Get Mystery Box with random crypto!

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የቴሌግራም ቻናል አርማ itsmetsiyearsemalj — ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘
የሰርጥ አድራሻ: @itsmetsiyearsemalj
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.69K
የሰርጥ መግለጫ

በቤቴ ሲታደሙ ከጥበብ ማዕድ ይቋደሳሉ
በኔና በሌሎች የተፃፉ
🌹ግጥሞች🌸
🌹ወጎች 🌸
🌹ልቦለዶች 🌸
ሌሎችም...
━━━━━━━━ ✦
ለማንኛውም አስተያየት
@Tsiyon_awit and
@itsmetsita
ይጠቀሙ።
Join us
@itsmetsiyearsemalj

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 21:28:12 ሃሳቡ ቦግ ብሎ የታያትን ያህል በደስታ በራች፤ ናንሲ ።
‹‹ማለት ፒያኖ ብለማመድ ፤ አካሄዴን ብቅይር፣፤ አዲስ ሰዉ ሌላ ሰው ሆንኩ ማለት ነው ፤ አደል ? ከዚያ በኋላ እኮ ብፈልግ ስሜንም መቀየር እችላለሁ ?! » አለች ናንሲ ። «ያን ያህልም መቻኮል የለብንም ስም እስከመለወጥ ማለቴ ነው ። አንደኛሽን ራስሸን ያጣሽ መስሎ እንዲሰማሽ አያስፈልግም ። ራስሽን ማጣትሽ ሳይሆን መጨመርሽ ፤ ማደግሽ መሆኑን ማወቅ አለብሽ ። እስኪ እናስብበትና እንሞክረው ። ድንቅ ነገር ሳይገጥመን አይቅርም » አለች የአዕምሮ ህክምና ሊቋ ፌ «
« በመጀመሪያ ድምፄን… ሌላ ድምፅ እፈልጋለሁ» አለች ናንሲ እየሳቀች ። « እንደዚህ ዓይነት ድምፅ » አለች ድምጸን ቀነስ ወፈር አድርጋ ። ፌ ሳቀችእና « እሱን ድምፅ በደንብ ከተለማመድሽው ፒተር ሥራ ሊበዛበት ነው ማለት ነው » አለች። «እንዴት? » አለች ናንሲ በዚያው ጐርነን ባለው ድምፅ። «ጺም መሥራት ግድ ይሆንበታላ !»
« እንዲህ ነው ። እንኳን ነገርሺኝ !» ሁለቱም አንዴ በሳቅ መንከትከት ጀመሩ ። ተነስታ እንደትንሽ ልጅ መቅበጥበጥ ጀመረች ። ናንሲን እንዲያ ስትሆን ስታያት ፌ ሁልጊዜም ይገርማታል ። ሀያ ሶስት አመቷ ነው ። ናንሲ ግን ሃያ ሶስት ዘመን ቀርቶ ረጅም ዘመን የኖረም ሰው ቢሆን ያላየውን ብዙ ነገር እያየች ነው፡፡ እየሆነች ነው ። ውስጧ ግን ትንሽ ልጅ ናት ። ይኸው ስትቀብጥ ስትቅበጠበጥ !
« ግን አንድ ነገር አለ ፤ ናንሲ››
« ምን ነገር ?»
«ለምን ኦዲስ አንችን መፍጠር እንዳለብን ማወቅ አለብሽ ። ምክንያቱን ካወቅሽው ፤ ችግሩን ከተረዳሽው ነገሩ ቀላል ይሆናል ። እናትና አባትሽን አታውቂያቸውም ፤ እደለም ? ይኽ ደግሞ ምን እንደሚያስከትል ማወቅ አለብሽ ። እናትና አባት እኛ ራሳችንን ለመሆናችን ምስክር ናቸው ። ከየት መጣሁ ? እናትና አባቴ ወለዱኝ ። እውን ይሆናል ነገሩ ። ያ ጥያቄ ላንች ክፍት ቦታ ቢጤ ነው ። እሱን የምትሸሺ መምሰል የለበትም ። ሌላ ሰው ልችሆኝ እንደምትፈልጊ መሆን ነው ያለበት ። ያኔ መንገዱ ቀላል ይሆናል » አለች ፌ ።

ናንሲ ምንም ምን ሳትል ጸጥ ብላ ተቀመጠች ። ይህን ያየችው ፌ በፍቅር ፈገግ ብላ ከተመለከተቻት በኋላ ወደኋላዋ ተለጥጣ ተዝናንታ ተቀመጠች። ክፍሉ ምቾት የሚሰጥና መከፋትን ባንድ ጊዜ ከአዕምሮ ውስጥ እንደሚደመስስ ሆኖ የተዘጋጀ ይመስላል ። የግድግዳው ቀለም ፣ የዕቃዎቹ ዓይነት ፤ የዕቃዎቹ አቀማመጥ፤ ሁሉ ነገር የመንፈስ ሰላም የሚለግስ ነው ።
« እሺ እንግዲህ አሁን ያልኩሽን ቀስ እያልሽ አስቢበት። ለጊዜው ሌላ ነገር አለ ፤ ልንነጋገርበት የሚገባ። የእረፍት ጉዳይ፤ ያመትባል ጉዳይ »
« የመጪው አመትባል ምን እንዲሆን ? »
«ዘመን መለወጫ መምጣቱን ስታስቢ ምን ይሰማሻል ? ይጨንቅሻል ? ፍርሃት ፍርሃት ይልሻል ?››
«አይለኝም»
«ይከፋሻል ? »
‹‹በፍጹም »
«ደግ ናንሲ ። እኔ ከምገምትና ብዙ ከምሳሳት የሚሰማሽን አንች ብትነግሪኝስ ?»
«ምን እንደሚሰማኝ ለማወቅ ነው እምትፈልጊው ?» አለች፡፡
« በእርግጥ ማወቅ ትፈልጊያለሽ ?» ከተቀመጠችበት ተነሥታ እንዴ በክፍሉ ውስጥ በፍጥነት ወዲያ ደርሳ ወዲህ ከተመለሰች በኋላ ፣ «ምን እንደተሰማኝ ልንገርሽ ? » አለች «የተጣልኩ ፤እንደሽንት ተከፍዬ የተደፋሁ ይመስለኛል ፤ ስለዚህ ብሽቅ እላለሁ »
«እንደሽንት ? »
«አዎ ! ሽንቶ የደፋኝ መስሎ ይሰማኛል ፤ አናዶኛል ፤ አበሳጭቶኛል ፤ አብግኖኛል »
«ማን?››
«ማይክል…..


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
308 viewsTsi , 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:28:11 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ አምስት (15)

«ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !»
«አይ ! አይመስለኝም ። ፒተርን እንዳባቴ ነው እማየው። አየሽ እንደማላውቀው አባቴ ። ስጦታ ሲሰጠኝ ሲያሞላቅቀኝ አባቴ ነው እሚመስለኝ ። ፍቅር ከማይክል ጋር ነው»
«እሱንም ስንቆይ እናያለን» አለችና ፌ አሊሰን ሰዓቷን አየች ። «ያምላክ ያለህ |! ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቂያለሽ ? » አለች ። ናንሲ ሰዓቷን አየች ። በጊዜው ያን ያህል መክነፍ በጣም ተደነቀች ። « ፒተር እንዳለው እውነትም የምትገርሚ ልዩ ዓይነት ሰው ነሽ ! ምን አድርገሸ ነው እንዲህ ጊዜውን ያስረሳሽኝ ፌ? እውነትም ልዩ ሰው ነሽ!»
«በመስማማታችን ደስ ይለኛል ። እንዲያውም ፒተር በተወሰነ ጊዜ ዘወትር መገናኘት እንዳለብን ነው የሚያስበው ምን ይመሰልሻል ናንሲ?»
«በጣም ደስ ይለኛል»
«ግን በየጊዜው ይህን ያህል አብረን ልንቆይ እንችላለን ማለት አይቻልም ። ጊዜ ላይኖረን ይችላል ። ስለዚህ በሳምንት ሦስት ቀን ብንገናኝ ምን ይመስልሻል ? በተረፈ ግን እንደጓደኛ በትርፍ ጊዜ መገናኘት ይቻላል። ይስማማሻል? »
«በጣም በጣም ይስማማኛል» ተጨባብጠው እንደተለያዩ ናንሲ ከሁለት ቀን በኋላ ሊገናኙ የወሰዱት ቀጠሮ ሩቅ መስሎ ታያት የራሷ ስሜት ራሷን አስገረማት ።

