Get Mystery Box with random crypto!

ልዕልት አንድሮሜዳ🌍

የቴሌግራም ቻናል አርማ jandromeda — ልዕልት አንድሮሜዳ🌍
የቴሌግራም ቻናል አርማ jandromeda — ልዕልት አንድሮሜዳ🌍
የሰርጥ አድራሻ: @jandromeda
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 363
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የተከፈተው ስነ ፈለግን ለሚወዱና ለሚመረምሩ ብቻ ነው።
በዚህ ቻናል ላይ ስለ ህዋ መጤ ፍጡራን(ALIEN)👽፣ስለ ሁለንታ(UNIVERSE)፣ስለ ህብረ ኮከብ(constellation)🌌፣ስለ ጨረቃ🌑 ፣ስለ አነጋጋሪው ቤርሙዳ፣ስለ አስደናቂ ተፈጥሮ ስላለው back hole....እናወጋበታለን።

ይህን ቻናል ለሚዷቸው ለወዳጅ ዘመድ ሼር
በማድረግ እውቀትን ያስተላልፉ ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-15 12:06:44 ግንቦት 8/2014 ዓ.ም. ሙሉ ጨረቃ በኢትዮጵያ በሌሎች ሃገራት ደግሞ የደም ጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
እንደሚታወቀው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰተው ጨረቃ ሙሉ ለሙሉ በመሬት ጥላ ውስጥ ስታልፍ ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉ በተጋረደችባቸው ሰዓታትም ቀይ ሆና የደም ጨረቃ (ብለድ ሙን) የሚባለውን ቀለም ታሳያለች፡፡ በጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ ሰማያዊ ብርሃን በመሬት ከባቢ አየር ሲበተን ቀዩ ብርሃን ብቻ ጨረቃ ላይ ይደርሳል።

የደም ሙሉ ጨረቃ ደም ግርዶሽ Super Blood Moon total lunar eclipse በሃይማኖት፣ በሳይንስ እጅግ ብዙ ምሳሌዎችና ትርጉሞች ያሉት ሲኾን በማዛሮት መጽሐፌ ላይ በስፋት ስለተተነተነ አንባብያን መጽሐፉን አንብበው እንዲረዱት በመጋበዝ በዚህ ላይ ግን ክስተቱን ብቻ ጠቅሼዋለሁ።

ይህ የደም ጨረቃ ግርዶሽ (Super Blood Moon)
በምሥራቅ ፓስፊክ፣ በአሜሪካ፣ አንታርክቲካ፣ በአውሮፓ በደንብ ይታያል። በአህጉራችን አፍሪካ ቢታይም በኢትዮጵያ ግን አይታይም ምክንያቱም በኢትዮጵያ ማታ 12:02 ላይ ስለምትጋረድ በዚህ ሰዓት ደግሞ ጨረቃ ከአድማስ በታች በመኾና ለማየት አዳጋች ስለሚኾን ነው።

ቢሆንም ግን በሀገራችን ሰኞ ግንቦት 8 ሙሉ ጨረቃ በመሆኗ ወደ መሬትም በጣም በመጠጋቷና መጠኗና ብርሃኗም ከወትሮው ስለሚጨምር “ሱፐርሙን” (ታላቋ ጨረቃ) super moon ተብላ የምትታወቅበት ወቅት ላይ መሆኗ ነው፡፡

በተለይ ጨረቃን ፎቶ ማንሣት እንደኔ ለሚወዱ ውብ የሆነ የሙሉ ጨረቃን ፎቶ ለማንሣት ይህ የሙሉ ጨረቃ (ፉል ሙን ፌዝ) እና ሱፐር ሙን ወቅት ከሁሉም ጊዜ በተለየ በጣም ተመራጭ ጊዜ ነው፡፡

ፀሐይ እንደጠለቀች ምሽት ላይ ጀምሮ እስኪነጋ ድረስም ደምቃ አብርታ ጎልታ ስለምትታይ ለአድናቂዎችና ለተመልካቾች ጥሩ ጊዜ ይሆናልና ፎቶ እያነሣችሁ መደሰት ትችላላችሁ፡፡

