Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ለማገልገል በእጩነት የተያዙ | Jimmaa Abbaa Jifaar/ጅማ አባጅፋር እ/ኳ ክለብ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት ለማገልገል በእጩነት የተያዙ ግለሰቦች ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል

የአስመራጭ ኮሚቴው በትናንትናው ዕለት ጉባኤው የአፋር እግርኳስ ፌዴሬሽን አቶ ዓሊሚራ መሐመድ በሥራ-አስፈፃሚ እጩነት ይያዙልኝ ብሎ ያቀረበውን ጥያቄ ጉባኤው ማፅደቁን አንስቶ ምርጫው ህጋዊነቱ ላይ ጥያቄ እንዳይነሳ የአቶ ዓሊሚራ መሐመድ ጉዳይ ወደፊት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማሟያ ምርጫ ሲደረግ እንዲካተት ተወስኗል። በዚህ መሐል በአፋር እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዮች፣ አቶ ዓሊሚራ መሐመድ እና አስመራጭ ኮሚቴው መካከል አለመግባባት ተከስቶ የነበረ ቢሆንም ከፊፋ የመጡት ታዛቢ ባቀረቡት ሀሳብ በመጨረሻ የአስመራጭ ኮሚቴው ሀሳብ ፀንቷል። ይህንን ተከትሎ ዛሬ ከፕሬዝዳንት ምርጫው ውጪ ለ10 የሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ እንደሚደረግ ተገልጿል።