••••••••••••••

ናንሲ በክፍል ማሞቂያው ምድጃ አጠገብ በሚገኝ ምቹ ወንበረር ላይ ተዝናንታ ተቀመጠችና በረጅሙ እየተነፈሰች ራሷን ወንበሩ የራሰ መከዳ ላይ አሳረፈች ። ከፌ ጋር ባደረጉት ቀጠሮ መስረት፣ ነበር የመጣችው ። የቀጠሮው ሰዓት ገና አምስት ደቂቃ ያህል ቢቀረውም እሷ ግን ከዚያች ሴት ጋር ለመጨዋወት ቸኩላለች ። ወዲያው እሌላኛው ክፍል ውስጥ ቀጭ፣፤ ቋ የሚለው የፌ ኮቴ ተሰማት ። ናንሲ የተቀመጠችው ፌ የአዕምሮ ችግር ያለባቸውን ሰዎች በምታነጋግርበት በምትመረምርበትና ህክምና በምታደርግበት ክፍል ነበር ። የፌን ኮቴ እንደሰማች በደስታ ፈገግ ብላ ትስተካክላ ተቀመጠች ። ሁሉም ነገር ፌ እንደለመደችውና እንደምትፈልገው እንዲሆንላት ለማድረግ አስባበታለች ።
« እንደምን አደርሽ ፤ የንጋት ወፍ ። ይኸ ቀይ ልብስ እንዴት አድርጎ ተስማምቶሻል እባክሽ !» ፌ ይህን ብላ እበሩ ላይ እንደቆመች ፈገግ አለች ። ቀጥላም «ቀዩን ውብ ልብስ እንተወውና እስኪ አዲሱን ፊትሽን አሳይኝ » አለች ። ይህን ብላ ናንሲ ወዳለችበት ቀስ እያለች ተጠጋች ። ከፋሻ የተገለጠውን ፤ ከፊት አጥንቷ በታች የሚገኘውን ጉንጫን ካየች በኋላ እንኳን ደስ አለን የሚል ፈገግታ እፊቷ ላይ ነጋ። አይኖቻቸው ግጥምጥም አሉ ።
« እንዴት ነው ? ጥሩ ነው ? » እለች ናንሲ።
«ናንሲ ፤ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ሆንሽኮ ። ቆንጅዬ… በቃ አለች ፌ። ናንሲ እመነቻት ። ምክንያቱም የፌ ፊት በናንሲ መዳን ደስ መሰኘቷን ፤ በፒተር ስራ መደነቋን ቁልጭ እድርጉ ይናገር ነበር ።

ፌ ደግሞ እንዲያ ስትል ከልቧ ነበር ። ለግላጋ አንገቷ ከቅርጸ መልካም ትከሻዋ ላይ እንደ ባህር ሸንበቆ ተመዞ ፤ ልስልስ ጉንጯ ፤ ገርና ሳሙኝ የሚል አፏ ተገልጦ ያየ ሰው ቢደነቅ የማያስገርም ነገር ሊሆን እይችልም ። ሁሉም ከናንሲ የተፈጥሮ ጠባይ ጋር የሰመረ አካል ሆኖ ታያት ፤ ለፌ ። የፒትር ሁልቆ መስፈርት የሌለው የንድፍና የጥገና ፤ የሞዴል መቅረፅ ሥራ ፤በከንቱ እንዳልነበረ ግልፅ ሆኖ የታያት ፌ

« አስቀናሽን ፣ ዕውነት ቀናሁ ። እኔም እንዳንች ብሆን እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለሽ ! » አለች ። ይህን የሰማችው ናንሲ በሳቅ እየተፍለቀለቀች ወደ ኋላዋ ተለጠጠች ። ከጉንጪ በላይ ያለው ፊቷ ገና በፋሻ እንደታሰረ ሲሆን ፤ ባደረገችው ጥቁር ቡናማ ዘናጭ ባርኔጣ ጥላ ደብዘዝ ብሏል ። ይህን ባርኔጣ የገዛችው ከአሥራ አምስት ቀን በፊት ሲሆን በቀይ ቀሚስ ላይ ከሰበሰችው ቡና ዓይነት ሱፍ ኮትና ካደረገችው ቡናማ ቡት ጫማ ጋር ይሄዳል ። ናንሲ ድሮም ቅርጸ መልካም ልጅ ነች ። አዲሱ ፊቷ ሲጨመር ወንድን ሁሉ በያለበት የምትጥል ሴት ትሆናለች ስትል አሰበች ፤ ፌ ናንሲም ቢሆን ይህ ሊሰማት ጀምሯል ። ፒተር ቃሉን ለመጠበቅ የሚችል ሰው እንደሆነ አምናለችና ።

« ፌ በጣም ደስ ይለኛል ። አንዳንድ ጊዜማ ደስታ የሰራ አካላቴን ውጥር እስኪል ስለሚሞላው ጩሂ ! ጩሂና እፎጥ በይ ይለኛል » አለች ናንሲ።
«እንደሱ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ስላልሺኝ ደስ አለኝ ናንሲ ። ግን ይኽ ሌላ መሆኑስ ? ያልለመድሽው ገፅታ መሆኑስ ፣ ትንሽ አያስጨንቅሽም ?»
« የለም የፈራሁትን ያህል እይደለም ። ግን ሙሉ ፊቴን ስላላየሁት ሙሉውን ሳይ ምን እንደሚሰማኝ እንጃ ብቻ አየሽ ዱሮውንም ያን የአፌን ቅርፅ አልወደውም ነበር ብቻ ሲሆን ይታያል »
«ናንሲ… አንድ ነገር አለ››
« ምን? ምን ነገር»
« አየሽ ናንሲነትሽን ቀስ በቅስ እንድትረሺ ያስፈልጋል ግድ የለበትም ። አንች እንደተቻለሽ ። ስለዚህ ናንሲን ለመርሳት ናንሲን በደንብ ማስታወስ ያሻ ይሆናል ። ለምሳሌ እንበል የዱሮ አካሄድሽን ትወጂው ነበር ? » ይህ ነገር ለናንሲ ፈፅሞ አዲስ ነበር ፤ ተነስቶ ተወሰቶ የማያውቅ ።

« እኔ እንጃ ፣ ስላረማመዴ አስቤ እማውቅ ኢይመስለኝም » አለች ።« ለወያፊቱ በደንብ ታስቢበታለሽ። ድምፅሽን መስማት ትወጂ ነበር ? ለምሳሌ ድምፅሽን ለመገራት የዜማ አለማማጅ ቢቀጠርልሽ ምን ትያለሽ ? አየሽ በጣም ቆንጆ ድምፅ አለሽኮ ። ለምን መሰለሽ እንዲህ እምልሽ ? ከዚህ በፊት ያልሆንሽው ግን ልትሆኝው የምትችይውን ነገር እንድትለማመጅ ብናደርግስ ለማለት ነው ። ያን ስትሆኝ ያው አዲስ ሰው ሆንሽ ማለት ነውኮ ። ፒተር የተቻለውን እያደረገ ነው ። እኛስ ለምን አንሞክርም ? »
329 viewsTsi , 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:45:25 ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዴት እንደተነሳ ሳታውቅ ስለ ማሪዮን ሂልያርድ ታጫውታት ጀመር ። ፌ አሊስን ይህን ሁሉ የምታዳምጣት በጽሞና ነበር ፤ መገረም የለ፤መጨነቅ የለ ። በጽሞና ፤
«እኔንጃ ፤ ብቻ ስናገረው እንኳ ለራሴም እንግዳ መሆኑ ይታወቀኛል ። ግን…» አለችና ንግግሯን መቀጠል ተሳናት። ለምን ? ቂል የሆነች፤ ልጅ የሆነች መስሎ ተሰማት ። እና በጽሞና እምታዳምጠውን አዲስ ጓደኛዋን ቀና ብላ አይታ ለመቀጠል ሞከረች ። «ግን እየሽ እኔ . . . እንዳልኩሽ ያላባትና ያለናት ስላደግኩ» አሁን አፏ ፈታ እያለ ሄደ ። «ምንም ዘመድ አዝማድ የሚባል ነገር ኖሮኝ አያውቅም ነበር ። እናት ወደሚባለው ነገር ቀረብ ልትል የምትችለው ያው የሕፃናት ማሳደጊያው ዋና ነበረች ። አበምኔቷ ። እሷም ያው እንዶ እናት ሳይሆን ምናልባት እንደ ጋለሞታ አክስት ብትቆጠር ነው ። ስለማሪዮን ግን ያው መቼም ማይክልም ፤ ቤን የሚባለው የሱ ጓደኛም ሆነ ብለው ከነገሩኝ ወይም ድንገት ከምሰማው ብዙ ነገር እየሰማሁም ይህ ሁሉ እያለ ፤ ብንገናኝ ትወደኝ ነበር ፤ በተገናኘን ብቻ ! የሚለዉ ጅል ሐሳብ ልበልሽ ቅዝት ወይስ ሕልም ሁልጊዜ ይታየኝ ነበር ። መቼም ቢሆን ፤ ማሪዮንና እኔ ስምም ሆነን እንኖራለን የሚለውን ሐሳብ አምንበት ነበር» ድንገት ዓይኗ ላይ እንባ ግጥም አለ ። ላለማልቀስ እየታገ ለች ፊቷን ወደ ሌላ አዞረች ። «ምናልባትም እናቴ ትሆናለች ፤ ማለት እንደ እናት ትሆነ ኛለች ብለሽ ታስቢ ነበር ?» ናንሲ በአዎንታ ራቧሷን ነቀነቀች ። «እብደት አይደለም ይኸ ታዲያ ? »