ግርዶሹ በሚታይባቸው በምሥራቅ ፓስፊክ፣ በአሜሪካ፣ አንታርክቲካ፣ በአውሮፓ ሀገራት ያላችሁ ደግሞ ደመና ከሌለ በስተቀር ግርዶሹ በምሽት ስለሚታይ የሚታይበትን Space.com በመጠቀም ያላችሁበትን ከተማ በመሙላት
ማታ እያያችሁ መደሰት ትችላላችሁ።
374 viewsThat Man y 19gu, 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 11:27:19
EID MUBAREK اد مبرك
ለሁሉም ሙስሊም ወንድም እህቶቼ እንኳን ለተከበረው ለ1443ኛ ኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን , በዓሉ የሰላም፤የፍቅር፤የመተሳሰብ ይሁንልን!!
309 viewsThat Man y 19gu, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 10:51:39
632 viewsThat Man y 19gu, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 10:51:38
ዛሬ ምሽት “ቬነስ እና ጁፒተር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠጋግተው እንደሚታዩ” የህዋ ሳይንቲስቶች አስታወቁ!

የህዋ ሳይንቲስት እና ሶሳይቲ ፎር ፖፑላር አስትሮኖሚ ውስጥ ዋና የከዋክብት ተመልካች ፕ/ር ሉሲ ግሪን ፣ ክስተቱ ለከዋክብት አጥኚዎች ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ማኅበረሰብም አስደናቂ ብለዋል፡፡ሁለቱ ደማቅ ፕላኔቶች ዛሬ ምሽት ለመነካካት ጥቂት እስከሚቀራቸው ድረስ ነው የሚቀራረቡት።ፕላኔቶቹ በየዓመቱ የሚቀራረቡ ቢሆንም፤ ዘንድሮ ግን ከመቼውም በበለጠ የሚጠጋጉበት ነው ተብለዋል፡፡

ይህንን አይነት ክስተት እስከ ፈረንጆቹ 2039 ድረስ በድጋሚ እንደማያጋጥምም ነው የተገለጸው። ክስተቱን ዛሬ ምሽት በዐይን ወይም በአጉሊ መነጽር መመልከት እንዳሚቻልም ነው የህዋ ሳይንቲስቶች መረጃ የሚያመለክተው፡፡
606 viewsThat Man y 19gu, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 21:22:06 ኤለን መስክ፤ ስታርሊንክ የተሰኘው የበይነ መረብ ፕሮጀክቱ ሳተላይቶች ሕዋን እያጣበቡ ነው መባሉን አስተባብሏል።

በምድር ምህዋር "በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ" ሳተላይቶች መንቀሳቀስ ይችላሉ ሲል ለፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ተናግሯል።

ኤለን ይህን አስተያየት የሰጠው የዓለም አቀፉ ሕዋ ምርምር ጣቢያ ኃላፊ "መስክ የሕዋ ኢንዱስትሪ ሕግ ራሳቸው ናቸው የሚያወጡት" ካሉ በኋላ ነው።

በያዝነው ሳምንት ቻይና ሳተላይቶቼ ከስታርሊንክ ሳተላይቶች ጋር ሊጋጩ ነበር ስትል ቅሬታ አቅርባለች።

"ሕዋ ማለት እጅግ ሰፊ ሥፍራ ነው፤ ሳተላይቶች ደግሞ ከዚህ አንፃር በጣም ኢምንት( ትንሽ ) ናቸው" ብሏል መስክ።


የስፔስኤክስ ባለቤቱ ኤለን መስክ የእሱ ድርጅት ሳተላይቶች ሌሎች ድርጅቶችን ከገበያው እያስወጡ ነው ስለመባሉም ማስተባበያ ሰጥቷል።

"ይህ ሌሎች እንዳይንቀሳቀሱ የምናደርግበት ዘርፍ አይደለም። እኛ ማንም ሥራውን ከመሥራት ወደ ኋላ እንዲል አላደረግንም። እንድናደርግም አይጠበቅም።"

"በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶች ምንም ማለት አይደሉም። ምድር ላይ ጥቂት ሺህ መኪናዎች አሉ እንደማለት ነው" ሲል ለጋዜጣው ተናግሯል።

