#እኔ_ነኝ_አልዓዛር ... አምላክ ተሸነፈ #Part_2 “ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።” — ዮሐንስ 11፥35 ከደቂቃዎች በኋላ ከምት ሊያስነሳው ሳለ ማልቀስ ምን አስፈለገው ?? እዩልኝ የጌታዬን ፍቅር : ማርያም እግሮቹ ስር ተደፍታ ስታነባ የጌታችን አንጀት ተላወሰ: አብሯቸው አለቀሰ። #በምንም_አይነት_በደል : #ድካም : #ሀዘን : #ብቸኝነት : #ተስፋ_መቁረጥ እግሮቹ ስር ድፍት ብለው ለሚያነቡ በሀዘን ለደቀቁ ነብሶች : ለተሰበሩ ልቦች ጸሎትን ከመመለስ #ያለፈ ነውና ጌታችን : ሀዘንችንን የሚካፈል ርህራሄውም የማያልቅ ነውና #መፀለያችሁን : #እግሮቹ_ስር_መደፋታችሁን መቼም እንዳታቆሙ !! #ይገባዋል : #ይረዳናል #ይራራልናል : #ህመማችንን ይካፈላል ። “እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።” — ዕብራውያን 2፥18 በተጠቀሰው ክፍል ለክርስቶስ እንባውን ማፍሰስ ከታላቅ ፍቅሩ በስተቀር ምክንያት : ከርህራሄው በስተቀር ሰበብ የለንም። ደርሶም በመቃብሩ የተጫነበትን ድንጋይ አንሱ ቢላቸው : የገዛ እህቱ #ይሸታል አለች( አልዓዛርስ 4 ቀኑ ለዘመናት በሃጢያት የሞትን እኛ እንደምን እንብስ??) ከዚያም በእምነት የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታይ ነገራት። #ይሄ_ሁሉ_አልበቃ ብሎት ቸሩ ጌታ #የሞተውን(እኛ ሬሳ የምንለውን ) እርሱ አልዓዛር ሆይ ብሎ #በስሙ ጠራው ።እኛማ የምንወደው ሰው እንኳ ለሞት ከሆነ እንፈራው የለ : የክርስቶስ ፍቅር ግን ከመቃብርም ያለፈ ነው። #በሃያል_ድምፁ_ሞት_ተንበረከከ!! እኛም የሚያፅናናንን የትንሳኤ ተስፋ በዚህ ቃል ብርሃን ተመለከትን። ክብር ለስሙ ይሁን። #ከነመግነዙ አልዓዛር ከመቃብር ወጣ። በአይሁድ ዘንድ ተሰምቶ የማይታወቅ ነገር ሆነ ። ጌታም ፍቱትና ይሂድ ብሎ በነፃነት እንዲኖር ነፃ አወጣው። #እኔ_ነኝ_አልዓዛር ... See the aamazing operation of #GRACE here ልክ እንደ አልዓዛር #እኔም_ሙት ነበርኩኝ። በሃጢአት ታምሜ በሞት ተቀጣሁኝ ። የኔ ጌታ ባለበት መች ቆየ : እኔ ወዳለሁበት ወረደ : ባለበት ሆኖ አይደለም ያዳነኝ : ሰው ሆኖ መጥቶ ነው ። ለአልዓዛር እንባውን በሀጥያት ለሞትኩት ለእኔ ግን #ደሙን አፈሰሰልኝ ። የበደልና የሀጥያትን #ድንጋይ ከላዬ አንከባለለ። #በስሜ ቢጠራኝ ወደ እርሱ መጣሁ። የሀጥያትና የሞት ሰንሰለቴን በጣጥሶ #ፈቶ ለቀቀኝ። ክብር ምስጋና ይግባው !! እባካችሁ ወደሚወዳችሁ ክርስቶስ ኑ!! እመኑ በእርሱ ያድናችኋል ። “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” — ራእይ 3፥20 @untothelamb @untothelamb @untothelamb 323 viewsⓈ ⓘ, 07:22