«በፍጹም ። በፍጹም እብደት አይደለም ። ያለ ነገር ነው። ያለ እናት አደግሽ ።ማይክልን ወደድሽ ። የማይክልን እናት እንደ እናትሽ ለማየት ፤እናትሽ ለማድረግ ተመኘሽ። ያለ ነው። ምናልባት በዚህ ምክንያት ይሆን ፤ በመጨረሻ በውል መልክ ስትስማሙ በማሪዮን በጣም የተማረርሽባት ፤ አንችንም በጣም የከፋሽ ?»
«አዎ ። አየሽ እንዲያ ባለ ሁኔታ ቃል ስታስገባኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ምን ያህል እንደምትጠላኝ አረጋገጠችልኝ»
«እኔ ደሞ እንዲያ አይመስለኝም ። የሆነ ነገር ያላት ይመስለኛል ። ያ ባይሆን ይህን ሁሉ ነገር አታደርግልሽም ነበር ።ያ ሁሉ ገንዘብ ከፍላ አካልሽ እንዲመለስ ማድረጓ በጣም ስለምትጠላሽ አይመስለኝም» ይህን ሁሉ ምቾት ትተን አለች በልቧ ፌ አሊሰን ። «ግን ውሉን አስቢው። ይህን ሁሉ ያደረገችልኝ እኮ ማይክልን እንድተውላት ነው ። ከማይክል ጋር ግንኙነት ብፈጥር… እኔ ፈልጌ ዉሉ ሙሉ በሙሉ ይፈርሳል፡፡ ተቀብለሽ ከሱም ፊት ከኔም ፊት ጥፊ እንደማለት ነዉ ያኔ ስታነጋግረኝ ገባኝ ። ማሪዮን መቼም ቢሆን ልትቀበለኝ አትፈልግም ፤ ብዬ አሰብኩ ። ይህ ሐሳብ እንደተሰማኝ የሆንኩትን ልነግርሽ አልችልም ። በሕይወቴ ውስጥ ካጋጠሙኝ አስከፊ ነገሮች አንዱ ነበር» ይህን ብላ በረጅሙ ተነፈሰች ። እንደገና መናገር ስትጀምር ድምጺ ለስለስ ብሎ ነበር ። «ግን ችግርም ፣ ስቃይም መከፋትም ለኔ ኦዲስ አይደሉም ። ደጋግመው ደርሰውብኝ ደጋግሜ አሳልፌአቸዋለሁ»

«ወላጆችሽ ሲሞቱ ነፍስ ታውቂ ነበር ?»
«ይህን ያህል የጐላ ትዝታ የለኝም» የምታስታውሰውን ያህል ነገረቻት ። ቀጥላም ፤ «ትዝ የሚለኝ የሚመስለኝ ምናልባት ብቻን መቅረት አለ አይደል እንደዚያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር መሰለኝ» አለች ። «ልክ አሁን እንደሚሰማሽ ዓይነት ስሜት?» ግምት ነበር ። ቢሆንም ባዶ ግምትም አልነበረም። «ምናልባት ሳይሆን አይቀርም ። የት እገባ ብሎ ማሰብ ። ልክ ሳይሆን አይቀርም ። ከዚህ በኋላ የት ነው እምገባ ? ማነው አይዞሽ የሚለኝ ? የሚል ስጋት ። አሁንም አልፎ አልፎ የዚህ ዓይነት ስሜት ይሰማኛል» «ምናልባት ማይክል ? ማይክል ይፈልገኛል ፤ አይጥለኝም ብለሽ ትገግምቻልሽ ? »
«አዎ ፡፤ አንዳንዴ እንደሱ አስባለሁ። የለም አንዳንዴ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ።»
«በሌላ ጊዜስ ? ማለት ሁሌም አላልሽም»
«እሁን አሁን መጠራጠር ጀምሬአለሁ ። በፈት በፊት አየሽ ሳይመጣ ሲቀር ጊዜ ፊቴን ማየት ፈርቶ ነው ፤ ተሳቆ ነው እል ነበር ። አሁን አሁን ግን ስለሕክምናው ያውቃል ። ስለዚህ ምን ደረሰች ፤ እንዴት ነው ብሎ መጠየቅ ነበረበት ። ታዲያ እንዴት እንዲህ እልም ሊል በቃ ? እላለሁ»
«የግምት መልስ ሰጥተሽዋል ለጥያቄሽ ? »
«አዎ ። ግን በቂ መልስ የምትይው አይደለም ። አንዳንዴ ማሪዮን ያሳመነችው ይመስለኛል ። የሱ ዓይነቱን መልካም ስም ከሌለው ቤተሰብ የወጣች ሴት ጋር ማጋባት ለሙያህ ደግ አይደለም ብላ አሳምናው ይሆን እላለሁ ። ማሪዮን ቀላል ሰው እንዳትመስልሽ !»
«እሱ እንዲህ ዓይነቱን ሐሳብ ይቀበላል ትያለሽ ? »
«በፊት እንኳ ርግጠኛ ነኝ አይቀበልም ። አያምንበትም ፤ ነበር ... አሁን ግን እንጃ፤ምን ይታወቃል?»
«ሌላ ቢያገባ... ቢተውሽ ምን ያህል የምትጐጂ ይመስልሻል?» ናንሲ ኩምትር ስትል ታየች ። መልስ አልሰጠችም ። ግን መላ አካሏ መልሱን ሰጥቷል ። «የሆንሽውን ሲሰማ ደንግጦ ወይም እንዲያ ሆና ላያት አልፈልግም ብሎ እንደሆነስ ያልመጣው ? አየሽ ናንሲ ፤ አንዳንድ ወንዶች እኛ የምንፈልገውን ያህል ጠንካሮች አይደሉም»
« ይሆን ይሆናል »
«ታዲያ. . . በኋላ ከዳንሽ ከተስተካከልሽ በኋላ ቢመጣ ቅር አትሰኝበትም ?››
«ምናልባት ቅር ይለኝ ይሆናል ። ምኑም ግልጽ ሆኖ አይታወቀኝም ። አስባለሁ ፤ አስባለሁ ። ግን መልስ የለም»
«መልሱን መፈለግም አያሻም ። መቆየት ይመልሰዋል ጊዜ ይመልሰዋል ። ዋናው ነገር ግን ስሜትሽን መሸሽ የለብሽም ። ስሜትሽን በትክክል ለመረዳት መሞከር አለብሽ በቂ ነው ።ለመሆኑ ስላንቺ የሚሰማሽ ምንድነው ? ማለት ፊትሽ እንግዳ ነው እንግዳ ነሽ ለራስሽም ። ይህን ስታስቢ ትቅበጠበጫለሽ ? ትፈሪያለሽ ? ትደሰቻለሽ ? ትናደጃለሽ ?»

«ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ» አለች ። ሁለቱም ሳቁ «ግን አብዛኛውን ጊዜ በጣም እፈራለሁ ፤ እጨነቃለሁ ። አብሮ የኖረ ነነር ቀላል አይደለም ። ሀያ ሁለት ዓመት ሙሉ እኔ ያልኩት ሌላ ሲሆን አስቢው ፤ አያበሳጭም ብለሽ ነው?»
«እንዲያ ዓይነት ስሜት ተሰምቶሽ ያውቃል?»
«አንዳንዴ. . . ግን አብዛኛውን ጊዜ ደፍሬ አላስብም ስለዚህ ጉዳይ»
«ብዙ ጊዜ እምታስቢው ስለምንድነው ?››
«እውነት ንገሪኝ ነው እምትይኝ ? »
«አዎና»
‹‹ማይክልን ። አንዳንድ ጊዜ ፒተር በሐሳቤ ይገባል ። አብዛኛውን ጊዜ ግን ስለማይክል ነው እማስበው»
«ፒተርን ማፍቀር እየጀመርሽ ይመስልሻል !»

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
710 viewsTsi , 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:45:25 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ አራት (14)

ይህን ሐሳብ ግን ልትገፋበት አልደፈረችም ። ይህ ሀሳብ በፊቷ ላይ ሲዳምን ፒተር አይቷል ። ብዙ ጊዜ ይጠብቀዋል ። እንድ የተጐዳችበት ነገር . . . ያለፈ ሕይወቷ ቁስል...
ቢሆንም በጊዜ ብዛት ልትረሳው ትችላለች ተስፋ ያደርጋል።
«ፊልምስ ? ፊልም አላመጣሀልኝም ? »
«አምጥቻለሁ እንጄ !» አለና አነስ ያለች አራት ማዕዘን ጥቅል እየወረወረላት ፤ «ካሜራ አምጥቼ ፊልም ልርሳ ?» ሲል ጠየቃት ። «አንተ !! አንተ ምንም አትረሳ !» አለችና መጣደፍ ጀመረች ፤ ካሜራውን ፊልም ለመሙላት ። ወዲያው በተለያዩ አቅጣጫዎች ፤ በተለያየ መንገድ ጠቅ ጠቅ ፤ጠቅ ፎቶ ታነሳው ጀመር ። ይህን እያደረገች እያለ አነስ ያለ ቁጥር ያላቸው ወፎች ባጠገባቸው ሲበሩ ቶሎ ብላ አነሳቻቸው ። «ምናልባት ደህና ፎቶ ላይወጣ ይችላል ። ግን ለመነሻ ምንም አይልም» አለች ። እሱ ግን በጽሞና ይመለከታት ነበር ። ለረጅም ጊዜ በዚህ ሁኔታ ሲያጤናት ከቆየ በኋላ ብድግ ብሎ አጠገቧ ቆመና እጁን ጣል አደረገው እትከሻዋ ላይ ። ከዚያም «ናንሲ ዛሬ ላበረክትልሽ ያቀድኩት ሌላም ስጦታ አለኝ» አላት ። «ገባኝ አወቅኩት ፤ መርሰድስ ነው አይደል?» «የለም ናንሲ ፤ አሁን እውነቴን ነው» አለና በለስላሳ የጽሞና ፈገግታ ተመለከታት ፤ ካንዲት ጓደኛዬ ጋር ላስተዋውቅሽ እፈልጋለሁ ፤ የሁለታችንም ጓደኛ እንድትሆን ። ለየት ያለች እመቤት ነች»