የአውሮፓ ሕዋ ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ጆሴፍ አስክባቸር ስታርሊንክ የሚያስወነጭፋቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የኮሚዩኒኬሽን ሳተላይቶች ለተወዳዳሪዎች አስጊ ናቸው ሲሉ በቅርቡ ተናግረው ነበር።

ሌሎቹ ባለሙያዎች ደግሞ በሳተላይቶች መካከል የሚኖር ግጭትን ለማስቀረት ርቀታቸውን ጠብቀው ነው መንሳፈፍ ያለባቸው ይላሉ።

ሳይንቲስቶች ከዚህ በፊት በሕዋ ላይ የሳተላይቶች ግጭት እንዲቀንስ የዓለም መንግሥታት መረጃ እንዲያጋሩ ጠይቀው ነበር።

ሳይንቲስቶቹ፤ መንግሥታት በግምት ሕዋን እየዞሩ ነው ስለሚባሉት 30 ሺህ ሳተላይቶች እንዲሁም ስብርባሪዎች መረጃ ማቅረብ አለባቸው ይላሉ።

ቻይና የስታርሊንክ ሳተላይቶች የእኔን ሳተላይቶች ሊገጩ ለጥቂት ነው የተረፉት ካለች በኋላ ኤለን መስክ የመገናኛ ብዙሃንና የማኅበራዊ ድር አምባው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

ቻይና፤ ሁለት ጊዜ ሳተላይቶቿ ከስታርሊንክ ሳተላይቶች ጋር ከመጋጨት መትረፋቸውን ገልጣለች።

ቻይና ለተባበሩት መንግሥታት የሕዋ ጉዳዮች ቢሮ ባስገባችው ደብዳቤ ላይ እንዳሰፈረችው ሁኔታው የተፈጠረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነው።

"የቻይና ሕዋ ጣቢያ ለደኅንነት በማለት የግጭት ማስወገድ መንገዶችን ተጠቅሟል" ሲል የጣቢያው ድረ-ገፅ አስነብቧል።

ቻይና በኤለን መስክ ላይ ያቀረበችው ጥያቄ እስካሁን በገለልተኛ አካል አልተጣራም።

ቻይና፤ ዩናይትድ ስቴትስ የሕዋ ሕግጋትን በመጣስ የጠፈርተኞችን ሕይወት አደጋ ላይ እየጣለች ነው ስትልም ወቅሳለች።

የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ዣዎ ሊጂያን አሜሪካ ኃላፊነት እንዲሰማት ሃገራቸው ጥሪ እንደምታቀርብ ገልጠዋል።

ስፔክስ የተባለው የኤለን መስክ ድርጅት እስካሁን 1900 ሳተላይቶችን በስታርሊንክ ኔትዎርክ ስም አምጥቋል።

https://t.me/jAndromeda
536 viewsኢትዮጵ , edited  18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 10:03:17 ሰሞኑን ስላልፖሰትን ይቅርታ እንጠይቃለን

ከነገ ጀምሮ በአዲስ መልክ ወደ ስራ እንገባለን

https://t.me/jAndromeda
389 viewsኢትዮጵ , edited  07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 12:59:00 ኤለን መስክ ያስወነጨፋት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ልትጋጭ ነው


የኤለን መስክ ሕዋ ምርምር ተቋም ያስወነጨፋት አንዲት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ተጋጭታ ልትፈነዳ እንደምትችል ተሰምቷል።

ፋልከን 9 የተሰኘችው ሮኬት ወደ ሕዋ የተወነጨፈችው በፈረንጆቹ 2015 ሲሆን ነገር ግን የያዘችው ነዳጅ በመገባደዱ ምክንያት ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ ምድር ከመመለስ ይልቅ ሕዋ ላይ ስትዋልል ነበር።

ጠፈርተኛው ጆናታን ማክዶዌል፤ ከጨረቃ ጋር የተጋጨች የመጀመሪያዋ ከቁጥጥር ውጭ የሆነች ሮኬት ትሆናለች ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር መጋጨቷ ያለው ፋይዳ ይህን ያህል የሚባል አይደለም።

ከሰባት ዓመታት በፊት ሥራዋን ጨርሳ ሕዋ ላይ የተረሳችው ሮኬት ከ1.6 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት አዳርሳለች።

