዮሐንስ አለመ)

+++[አፍቀራ ቅድስት ስላሴ ]!ሚስጥራዊ ቦታ
/ሰሜን ሸዋ መንዝ ላሎምድር /መንዝ አፍቀራ ቅድስት ስላሴ/
++ ይህ ቤተክርስትያን ተራራ 4ሰዓት ይፈጃል ከወጣን በኋላ የተራራው መጨረሻ ሜዳ ሲሆን አጋዕዝተ አለም ስላሴ የቅድስት ሰላሴ ቤተክርስትያን እናገኞለን መንገዱም የተራራው 1መውጫ መግቢያ ብቻ ነው ያለው፤ የእግር መንገድ ከምንጀምርበት ጀምሮ መንገድ ሙሉ ቀን በሉት እስከ ተራራው መውጫ

ተራራውን እንደጨረስንም መግቢያው መውጫውም 1ብቻ ነው።

ከጥንት ጀምሮ ነገስታት ይህንን ቦታ ያልረገጠ ያልተባረከ የለም እምየ ምኒልክ እናትም በዚህ ቤተክርስትያን አቃቢት ነበሩ።

ይህ የምታዩት ድንጋይ ያደለው እግዚአብሔር የፈቀደለት ብዙ ነገስታት ሊቃውንት ምእመን ገዳሙ ግቢ የሚጸልዩበት ነው ሌላውን ነገር በግዜው። አፄ ሚኒልክ ጸሎት የሚያረጉበት እና የሚያርፉበት ቦታ ነው።

ተራራውን ከመውጣታችን መሬት ላይ ከ900 በላይ የጣሊያን ጦር የጭንቅላት አጽማቸው ይገኞል ይታያል።

ቤተክርስትያኑን ጣሊያን ሊያቃጥል ተራራውን ከወጣ በኋላ መግቢያዋ 1ሰለሆነች በባላ በቂ ነው ለመጠበቂያ።

ይህ የቤተክርስቲያን በአንድ በኩል በሃይቅ የተከበበ ሲሆን፤

ይህ ሃይቅ የአካባቢው ሰዎች ከዚህ በፊት ለጥናት መጥተው 2 ግዜ እስከ ኢሊኮፍተር እና ፕሌንም ወደ ባህሩ ስቦት ደብዛው እንደጠፉም ይናገራሉ

ባህሩ ሃይቁ ሚስጥር እንዳለው እና በግዜ እግዚአብሔር ሲገለጥ አለም ሁሉ የሚሆን ሚስጥር እንዳለው ይናገራሉ።

ሀይቁ ሚስጥር እንዳለው መጥጋትም አይቻልም ይስባል ከተራራው መጀመሪያ መግቢያው ነው ባህሩ፤ ወደ ተራራው ለመግባትም መሪ የሚያሳይ የአከባቢው ሰው ያስፈልጋል ዝምቡሎ መጠጋት መግባት አደጋ አለው። ተራራውም በባህር በሐይቅ የተከበበ ነውመግቢያው አንድ ነው።
የመንገዱ ነገር አይነሳ ሙሉቀን በሉት መንገዱ ከበድ ይላል።

ከጥንትም ጀምሮ እስከ ቅዱሱ አፄ ሃይለስላሴ(ተፈሪ መኮንን) ድረስ ባለባቶች ሃገረ ገዥዎች አሻፈረኞ ያሉ ራሶች ደጀአዝማቾች ቀደምት ነገስታት የሚታሰሩበት ቦታ ነበር።መታስር ማለት እስር ቤት አይደለም ቦታውን የረገጠ ጠባቂው እርሱ ባለቤቱ የተራራው መጨረሻ የአጋስተ አለም ስላሴ ገዳም ይገኞል።

< ዧን ሸዋ >መንዝ ነው።
"መንዝ"
+++[መንዝ] +ማለት መንዛት ቅዱስ ኡራኤል የጌታን ደም የረጨበት ቦታ ስለሆነ መንዝ መንዛት ማለትም ነዉ።
+++ መንዝ ማለት "መላው ንጉሳዊ ዝርያ"ማለት ነው።