አንዳንድ ቅጽበት አለች ። የምናስበውን በቅጡ መረዳ? የማንችልባት ። በዚያች ዓይነቲቱ ቅጽበት ናንሲን የሆነ ቅናት መላ አካሏን ሲወርራት ተሰማት ። ቢሆንም ከፒተር ሁኔታ/ ስሜት ሊሰማት እንደማይገባ ተረዳች ። «ፌ ትባላለች» አለ ፒተር ። «ሕክምና ያጠናነው ባንድ ነው ። ባሁኑ ጊዜ ፌ አሊሰን በምእራብ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙት ሳይኪያችሪሰቶች አንዷ ናት ።ምናልባትም በሀገሪቱ ሉ ከሚባሉት ታላላቅ የአዕምሮ ሐኪሞች አንዷ ልትሆንም ትችላለች ። በጓደኝነት መልክ ከሆነ ደግሞ ጓደኛ ሳይሆን ሁሉን ነገር የማለት ያህል ናት ።እንደምትወጂያት ተስፋ አለኝ ።»
«እና ?» አለች ናንሊ በመንፈሷ ውጥረትና የማወቅ ጉጉት ይታይባታል ።
«እናማ ብትተዋወቁ... ብታነጋግሪያት ደህና ይመስለኛል ። ማለት ነገሩን ከዚህ በፊት በመጠኑ ይሁን እንጂ ተነጋግረንበታል»
«ትንሽ የተዛባ ፤ ማለቴ መንፈሴ በቅጡ የተረጋጋ መስሎ አልታየህም ማለት ነው? » የመከፋት ድምጽ ነበር ። ይህን ስትጠይቀው ካሜራውን ወደ ጐን ቁጭ አደረገች ።
«አላልኩም ናንሲ ፤ በሁሉም በኩል ምንም እንከን የለብሽም ። ከቀን ወደ ቀን እየተረጋጋሽ ፤ ከቀን ወደ ቀን አዲስ እየሆንሽ እንደምትሄጂ አትጠራጠሪ ። ግን ደግሞ አስቢው ። ሌላው ቢቀር የሚያዋራሽ ፤ ከኔ ሌላ ሰው ያስፈልግሻል ። እኔ ፤ ሊሊና ግሬችን ብቻ በቂ አይደለንም ። ሌላ ሰው ያስፈልግሻል ወይስ አያስፈልግሽም ? » አለ ። መልሱን በልቧ ሰጠች ። አዎ አለች በልቧ ፤ያስፈልገኛል ። ያም ሌላ ሰው ማይክል፤ እሱ ብቻ ነው ።

«እንጃ ርግጠኛ አይደለሁም ። አስቤው አላውቅም» አለችው፡፡ «ከፌ ጋር ከተዋወቃችሁ በኋላ ለካ ታስፈልገኝ ኖሯል እንደምትይ ርግጠኛ ነኝ ። በጣም ደግና ሰው ወዳድ ፍጡር ናት። በዚያም ላይ ስላንቺ ሁልጊዜ ትጠይቀኛለች»
«ታውቃለች ማለት ነው? »
«ገና ነገሩ ሲወጠን ጀምሮ !» አለ ። ይህን ያለውም ናንሲን ለማግባባት አልነበረም ። እውነቱን ነበር ። ዶክተር ዊክፊልድና ማሪዮን ሂልያርድ ደውለው ያነጋገሩት ዕለት ፌ አሊሰን አብራው ነበረች ። ምክንያቱም ምንም እንኳ ናንሲ ይህን ማወቅ ባይኖርባት ፤ ፒተር ግራግሰንና ፌ አሊሰን በአካልም ግንኙነት አላቸው ። እንደ ፍቅረኞችም ናችው ጉዳዩ ግን በጣም የጠነከረ አልነበረም ። ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ያደርጉታል ። ከሱ ይልቅ ጓደኝነታቸው የጠነከረ ነው ። «ዛሬ ከቀትር በኋላ እመጣለሁ ብላኛለች ። ቡና እየጠጣን እንጫወታለን ። እንዴት ነው ! ቅር ይልሻል ?»
«አይ ቅር አይለኝም» አለች ፤ ምክንያቱም ቅር ይለኛል ብትልም ዋጋ አልነበረውም ። ያለቀለት ጉዳይ ነው ። ከዚያ በኋላ የወትሮዋ ናንሲን መሆን አልቻለችም ። ሁሉ ነገሯ ቁጥብ ሆነ ። የለም የሌላ ሰው በሷና በፒተር መካከል መገባት ምንም ደስታ ሊሰጣት አልቻለም ። ሦስተኛ ጓደኛ... ለዚያውም ሴት ፤ አልመስልሽም አላት ። የውድድርና የእምነት ማጣት ስሜት ዋጣት ።

ይህም የሆነው ከፌ ጋር እስኪተዋወቁ ፤ ፌን እስክታያት ነበር ። ፌ አሊሰን በተባለው ሰዓት መጣች ። አየቻት። ረጅም ፤ ቀጭን ፤ ነጣ ያለ ወርቅማ ፀጉር ያላት አጥንተ ሰፊ ሴት ነበረች ። ሆኖም ፊቷ ምንም ዓይነት ጭካኔ ወይም ክፋት አይታይበትም ። ይህም ሁሉ ሆኖ የናንሲ ልብ አላመነም። ጨዋታ ሲጀመር ፌ በቀላሉ ቀጠለች። ዓይኖቿ ሕያው ሲሆኑ ፈጥኖ የመገንዘብ ችሎታም ይታይባታል ። ቀልድ ሲመጣ ሰም ቀለድ ፤ ሲጠይቋት ለመመለስ ፤ የሳቅ ሰዓት ሲሆን ደግሞ ከት ብላ ለመሳቅ ተዘጋጅታ የምትጠብቅ ትመስላለች ። ልብ ብሎ ያያት ሰው ለቁምነገርና ጨዋታም ዝግጁ መሆኗን ሊገነዘብ ይችላል ። በቂ ቃላት ከተለዋወጡ በኋላ ፒተር ሹልክ ብሎ ወጣ ሁለቱ ይበልጥ እንዲጫወቱ ብቻቸውን እንዲሆኑ ። ያኔ ናንሲ ደስ ተሰኘች ። ከልብ ደስ ተሰኘች ።

