Get Mystery Box with random crypto!

بسم الله الرحمن الرحيم በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው። | ELAFE TUBE

بسم الله الرحمن الرحيم በአላህ ስም እጅግ
በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።

ዝግጅት ፦ በዓብዱልሰመድ መሓመድኑር የመሳኢሊል ጃሂልያ ኪታብ ትርጉም እና ከመሳኢሊል ጃሂልያ ኪታብ የምንወስዳቸው ትምህርቶች

በቅድሚያ የጃሂሊያ ማህበረሰቦች (የጃሂሊያ ዘመን) --- ማለት ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በፊት የነበረውን የሰዎችን ሁኔታ የሚገልፅ ነው። ይህ መጠርያም ክርስትያኖችን፣ አይሁዶችን፣ ጣኦት አምላኪዎችን፣ እሳት አምላኪዎችን እና የመሳሰሉትን ጠቅሎ የያዘ ነው። ይህ የጃሂሊያ ዘመን የሚለው መጠርያ ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ቁርአንን ይዘው ከመጡ ቡሃላ ተነስቷል።

قال شيخ الإسلام محمد بن عبد الوهاب – رحمه الله تعالى – في مقدمة رسالته: مسائل الجاهلية: هذه مسائل خالف فيها رسول الله صلى الله عليه وسلم أهل الجاهلية الكتابيين والأميين، مما لا غنى للمسلم عن معرفتها. فالضِّدُّ يُظْهِرُ حُسْنَهُ الضِّدُّ وبِضِدِّها تتبيّن الأشياء فأهم ما فيها وأشدها خطراً: عدم إيمان القلب بما جاء به الرسول صلى الله عليه وسلم، فإن انضاف إلى ذلك استحسان ما عليه أهل الجاهلية تمت الخسارة، كما قال تعالى {وَالَّذِينَ آمَنُوا بِالْبَاطِلِ وَكَفَرُوا بِاللَّهِ أُولَئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ} [سورة العنكبوت: 52]

ይህ መፅሃፍ የሚዳስሰው ነብያችን የተቃወሟቸውንና ያወገዟቸውን የጃሂሊያ ማህበረሰቦች (በጃሂሊያ ዘመን) ሲሰሯቸው የነበሩትን ተግባራትን ነው። እነዚህን ጉዳዮች ሙስሊም ሁሉ ሊያውቃቸው ይገባል። ምክንያቱም መጥፎን ነገር ማወቅ ከመጥፎ ነገር ለመጠበቅ ግድ ይላል እና። የመፅሃፉም ግብ የነሱን ተግባራት ካሳወቀን ቡሃላ ከነዚህ ተግባራት እንድንርቅ ነው። የጃሂልያ ማህበረሰቦች ከሚሰሯቸው ከነበሩት ሁሉ የከፋው ነብያችን ያመጡትን አስተምህሮ በልብ አለማመን ነው። በዚህ ላይ ደግሞ የጃሂልያ ማህበረሰቦች ሲሰሩት የነበረውን ነገር ማድነቅ እና ማሳመር ከተጨመረበት ትልቅ ኪሳራ ውስጥ እንገባለን።

አላህ ልክ እንደሚለዉ)

قُلْ كَفَىٰ بِاللَّهِ بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ شَهِيدًا يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَالَّذِينَ آمَنُوا بِالْبَاطِلِ وَكَفَرُوا بِاللَّهِ أُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ ﴿العنكبوت: ٥٢﴾

«በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ በአላህ በቃ፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለውን ሁሉ ያውቃል» በላቸው፡፡ እነዚያም በብላሽ ነገር ያመኑ በአላህም የካዱ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎች ናቸው፡፡ (29: 52)

የሚከተሉት የጃሂልያ ማህበረሰቦች (በጃሂሊያ ዘመን) ሲሰሯቸው የነበሩትን ተግባራት ናቸው ፦

መፀተፏ እጅግ አስተማሪ መፀሀፍ ነዉ መኸታተል ለምትፈልጉ ኪታቡን ገዝታቹ በቻናላችን ስለተጀመረ መከታተል ትችላላቹ

አል ሂዳያ ቲቪ ቀጥተኛዉ መገድ