Get Mystery Box with random crypto!

Jigjiga University Students union

የቴሌግራም ቻናል አርማ jjusuofficialchannell — Jigjiga University Students union J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jjusuofficialchannell — Jigjiga University Students union
የሰርጥ አድራሻ: @jjusuofficialchannell
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 699
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የጂግጂጋ/ዩ/ተ/ህ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official telegram channel of JJUSU. In this channel educational & useful info about Jigjiga University students will be released.

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-07 09:41:02 የዘንድሮ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

https://t.me/JJUSUOfficialChannell
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
229 views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 09:09:49 #Reminder

#National_Exit_Exam

በመጪው 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው

• የመውጫ ፈተና ምዘና የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።

• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡

• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡

• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፤ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።

• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡

• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።

https://t.me/JJUSUOfficialChannell
235 views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 09:42:52
To all freshman students of 2014
2.2K views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 12:53:34 ዝውውር በላኪና ተቀባይ ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ትምህርት ሚኒስቴር ወሰነ።

ትምህርት ሚኒስቴር ዝውውርን በተመለከተ ያለፉትን ጥቂት አመታት ሲጠቀምበት የነበረውን ማለትም ዝውውር የሚጠይቁ ተማሪዎች ከመንግስት ሆስፒታሎች በህክምና ቦርዶ የተረጋገጠ ማስረጃ ይዘው ለመስሪያ ቤቱ በማቅረብ ዝውውር ይፈፅም የነበረውን ስርዓት የተማሪዎችን ጊዜ እና ገንዘብ ወጪ እያስደረገ መሆኑን በማየት ዝውውርን በተቀባይና በላኪ ዩንቨርሲቲዎች የጋራ ስምምነት ይፈፀም ዘንድ ውሳኔ አስተላልፏል።

#ማሳሰቢያ

፨ዝውውር የሚጠይቁ ተማሪዎች ከመንግስት የህክምና ተቋማት የህክምና ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
1.8K views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 11:48:12
ለ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን
አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ከግንቦት 1-3/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲው ስትመጡ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

ከ8-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃወችን ዋናውና ኮፒው
3×4 ፎቶግራፍ (8)
አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስ ጨርቅ
የስፖርት ትጥቅ

https://t.me/JJUSUOfficialChannell
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
1.6K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 13:59:42 #MoH

የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች ከግንቦት 01 እስከ 04/2014 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የተፈታኝ ባለሙያዎች የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አድርጓል።

ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 01/2014 ዓ.ም

ነርሲንግ ~ ግንቦት 02/2014 ዓ.ም

ሕክምና፣ ጤና መኮንን እና ዴንታል ሜድስን
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 03/2014 ዓ.ም

ሚድዋይፍሪ እና ሜዲካል ላቦራቶሪ
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም

https://t.me/JJUSUOfficialChannell
873 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 12:26:00 የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ


ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ አደረገ፡፡

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣ በSMS፡- 9444 እንዲሁም በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ መባሉን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢውን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሐ ግብር የሚያሳውቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
1.5K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 18:34:43 #NewsAlert

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንዲሰጡ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

መኮራረጅ፣ የፈተና ስርቆትና ሌሎች ችግሮችን ለማስቀረት ከዚህ በኋላ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በትምህርር ቤቶች ሳይሆን በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ የሚሰጡ ይሆናል ሲሉ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል።

ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የትምህርት ጥራት ላይ እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ አንዱ ችግር ከሀገር አቀፍ ፈተና ጋር ተያይዞ የሚነሳ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት የሚያስችሉ አንድ ሚሊዮን ታብሌቶችን በማስመጣት ላይ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሀኑ መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

ይህ የጂግጂጋ/ዩ/ተ/ህ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official telegram channel of JJUSU. In this channel educational & useful info about Jigjiga University students will be released.
https://t.me/JJUSUOfficialChannell
1.7K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 17:09:07
"ሰላሟን አፅናለሁ ለወገኔ እደርሳለሁ" በሚል መርህ ያገባናል ኢትዮጵያ በጎ-አድራጎት ማህበር ለድንቆቹ ለጅግጅጋ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች፣ከፍተኛ የስራ አመራሮች እና ለግቢው ማህበረሰብ ከ01/08/14 እስከ 02/08/14 ዓ.ም የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተዘጋጀውን ልዩ የመዝናኛ እና የዐዕምሮ ማንቂያ ስልጠናን ያለውን ሂደት እና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚኖረንን ክስተት የሚሆነውን ቆይታችንን ዝርዝር በቅርብ ቀን።
ወጣት ለምክንያት እንጂ
ለስሜት አይሞትም!!!!
ያገባናል ኢትዮጵያ!!
819 views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:08:57 የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
----------------------------------------

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።በማህበራዊ ሳይንስ አይነስውራን መደበኛ ተፈታኞች ሁለቱም ፆታ ማለፊያ ነጥብ 200 ሆኖ ተቆርጧል።


በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።በማህበራዊ ሳይንስ አይነስውራን መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 250 ሆኗል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።
1.3K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