ፌና ናንሲ ስለብዙ ነገር አወሩ ። ሺህ ጉዳዮችን አነሱ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን በናንሲ ላይ ስለደረሰው አደጋ አላነሱም፡፡ ወዲያው ፌ ስላሳለፈቻቸው ነግሮች ቀስ እያለች ታጫውታት ጀመር ። ቁርጥራጭ አጋጣሚዎችን ከሕይወቷ ውጥንቅጥ እየመዘዘች ነገረቻት ። ናንሲም ሳታስበው ከሕይወቷ አካል ትንሽ ገለጥ እያደረገች በጨረፍታ አሳየቻት ። እየቆየች ከዚያ በፊት በተለይም ከማይክል ጋር ከመገናኘቷ በፊት ለማንም ሰው ነግራ የማታውቃቸውን ነገሮች ሁሉ ነገረቻት ። ስለ እጓለማውታን ማሳደጊያው አወጋቻት ። ይህም ለፒተር በነገረችው መንገድ ሳይሆን ፤ ማለት በቀልድ ሳይሆን የምር ይሰማት የነበረውን ትዘከዝክላት ጀመር ። ብቸኝነቱን ፤ ማን ነኝ ? ከየት መጣሁ ? ብላ ትጠይቀው የነበረውን ፤ ማን ለምን እዚያ ወስዶ ከተተኝ ? ትል የነበረውን ሁሉ ።
661 viewsTsi , 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:25:16 አንድ ከበድ ያለና የተጠቀለለ አራት ማዕዘን ነገር ይዞ መጣ ። ገና ስታየው መፈንደቋ ጨመረ ። ምን ይሆን ? ትልቅ ነገር መሆን አለበት ። ጭኗ ላይ አስቀመጠላት ። ልክ ነው የገመትኩት ፡ ልክ ነው ! ስትል አሰበች ። «ምንድነው ፒተር ? የሆነ እንደ ድንጋይ የሚከብድ ነገር» አለች ። «እንደ ድንጋይ አልሺኝ ? አልተሳሳትሽም ። በየሱቁ ዞሬ በገበያ ላይ ያገኘሁትን የመጨረሻውን ትልቅ የከበረ ድንጋይ ነው ገዝቼ ያመጣሁልሽ» አላት ። ይህን ነበር የገመተችው ። ፈታችው ። ከገመተችው ፤ ካሰበችው ውጭ ነበር የዛሬው ስጦታ ።« ሆኖም ልክ ነው።ካሰበችውም የሚበልጥ ታላቅ ስጦታ ሆኖ አገኘችው ። «ፒተር ! አምላኬ ፤ ምን ዓይነት ስጦታ ነው ይሄ ? በፍጹም ልቀበልህ አል...»
« ትችያለሽ እንጂ ! መቀበል አለብሽ ። ሆኖም ይሀን ስጦታ በነፃ ልሰጥሽ አልፈልግም ። ብዙ ስራ ፤ ቆንጆ ሥራ ሠርተሽ እንድታሳይኝ እፈልጋለሁ » ካሜራ ነበር ስጦታው ። ፤ ይህ ደግሞ ቀላል ነገር አልነበረም ። ፒተር ይህን ስጦታ ብዙ አስቦበት ፤አውጥቶ አውርዶ ነበር የገዛው። ምክንያቱ ለፒተርም ለናንሲም ግልጽ ነው ። ። እንግዲህ ናንሲ የስዕል ሥራዋን እንደገና ለመጀመር ሐሳቧ እምቢ እንዳላት ሁለቱም ያውቃሉ ። ሥዕል ሞክሪ ስትባል በመጀመሪያ በእጅዋ ስታመካኝ ቆየች ። አሁን የእጅዋ ሕክምና ሲያልቅና ሲፈታ ምን ምክንያት ልትፈጥር ትችላለች ? ለናንሲ ይህ ጭንቅ ነበር ። ለፒተር ደግሞ መፍትሔ የሚፈለግለት ጉዳይ ነበር ። መፍትሔ ይኸው ካሜራ ። ሥዕል ለመሳል ስላልፈለገች ፤ ነርሶች ያመጡአቸው የዱሮ ሥዕሎቿ እንኳ ለጉዞ እንደተቀረቀቡ ናቸው ። ልታያቸው አልፈለገችም ። አሁን በቃ ። ፎቶግራፍ ታነሳለች ።

«በነገራችን ላይ ካሜራው መመሪያ አለው ። እኔ ላነበው ብሞክር ምኑም አልገባህ አለኝ ። ከዚህ ካሜራ አሠራር ይልቅ የሕክምና ሙያ ትምህርት ቀለል ሳይል አይቀርም ። ላንቺ ግን ይገባሻል ብዬ ነው » አለና ሰጣት ። ተቀበለችውና ገልበጥ ገልበጥ አደረገችው። ላንድ ካሜራ ይህን ያህል መመሪያ ! ካሜራው በጣም የተራቀቀ መሆን አለበት። ገልበጥ ፤ ገልበጥ ። ትንሽ አነበበች ። ተመሰጠች ። በኋላ ማስረዳት ቀጠለትች ካሜራውን ይዛ ። «አየህ… እየው ፤ እዚህ ላይ ጠቅ ስታደርገው. . . ይታይሃል ? » እያለች ፤ «ይህን ስተነካው ደሞ...» እያለች ። «ታዲያ ይህ ስጦታ በሕይወቴ ከተሰጡኝ ስጦታዎች ሁሉ የላቀና ያማረ ነው» አለች ። ሆኖም ማይክል እባዛሩ ላይ አሸንፎ ከሰጠኝ ያንገት ጌጥ ሌላ ብላ በልቧ ጨመረች ። ይህን ሐሳብ ግን ልትገፋበት አልደፈረችም ። ይህ ሀሳብ በፊቷ ላይ ሲዳምን ፒተር አይቷል ። ብዙ ጊዜ ይጠብቀዋል ። እንድ የተጐዳችበት ነገር . . . ያለፈ ሕይወቷ ቁስል...

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
826 viewsTsiyon Beyene, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:25:15 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ሶስት (13)

"ማይክ ፣ ለመሆኑ በቅርብ ጊዜ ፊትህን በመስታወት አይተኸው ታውቃለህ ? ማስፈራሪያ መስለሃልኮ! ማይክ እባክህ እምቢ አትበል። አንድ ነገር ልለምንህ››
«ምን?»
«እምቢ አትበል››
«እኮ ጠይቀኝ››
«በዚህ በመጭው እሁድ ቅዳሜ አንድ ቦታ ሄደን እናሳልፍ።» ሁሉም ፤ጓደኞቻችን ሁሉ ይምጣ ብለዋል። » ቤን ይሀንን ያለው ከልቡ ነበር። ይህ ደግሞ ለማይክል በደንብ ገብቶታል። ሆኖም አራሱን በአሉታ ነቀነቀ። «ቤን ደስ ይለኝ ነበር ። እውነት! ግን ይኸው እንደምታየው ነው ስራው፤ በተለይ የካንሳስ ሲቲ የገበያ ማእከል ጉዳይ። ሌላም አለ። ምን ዋጋ አለው ብለህ ነው። ምንም መልስ የማይገኝለት አርባ ሰባት ጥያቄ ሆነኮ። ትናንት ስብሰባው ላይ አንተስ ነበርክ አይደለምንዴ «እኔም ብቻ ሳልሆን ሌሎች ሃያ ሶስት ሰዎችም ነበሩ ። ታዲያ ያ ሁሉ ሰው እያለ አንተ ብቻህን ምን በወጣህ ነው ማይክ ? እስኪ አስበው! ትንሽ ማረፍ የለብህም እንዴ። ቢንስ ላንድ ዊክ ኤንድ! ወይስ ስራዬን ማንም እንዲነካብኝ አልፈልግም ባይ ነህ ?»

ይህ የመጨረሻው አረፍተ ነገር እውነት እንዳልሆነ ቤንም ይገባዋል። ያ ሳይሆን ሥራ ለማይክል መሸሻ መሸሸጊያው ስለሆነ ነበር። ሥራ ማደንዘዣው ፤ ከሀሳብ መገላገያ መድሀኒቱ በመሆኑ ነበር። «እባክህን እሺ በለኝ ማይክ። ያሁኑን ብቻ ። ላንድ ጊዜ ብቻ››
«አልችልም ስለማልችልኮ ነው። ወድጄ አይደለም፤ ቤን»
«ሥራ!» አለ ቤን በጩኸት «ሥራ!... እንዲህ ከሆነ አፈር ድሜ ይጋጥ ፤ ፊትህን በመስታወት እየው አልኩህ !ከዚህ የበለጠ ምን እንድልህ ትፈልጋለህ ? ! ሌት ተቀን ሥራ ሥራ እያልክ ከሰውነት ጎዳና ወጣህ አልኩህ ። ከዚህ የበለጠ ምን እንድልህ ትፈልጋለህ ? ማይክ ስነግርህ ለምን አትሰማኝም? ይኽኮ ታንቆ የመሞት ያህል ነው። ለምኑ ነው እንዲህ እምትሆነው ? ሥራ ትላለህ እንጂ ደሞ እውነቱን ሁላችንም እናውቃለን። ይመን አይመን ሴላ ነው። ይሁን እንጂ ሁሉም ሰው ያውቀዋል ።»

ትንፋሹን ውጦ በኃይል ከተነፈሰ በኋላ እንደገና በሀይለ ቃል ቀጠለ ። «ማይክ ትወዳት ነበር ፤ አውቃለሁ ። እኔም ላስባት እንኳ አልፈልግም እንኳን አንተ ። ግን አስበው ። እሷ አንዴ ቀረች፤ አንዴ አለፈች። ምንም ማድረግ አይቻልም ። አንተ ግን አለህ ይኸው ! በሕይወት አለህ ። ጤናማ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ! ታዲያ የተረፈውን ሕይወትህን እንዲሁ ልታስቀረው ትፈልጋለህ ? አመድ ልትነሰንስበት ትሻለህ እንደ እናትህ ሥራ ሥራ እያልክ ፤ ለፈጠርከው የገንዘብ መንግሥት ፤ወይም ለተቀበልከው ስውር መንግሥት አገልጋይ ሆነህ ልትቀር ብቻ ትፈልጋለህ ? አይገባኝም ፤ ማይክ ። አልቀበልህም ። ይህ አካልህ ያው ይምሰል እንጂ እማውቅህ እምወድህ ሰው አይደለሀም ። የማውቀውን ፤ የምወደውን ሰው ሌላ የማላውቀው ሰው ድቡሽት ሲጭንበት እያየሁ ነው።ይህን ደግሞ አልቀበለውም ። ወጣ በል። ለመኖር ሞክር። ከዚህ ከቅርብ እንጀምር ። ከቆንጆ ፀሐፊህ ጋር ውጣ ። ወይም በየፓርቲው በቀን መአት ቆነጃጅት ማግኘት ይቻላል ። ወይም... »