ስፔስኤክስ የተባለው የኤለን መስክ የሕዋ ምርምር ተቋም ወደፊት ሰዎች በሌሎች ፕላኔቶች ላይ እንዲኖሩ ማመቻቸት የሚል ዓላማ አለው።

ሮኬቷ ከ2015 ጀምሮ በተለያዩ የምድር፣ የጨረቃና የፀሐይ የስበት ኅይሎች አቅጣጫዋን እየቀያየረች ቆይታለች ይላሉ ጠፈርተኛው።

"የስበት ሕግን ተከትላ ከጥቅም ውጭ ሆና ነበር ማለት ይቻላል።"

ይህች ሮኬት ብቻ ሳትሆን ለተልዕኮ ተስወንጭፈው ዕቅዳቸውን ያሳኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሮኬቶች ሕዋ ላይ እየዋለሉ ይገኘሉ።

"ባለፈው አስር ዓመት ከቁጥጥራችን ውጭ የሆኑ ቢያንስ 50 ትላልቅ ሮኬቶች አሉ። ከዚህ በፊትም ሳናውቀው ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል። ይሄኛው የመጀመሪያው የታወቀ ክስተት ይሆናል ማለት ነው" ይላሉ ማክዶዌል።

የፋልከን 9 ወደ ጨረቃ መገስገስ ሊታወቅ የቻለው ጋዜጠኛ ኤሪክ በርገርና የዳታ ተንታኙ ቢል ጌሪ ባደረጉት ክትትል ነው።

ሮኬቷ፤ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወርሃ መጋቢት አራት ከጨረቃ ጋር እንደምትጋጭ ተገምቷል።

"4 ቶን የምትመዝን ከኋላ ሞተር ያዘለች ብረት ማለት ናት። ይህን ያህል ክብደት ይዛ በሰዓት ከ8 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር በላይ እየተጓዘች ስትጋጭ የሚፈጠረው ነገር አስደሳች አይሆንም" ሲሉ ያክላሉ።

ሮኬቷ ከተጋጨች በኋላ የጨረቃ መልክዓ ምድር ላይ አነስ ያለ ሰው ሰራሽ ጉደጓድ ትፈጥራለች።

ሶፍትዌር ተጠቅሞ ለምድር የቀረቡ ሕዋ ላይ ያሉ ቁሶችን የሚከታተለው ቢል ጌሪ ሮኬት መጋቢት 4 ከጨረቃ እንደምትጋጭ ገምቷል።

በፈረንጆቹ 2009 ፕሮፌሰር ማክዶዌልና ሌሎች ጠፈርተኞች መሰል ነገር ቢፈጠር ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን ሐሳብ በቤተ ሙከራ አዳብረውታል።

ይህ ማለት ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር ስትጋጭ ሳይንቲስቶች ብዙም የሚማሩት አዲስ ነገር የለም ማለት ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ።

አክለው አሁን ምንም እንኳ ሕዋ ላይ እየዋለሉ ያሉ ቁሶች እየሄዱ ሲጋጩ ችግር ባይፈጥሩም ወደፊት ግን አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ።

ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር እስክትጋጭ ባለው ጊዜ የስበት ህግን ተከትላ ሕዋ ላይ ትንሳፈፋለች።
507 viewsኢትዮጵ , 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 12:58:59
296 viewsኢትዮጵ , 09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 15:32:26
ይሄ ትኬት ያለው አለ እንዴ ?
449 viewsኢትዮጵ , 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 18:50:40 አስትሮ Promotion

የቴሌግራም ቻናል ያላችሁ በሙሉ ማንኛውንም ቻናላችሁን ያለምንም ክፍያ በመመዝገብ ቻናላችሁ ይተዋወቅላችኋል።

ከ 500 በላይ ቻናል ያላችሁ በፍጥነት ተመዝገቡ።
@Astro_bk
@Astro_bk

አስትሮ_PROMOTION ላይ ቻናል ለማስመዝገብ
@Astro_bk
@Astro_bk

በስር የምታዩዋቸውን አስተማሪና እውቀት ሰጪ ቻናሎች ናቸው የምትፈልጉትን በመምረጥ ተቀላቀሉ። ብትችሉ ሁሉንም ተቀላቀሉ።
363 viewsBiruk ||| s, 15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