+++መንዝ ማለት "የቅዱሳን ማረፊያ" ማለት ነው።

+++መንዝ ሦስት ቅዱሳን ወንድማማቾች ናቸዉ
/ጌራ;ማማእና ላሎ/

፩~+ትልቁ{መንዝ ጌራ} መሐልሜዳ ትልቅ እና ሰፊው ግዛት ነው ። በዚህ ስር
+/መንዝ ቀያ /የሚባለው በአለም የጥበብ ቦታ ጥበበኞች ጥንት ጀምሮ ጥበበኞች ቤት የቤት ዕቃዎች ስፊቶቸ አፈረን፣ ድንጋይን የሚያቀልጡ ብረት የሚሰሩ፣ ጦሩን፣ ጋሻውን፣ ጎራዴውን ጥበብን የሚሰሩ ጥበበኞች የሚባሉ በአለም ላይ የመጀመሪያውስለ ቡዲዝም የሚገልጽ በዋሻ የተሳሉ ምስሎቸ ምልክቶች ያሉበት ቦታ ነው።
+/መንዝ ዘመሮ/+የሚባለው በጣም ተዋጊ ጦረኞች በውጊያ የማይሸነፉ በሂዱበት ድል የሚያደርሩ ናቸው።
+/መንዝ ግሼ ራቤል/ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጥበበኞች የልብስ ሽመና በእንቁ፣ በወርቅ፣ በሃር፣ በጥጥ፣ በእንስሳት ፀጉር እየፈተሉ የንጉስ፣ የንግስት የነገስታት ልብስ ይሰሩ የነበሩ ጥበበኞቸ ህዝቦች ናቸው። በዚህ አካባቢ ብዙ ገዳማት ያሉበት ሚስጥራዊ ቦታዎች ዳየር ማርያም;ሩፊኤል ገዳም;አቡነ አረጋዊ ;ፉርክታ ኪዳነምህረት; ቀያ ገብርኤል ;ይገም ሚካኤል;ገደንቦ ጊዮርጊስ እረ ሰንቱ

፪~+መካከለኞዉ{መንዝ ማማ} ሞላሌ አካባቢ የጀግናው ሀገር /ደንገዜ /በጦርነት ምንም ነገር መሳት የማያቁ ጀግኖች በታሪክ የተነገረላቸው ብዙ የጦር አርበኞ አዛዦች ተዋጊዎች የነበሩበት በታሪክ ለሀገራቸው የተነገረባቸው ቦታዎች ናቸው። ሞፈር ውሃ፣ እረትመት ወንዞች ያሉበትአካባቢ ነው። ብዙ ገዳማት ያሉበት ሚስጥራዊ ቦታዎች እመጓ;እሳቷ ጽዮን ማርያም;አደሌ ሚካኤል ;ሰለድኩላ ሚካኤል ;ጉርሙኞ አቦ;አቡነ ዘራብሩክ ገዳም ;አቡነ ሲኖዳ ;ዋካ ጊዮርጊስ; እረ ሰንቱ

፫~+ትንሹ{መንዝ ላሎ} ወገሬ; /አፍቀራ /አካባቢ፣ የነገስታት መወለጃ፣ መቀያየርያ መሾሚያ፣ ያጠፋ የማቆያ የማስተማርያ ቦታ ያለበት ቦታ እና 4ወንዞች የሚገኞበት አዳባይ ወንዝ ያለበት ነው። ሌላ ሚስጥራዊ ባህር ያለበት ወደ በህሩ መጥጋት የማይቻልበት አንድ መግቢያ በር ያለበት፤ ባህር እንዲሁም ብዙ ሚስጥር ያዘ አንድ መግቢያ ተራራ ያለው አፍቀራ ሰላሴ ያለበት ነው። ብዙ ገዳማት ያሉበት ሚስጥራዊ ቦታዎች አፍቀራ ስላሴ;አፍቀራ ኪዳነምህረት ;ገላዎዲዮስ ገዳም;ነጎድጓድ ጊዮርጊስ ;ገዲ ጊዮርጊስ ; ጨለሚት ኪዳነምህረት ;ወይን አባ ገብርኤል ;ዘብር ገብርኤል ;ግንድ አጥሚት ማርያም;;አባ ሊባኖስ;ገፈቱ እግዚአብሔር አብ;12ቱ ሐዋርያት ገዳም እረ ስንቱ

+በአንድ ወረዳ ከ170 በላይ ገዳማት ደብር ያለበት ሐገር ነዉ።

ለምሳሌ የምታውቋቸው የውሸት ንትርክ የሚያሟቸው አፄ ዳዊት አፄ ዘርዓያዕቆብ አፄ ዩኩኖ አምላክ አፄ ገላውዴዎስ አፄ ፋሲል አፄ ሚኒልክ ፤ራስ መኮንን አፄ ሃይለስላሴ አባት ድረስ የዘር ሃረጋቸው ሃገር ነው ይህ ቦታ።

4ወንዞች ተገናኞተው 1የሚሆኑበት የሚገኙበት አዳባይ ወንዝም በዚህ ይገኞል።

እንዲሁም አፍቀራ ቅድስት ኪዳነምህረት ከሰማይ ጽዋ የወረደላት ከየት እንደመጣ የማይታወቅ እንደ ናዳ ስንዴ ወርዶ የሚገኞባት ገዳሟን ለመሳለም ለመጣ 1ሙሉ ድፎ ዳቦ ለየአንዳንዱ የሚሰጥበት አስገራሚ ገዳም ያለበት ቦታ ነው።

ብዙ ሚስጥር ይዞ ያልታወቀ ቦታ እግዚአብሔር እውነቱን 1ቀን ይገልጸዋል።

ቦታው ለመርገጥ እግዚአብሔር ይፍቀድላችሁ።አሜን!

ቦታው፦ሰሜንሸዋ ሞላሌ 255ኪሜ እንደደረስን ከሞላሌ ወገሬ 30ኪሜ በመኪና እንደሄድን ከወገሬ የ5ሰዓት የእግር መንገድ አፍቀራ ያገኞሉ።