« ውጣ!» አለ ማይክ ከጣራ በላይ ጮሆ አቋርጦት «ውጣልኝ ቤን! . . . ከቢሮዬ ውጣልኝ ። ሳላንቅህ ፤ ሳልገልህ ውጣልኝ !» ከመቀመጫው ተነስቶ ፤ጣቶቹን ለማነቅ አንጨፍርሮ በጠረጴዛው ላይ ሰውነቱን አስግጎ ነበር እንዲህ ያለው ። ጩኸቱ የቆሰለ አንበሳ ጩኸት ነበር ። ለቅጽበት ያህል ሁለቱም ጓደኞች ተፋጠው እያሉ በያሉበት ቆመው ቀሩ ። ሁለ ቱም ስለተናገሩት ነገር ፤ በመካከላቸው ስለተፈጠረው ሁኔታ ሲያሰቡ ደንግጠው ፈርተው ነበር ። «ኦ ይቅርታ አድርግልኝ ቤን » አለና ተቀመጠ ። እና ራሱን በእጆቹ ደግፎ አቀረቀረ ። እዚያው እንዳቀረቀረ ቆይቶ ቀና ሳይል ፣ «ለምን አንተወውም ። ይለፍ ሌላ ቀን» አለ ማይክ ። ቤን አቭሪ ቃል አልተነፈሰም ። ቀስ ብሎ የቢሮውን በር ከፍቶ ወጣ ። ሲወጣ እንኳ ማይክ ቀና ብሎ ሊያየው አልቻለም ። በሩን ዘግቶ ሔደ ቤን። ሌላ የሚባል የሚጨመር ነገር አልነበረምና ምን ምን ሊል አልቻለም ።

ያን ለት ቤን አቭሪ ከቢሮው የወጣው በሥራ ሰዓት ላይ አንድ ሰዓት ተኩል ጨምሮ ነበር ። ከምሽቱ አሥራ ሁለት ተኩል ላይ ከቢሮው ሲወጣ የማይክል ቢሮ መብራት እንደበራ ነበር። ገና እስከምሽቱ አምስት ሰዓት ድረስ ያ መብራት እንደማይጠፋ ቤን ተገነዘበ ። እውነት አለው ። የት ይሂድ ? ወደቤቱ እሚሔድበት ምን ምክንያትስ አለው ? ከሶስት ወር በፊት ማይክል የተከራየው አፓርትማ ባዶ ነው። ሁለት ታጣፊ ወንበሮች ፡ ፡ አንድ አልጋ ሌላ ምንም ዕቃ የለበትም ። ቤን ያ አፓርታማ በሆነ መንገድ የናንሲን የቦስተን አፓርትማ እንደሚመስል ተገንዝቧል ። ማይክም ይህን ሳያይ አይቀርም ። ምናልባትም የተከራየው ያን ስላየ ይሆናል ። ግን ዋጋ የለውም ። ቤቱ ቤት ሊመስለው አልቻለም ። ኑሮው ኑሮ ሊሆንለት አልቻለም ። ስለዚህም እሥራው ላይ ተደፍቶ መዋል ፤ ማምሸት አመጣ ። እንደ እብደት ሥራ ሥራ ሥራ አለ ። ካልደከመው እንቅልፍ ሊወስደው ስለማይችል ይሆናል ።

ይህ ነገር ቤንን ደስ ሊያሰኘው አይችልም ። ሆኖም እሱም ሆነ ሌላ ሰው ምንም ማድረግ አይችልም ። ማንም ሰው ማይክልን ሊያድነው ፤ ከገባበት ማጥ ጎትቶ ሊያወጣው አይችልም ። ያለ አንድ ሰው በስተቀር ። ያለ ናንሲ በስተቀር። ናንሲ ደግሞ የለችም ። ናንሲ ደግሞ ቀርታለች ። ሞታለች ። ቤን ስለናንሲ ሲያስብ መላ አካሉን ስቅቅ አለው ። ሆዱን አመመው ። ቢሆንም የሱ የአካልም ሆነ የመንፈስ ቁስል እየሻረለት ነበር ። ወጣት ነውና እየሻረለት ነበር ። ምነው የማይክልም ቁስል እንደሱ ቁስል ቢሽር? ነገር ግን የማይከል ስብራት ድርብ ነው ፤ የነፍስና የሥጋ ሥብራት

«እሺ ወጣቷ እመቤት ? እንዴት ነው ቃሌን የምጠብቅ ሰው ነኝ ወይስ አይደለሁም ? ቤቱ እንዴት ነው ? ውበትን ለማሳየት ታቅዶ የተሠራ አይመስልሽም ?» አለ ፒተር ግሬግስን ግሬግሰን ይህን የሚለው ለናንሲ በተከራየላት አፓርታማ መናፈሻ ሰገነት ላይ ተቀምጠው የአካባቢውን ትዕይንት በማየት ላይ እንዳሉ ነበር ። ይህን ሲል መለስ ብላ አየችው። እሱም አያት በመተያየት ሐሳባቸውን ተለዋወጡ ። የናንሲ ፊት አሁንም በፋሻ እንደተጠቀለለ ሲሆን ዓይኖቿ እፋሻው መሐል በደስታ ሲጨፋፍሩ ይታያሉ። የእጅዋ ላይ ፋሻ ተፊትቷል ምንም እንኳ የከዚህ በፊቱ እጆቿን ባይመስሉም ውብ ነበሩ ። አፓርትመንቱ ፤ እመናፈሻ ሰገነቱ ላይ ሆኖ ማታ የፀሐይን መጥለቅ ፤ ጥዋት የፀሐይን መውጣት ለማየት እንዲያመች ሆኖ የተሠራ ሲሆን ይህ ደግሞ ለናንሲ ወሰን የሌለው ደስታን ሰጥ ቷት ነበር ። ፒተር እንደፎከረው ከሁሉም የተሻለውን አፖርታማ አገኘላት ። ይህን ስታስብ «ታውቃለህ ፒተር፣ አንዳንዴ እንደኛየን ሙልቅቅ አልኩኮ እያልኩ አስባለሁ» አለች ።

«ሲያንስሽ ነው ። ይልቅስ? አንድ ነገር አስታወስሺኝ ።. አንድ ዕቃ አምጥቼልሻለሁ» አለ ፒተር ገና ዕቃ እንዳመጣላት ሲናገር እንደሕፃን ልጅ መፈንጠዝ ጀመረች ፒተር አየት አድርጓት ፊቱ በደስታ እንደበራ ወደ ቤት ገባ ። ናንሲ ስለፒተር አሰበች ። ደግ ሰው ነው ። ትወደዋለች ምን ጊዜም ቢሆን የሚያስደስታትን ነገር ሲያድን የሚውል ይመስላታል ። የማይሰጣት ስጦታ የለም። እንደልጅ ያጫውታታል የመጽሔት ክምር ፤ የመጸሕፍት ቁልል ፤ አስቂኝ አሠራር ያለው ባርኔጣ ፤ ወደር የሌለው ያንገት ልብስ ያበረክትላታል ። እጆቿን ጠግኖ ፋሻውን ሲፈታ ላዲሱ እጅዋ መመረቂያ የሚያማምሩ አምባሮች ሰጣት ።
774 viewsTsiyon Beyene, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:55:53 «እቢሮ ጠረጴዛህ ላይ ስጦታ ቢጤ አስቀምጩልሀለሁ» ስትለው፤ « አስፈላጊ አልነበረም » አለ ። ከልቡ ነበር ። ካሁን በኋላ ለሱ ምንም ምን ነገር አያስፈልገውም ። ልቡን ሊያፈካ የሚችል ምንም ዓይነት ስጦታ አይኖርም ። ቤን ይህን ተረድቶለታል ። ስለዚህም የልደት ስጦታ አልገዛለትም ። «ለኔ የልደት ቀንሀ ነው ማይክል። የሆነውም ቢሆን ላንተ የተወለድክበት ቀን ልዩ መሆኑን አትዘንጋ። በል መሥሪያ ቤት እንገናኝ » ብላ ወጣች ።

እናቱ ወደ ሥራ ከሔደች በኋላ እዚያው ምግብ ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ቆየ ። የውጭውን ትዕይንት እየተመለከተ

የሱ መኖሪያ ሌላ ነው ። መኖሪያውን በሚገባ ያውቀዋል ግን ያ አፓርታማ የሚገኘው ቦስተን ውስጥ ነው። ቢሆንም የተቻለውን ያህል ይፈልጋል ተመሳሳዩን እስኪያገኝ ። ዛሬም ልቡ አላመነም ። ዛሬም ተስፋ ያደርጋል ። ምንም እንኳ ከንቱ ተስፋ የሞኝ ተስፋ ቢሆንም ውስጡ ግን አልቆረጠም ።

«ሃይ፤ ሱ! ሚስተር ሄልያርድ አለ›› ቤን እቭሪ እማይክል ቢሮ ሲገባ ደስ ብሎት ነበር። አሰልቺው የስራ ሰዓት ወደ መገባደዱ ትቃርቦ ስለነበር ደስ ብሎታል ። ቀኑን በሙሉ ወዲያ ወዲህ ሲዋከብ ነው የሚውለው ። ማረፍ ቀርቶ ቂጡ መሬት ሊነካ የሚችልበት ጊዜ የለውም ። «አዎ ፣ ልታነጋግረው እንደምትፈልግ ልንገረው ? » አለች ሱ ፈግግ እያለች ።

