Get Mystery Box with random crypto!

አራቱ የብሉይ ኪዳን መስዋዕት 1.የኃጢአት መስዋዕት ቅድስናን ያመለክታል 2.የሚቃ | ስለ እውነት ዝም አልልም ( I will not remain silent about the truth‌‌)

አራቱ የብሉይ ኪዳን መስዋዕት

1.የኃጢአት መስዋዕት

ቅድስናን ያመለክታል

2.የሚቃጠል መስዋዕት

አምልኮን ያመለክታል

3.የእህል ቁርባን

ምስጋናን ያመለክታል

4.የደህንነት መስዋዕት

ሕብረትን ወይም አንድነትን ያመለክታል

-------------------------------------------
“የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ለእግዚአብሔርም ስለ ደኅንነት መሥዋዕት በሬዎችን እንዲሠዉ የእስራኤልን ልጆች ጐበዛዝት ሰደደ።”ዘጸ 24፥5

“የወይፈኑን ሥጋ ግን፥ ቁርበቱንም፥ ፈርሱንም ከሰፈር ውጭ በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።”ዘጸ 29፥14

“ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል። ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል።”ዘሌ 4፥10

“ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ቀንዶች ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም ለሚቃጠል መሥዋዕት ከሚሆነው መሠዊያ በታች ያፈስሰዋል።”ዘሌ 4፥25


“በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የደኅንነቱንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩ መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።”1ኛ ነገ 8፥64

https://t.me/IWNRSATT