በአለባበስ የተሸፈነው መልካም ቅርጽ አይኑን ሳበው። ማሪዮን ሂሊያርድ ሽቅርቅር ነኝ ባይ ፀሐፊዎችን አትቀበልም ፤ ለሌላ ሠራትኛ ቀርቶ ለልጅዋ እንኳን አለ በሃሳቡ ። ቀጥሎም ወይስ በተለይ ለልጅዋ ይሆን? ቤን ይህን ኢያሰበ «ልንገረው ?» ላለችው እንገቱን በአሉታ እየነቀነቀ «የለም ። አንችን ማድከምም አያስፈልግም ። እኔው ዝም ብዬ እገባለሁ» አላት ። የማይክልን ቢሮ በር አንኳኳ ። «እዚህ ቤት ! ሰው የለም ?» አለ እንደቀልድ ። ምንም መልስ አልነበረም ። እንደገና አንኳኳ ። አሁንም መልስ እልነበረም ።«ርግጠኛ ነሽ… ውስጥ አለ » እለ ቤን ፀሐፊዋን ዞር ብሎ እየተመለከተ ።
«እርግጠኛ ነኝ» ፤
«ነው?» አለና እንደገና አንኳኳ ። በዚህ ጊዜ የሻከረ ድምፅ «ይግቡ» አለ ከውሰጥ ። ቤን በሩን ቆስ ብሎ ገፋ አድርጐ ገባ ።
«ምን ሆንክ ? ተኝተህ ነበር ወይስ ምን ? » ማይክል ቀና ብሎ እየውና ፣ «ያማ መታደል ነበር ። መተኛት ፅድቅ አይደለም እንዴ እስቲ ይኽን ጉድ ተመልከትልኝ» አለ ። ጠረጴዛው ላይ የተከመረው ፋይል ብዛት መጠን አልነበረውም ። ያን ሁሉ ስራ የተመለከተው ቤን በልቡ ይህን ስራ ለማጠናቀቅ አስር ሰዎች ዓመት ይፈጅባቸዋል ሲል አሰበ። «ተቀመጣ ፤ ቤን» አለ ማይክል ።
«እሺ አመሰግናለሁ ፤ አለቃዬ» አለ ቤን ። ሁሌም እንደዚህ እያለ ያሾፍበታል ።
«ዝጋ እንግዲህ ! ደሞ ምንድነው የተሸከምከው ? አንተም ሌላ ተጨማሪ ስራ ይዘህብኝ መጣህ ልበል ?» አለ ማይክል ። «ደሞ ሌላ ተጨማሪ ስራ በተለይ ስለዚያ ጣጠኛ የገበያ ማዕከልና ስለ ካንሳስ ስቲው ገበያ ይዘህብኝ መጥተህ እንዳይሆን ! ራሴን ሊያዞረኝ ምንም አልቀረውም ለራሱ »
«ግን ያን ያህል አልጠላኸውም ። እንዲያውም ትወደዋለህ ። ማይክ ፤ እስኪ ንገረኝ በመጨረሻ ያየኸው ፊልም ምንድነው? ዘ ብሪጅ ኦን ዘ-ሪቨር ክዌያ ወይስ ፋንታሲያ ? ለምንድንው ከዚህ ጐረኖህ አንዳንዴ ወጣ የማትለው?» አለ ቤን።

« እንግዲህ ፋታ ሳገኝ መሞከሬ አይቀርም » አለ ማይክ «በነገራችን ላይ የምን ፋይል ነው የያዝከው ?» «አትጨነቅ ። ማስመሰያ ነው ። ላጫውትህ ፈለኩና ይህን?! ተሸክሜ መጣሁ » «ዝም ብለህ ብትመጣ የሚከለክልህ ነገር አለ?» «አይ እንዲያው ነው ። አንዳንዴ እናትህ ስነስርዓት አጥባቂውን የትምህርት ቤት ሞግዚት እንዳልሆነች እየተረሳኝ…» «እሉን ባለመሆኗ እግዜር ምስጋና ይግባው....» ይበሉ እንጂ ሁለቱም ያውቃሉ ፣ማሪዮን ከዚያ ከሚያሙት ሞግዚት ብትብስ እንጂ እንደማትሻል ።

ከዚህ በኋላ ባለፈው የዓመት ፈቃዱን ስላሳለፈበት ሁኔታ ጠየቀው ማይክል ፤ ቤንን ። «ታስብልኛለህ አደለም ?» አለ ቤን። « ለምን አላስብልህሀም ? » «ልክ ነህ» አለ ቤን ትንሽ ካሰበ በኋላ ትክዝ ብሎ «አምንሃለሁ ፤ ለኔ ታስብልኛለህ ። ለራስህ ግን ግድ የለህም» ሁለቱም ዝም አሉ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
934 viewsTsiyon Beyene, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 18:55:52 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ ሁለት (12)

«አረ?... እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ? » ምክንያቱም አለች በልቧ ፣ ምክንያቱም ዛሬ የማይክል ልደት ነው ። ማይክል ዛሬ ልክ ሃያ አምስት ዓመት ይሆነዋል ። አሁን በዚህ ሰዓት ምን እያደረገ ይሆን?
ይህን በልቧ ብላ በአፏ ግን «እንዲሁ አውቀዋለሁ» አለችው ። «ደግ። ሆኖም መልሱ እላጠገበኝም። ስለዚህ እኔ ልንገርሽ። ይህ ቀን የተለየ ቀን የሚሆንበት ዋና ምክንያት የመጀመሪያ ቀን በመሆኑ ነው። የቀዶ ህክምና ሥራችን መጀመሪያ አንችን ለመፍጠር በምናደርገው አስደናቂ ጉዞ የመጀመሪያው ርምጃችን በመሆኑ ነው። ምን ይመስልሻል ?» ይሀን ብሎ ፈገግ አለ። ዓይኖቿ በእንቅልፍ ተሸበቡ የተወጋችው የእንቅልፍ መርፌ ሠራ ማለት ነው።

«መልካም ልደት አለቃዬ»
‹‹እንደሱ ብለህ አትጥራኝ አላልኩም ፤ አንተ ወፈፌ። የክርስቶስ ያለህ። ምን መሰልክ ቤን? ለማኝ»
«አመሰግናለሁ ስለመልካም አስተያየትህ» አለ ቤን አቭሪ። ይህን ብሎ አንዲት ፀሐፊ ደግፋው በክራንች እየተረዳ ወደ ማይክል ቢሮ ገባ። ፀሐፊዋ ደጋግፋ አስቀምጣው ወጣች።
«እንዴት ያለ ቆንጆ ቢሮ ሰጡህ እባከህ። የኔም እንደዚህ ያማረ ይሆን ይሆን?» አለ ቤን።
«ከፈለክ ይህን ራሱን መውሰድ ትችላለህ ። እኔን እንደሆነ ገና ሳይጀመር ስልችት ብሎኛል» አለ ማይክል።

‹‹እሱም የሚከፋ ሃሳብ አይደለም ። አዲስ ነገር ቢኖር...» አለ ቤን። ቤንና ማይክል ሁለት ጊዜ ያህል መገናኘታቸው ነው። ቤን ከቦስተን ወደ ኒውዮርክ ከመጣ ጀምሮ ገና ያላነሱት ነገር አለ። የሚሸሹት ነገር አለ። ሁለቱም ሊያነሱት ይፈልጋሉ። ግን ይሸሻሉ። ስለናንሲ ማውራት ሁለቱም ይፈልጋሉ። ሀዘናቸውን ሊወጡ ይሻሉ። ግን አልቻሉም ዳርዳር ማለት ብቻ።
«ሐኪሙ ከሣምንት በኋላ ማለት በሚቀጥለው ሳምንት ስራህን መጀመር ትችላለህ ብሎኛል» አለ ቤን አቭሪ፡፡ ማይክል ይህን ሲሰማ ስቆ ‹‹ቤን በቃኮ አለቀልህ… የወጣለት ጅል ሆንክ » እለ ።
« አንተሳ፤ ጤነኛ?»

«ነኝና ! » አለና ፊቱ ድንገት ቅጭም ብሎ ወዲያው ፈካ አለ ቢያንስ የሚታይ የተሰበረ ነገር የለም ብሎ። ከዚያም «ስንት ጊዜ ልንገርህ? ቢያንስ ሶስት ሳምንት ማረፍ ትችላለህ… ካሁን በኋላ
ነውኮ የምልህ ! አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ከዚያ በላይ....» በደንብ ካየው በኋላ
«እንዲያውስ ለምን ወደ አውሮፓ አትሄዱም ፤ አንተና እህትህ?» አለው።
«ምን ልሠራ? በአካለ ስንኩል ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ተቀምጩ የሴቶችን ኋላና የዋና ልብስ እያየሁ ልጎመዥ? ይልቅስ አሁን እውነቴን ነው ስራ መጀመር እፈልጋለሁ»
«ደግ! እንደሁኔታው እናደርጋለን» ሁለቱም ዝም አሉ ፤ድንገት። ከዚያም ማይክል ቀና ብሎ
ምርር ባለ አተያይ ቤንን ከተመለከተወ- በኋላ ፤ « ከዚያስ ?» አለው ። «ከዚያ ስትል ምን ማለትህ ነው ማይክል ?» አለ ቤን። «ከዚያስ ማለቴ ነዋ! ስራ ጀመርን። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደፊት ለሚመጣው ሃምሣ ዓመት ያህል ስንለፋ፣፤ ስንባዝን እንኖራለን ። ኖረንስ ምን እናደርጋለን ? ማለት የመልፋት የመባዘን ጥቅሙ ምንድነው? ሰራህ፤ ለፋህ፤ ተከበርክ… እና ምን ይጠበስ››
«ደህና ደህናውን እያሳሰበህ ነውና ጃል !ምን ነካህና እንዲህ ምርር አልህ? በጧቱ ጣትህን በር ቀረጠፈህ?»
«የለም ቤን ፤ ቀልድ ይቁም ። በስላሴ ፤ ላፍታ ያህል ቁም ነገር እንነጋገር። እና ምን ይጠበስ?!»
‹‹ምንም የማውቀው ነገር የለም ። እኔም አደጋው ከደረሰብን ጊዜ ጀምሮ የዚህ አይነቱ ሀሳብ፣ የዚህ አይነቱ ጥያቄ አእምሮዬን እየኮረኮረ ሲያስቸግረኝ ነው የሰነበተው።»

«ምን… ምን መልስ አገኘህለት?»
«እንጃ፤ ማይክ ። እንጃ ። ርግጠኛ አይደለሁም ። እንዲያውም መምጣቴ ደግ ሆነ መሰለኝ ። ምናልባት ሞትን ቀምሼ በመዳኔ ህይወትን ይበልጥ እንድወዳት እያደረገኝ ይሆናል» አለና ሀዘን ፊቱን ሲሰብረው ታዬ። ፀጥታ ሆነ። ሁለቱም ተዋጡ። ማይክል አይኑን ጨፈነ። ከዚያም ተነስቶ ወደ ቤን ሄደ ። እፊቱ ተንበረከከ ። ፊት ለፊት እየተያዩ አለቀሱ ። እንባቸው በፊታቸው ላይ ተረጨ። እጅ ለእጅ ተጨባብጥው እርስ በርስ ተፅናኑ ። የአስር ዓመት ጓደኝነት ፤ የአስር ዓመት ፅኑ መግባባት ፤ ፅኑ ፍቅር።
«አመሰግናለሁ ቤን ፤ እግዜር ይስጥልኝ » አለ ማይክል።
«ማይክ ስማ!» አለ ቤን እንባውን እየጠረገና ተንኮል እፊቱ ላይ እየነጋ ። «ስማ ፤ ዛሬ የልደት ቀንህ አይደለም? ለምን አንወጣምና አንቀማምስም ? » ማይክም ፈገግ አለና ቤንን አየው። ተስማማ፤ በአንገት እንቅስቃሴ ። ከዚያም ሰአቱን አዬ። «አስራ አንድ ሰዓት መሆኑ ነው ። ስብሰባም የለብኝም ።
እንሂድ» አለና ቤንን ደግፎ አነሳው ። ተደጋግፈው ወጡ ። ደግፎ መኪና ውስጥ አስገባው። ከግማሽ ሰአት በኋላ ወዶ ሞቅታ አለም በመጋለብ ላይ ነበሩ።

ጧት እንደምንም ብሎ ተነሳ ። ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነበር እቤቱ የደረሰው። ወደ መኝታ ክፍሉ ያስገባው ዘበኛ ነበር። ሰራተኛዋ ለቁርስ ስትቀሰቅሰው አልጋው ላይ አልነበረም ። እወለሉ ላይ ተኝቶ ነበር ያገኘችው ። እንደምንም ብሎ ወደ ምግብ ቤት ሄደ ። ማሪዮን ቀድማ ለባብሳ ጋዜጣ ስታነብ አገኛት ። ለቁርስ የቀረበውን ነገር ሲያይ አቅለሸለሸው ። ራሱን ይወቅረዋል ። «ትናንት እንዴት ነበር ? » አለች ማሪዮን ። «ከቤን ጋር ነበር ያመሸሁት » «አብራችሁ እንደወጣችሁማ ጸሐፊህ ነገረችኝ ። የዚህ ዓይነት ነገር ባይለምድብህ መልካም ነው ።» እኮ ለምን ? አለ በሀሳቡ ። «ምኑ ? መጠጣቱ ?»
«ሰዓት ከመድረሱ በፊት ቢሮ ጥሎ መውጣት ማለቴ ነበር ። መጠጣቱም ቢሆን በርታ የሚያሰኝ አይደለም ። ወደ ቤት ስትገባ አምሮብህ እንደገባህ ነው »

‹‹እንጃ ትዝ አይለኝም » አለ ፤ፉት ያለው ቡና ሽቅብ እየተናነቀቅው ። «ሌላ የዘነጋኸው ነገር ትናንት ለራት ጋብዤህ ነበር።ግን አልመጣህም ። እኔና ሌሎች እንግዶች አሥር ሆነን ስንጠብቅህ ነው ያመሸነው»
«አላወቅኩም ። ራት ጋብዤሀለሁ ስትይኝ ሁለታችን ብቻ የምንገና መስሎኝ ነበር »
« እና… እኔስ ብሆን ፤ እኔ መጠበቅ ነበረብኝ ?»
« እንደሱ ማለቴ ሳይሆን ዘነጋሁት ። ተረጂልኝ እንጂ ችግሬን ማሚ ። የትናንቱ የልደት በዓል ለኔ በአል አልነበረም እኮ ደስ ብሎኝ ላከብረው እችላለሁ?»
« በቃ ተወው ። ይቅርታ›› አለች ። ትበል እንጂ ያ ቀን ለሱ ለምን መልካም እንዳልሆነ የተገነዘበች አትመስልም፡፡ ‹‹ነገርን ነገር ያመጣዋል ቤት ተከራይቼ ፤ ለብቻዬ መኖር እፈልጋለሁ»
‹‹በመገረም ቀና ብላ አየችውና ፤ « ለምን ? » አለች «ምክንያቱም ሃያ አምስት ዓመት ሞላኝ ። ሠራተኛ ነኝ። ዘላለም አብሬሽ መኖር የለብኝም »
«ምንም ነገር በግዴታ ማድረግ የለብህም » አለች። በልቧ ስለ ቤን አቭሪ ጓደኝነት ማሰላሰል እየጀመረች። «የለም ነገሩን በክፉ እንድትተረጉሚው አይደለም ። ሆኖም እንተወው ። ራስ ምታት እንደወፍጮ እየወቀረኝ ነው » «የዞረ ድምር መሆኑ ነዋ » አለችና ተነሳች ፤ ሰዓቷን እያየች «ቢሮ እንገናኝ ። በሰዓቱ ግባ ። ደሞ ስብሰባ አለ እንዳትረሳ። የሀውስተንን ጉዳይ በሚመለከት ስብሰባ መኖሩ ተነግሮህ የለ! እንዴት ነው ልትገኝ ትችላለህ ? »
«እችላለሁ .... እና ስለቤቱ ጉዳይ ... እሚከፋሽ ከሆነ ይቅርታ ። ግን ወስኜ ጨርሻለሁ። ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል። » ኮስተር ብላ ካጤነችው በኋላ « ይሆናል ማይክል ። ምናልባት ጊዜው ይሆናል ። በነገራችን ላይ መልካም የልደት በዓል ይሁንልህ » ብላ ግንባሩን ሳመችው። መልካም ምኞቷን በፈገግታ ተቀብሎ ራስ ምታቱ እየወቀረው
827 viewsTsiyon Beyene, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:49:03 «ተዘጋጅተሻል ?»
‹‹ይመስለኛል »
ናንሲ ማክአሊስተር የመጀመሪያው ኦፕራሲዮን ሊደረግላት ነው። ካንገቷ በላይ ምንም ስሜት አይሰማትም ። በዓይኖቿ ያለችበትን ባታይ ኖሮ ፊቷ ለመኖሩ ርግጠኛ ባልሆነች ነበር ። የአፕራሲዮን ማድረጊያው ክፍል መብራት ስለሚያብረቀርቅ አይኗን በደንብ መግለጥ እያስቸገራት ነው ። ዓይኗን ማጨንቆር ይኖርባት ነበር ። ይህን እንኳን ማድረግ አልተቻላትም ። የሚታያት የፒተር ፊት ብቻ ነው ። ኦፕራሲዮን የሚያደርገ ሀኪም የሚለብሰውን ልብስ ለብሷል ። አፉንም ተሸፍኗል ዓይኖቹ ፤ ፍቅርን የሚረጩ ዓይኖቹ ያበራሉ ።

ፒተር ግሬግሰን ናንሲ ከመጣችበት ጊዜ ጀምሮ አላረፈም። ኦፕራሲዮን ከመጀመሩ በፊት ቀዶ ህክምናውን የሚያካሔድ በትን ዘዴ ሲቀይስ ፤ ሲነድፍ ፤አጠናክሮ ንድፉን ሲያወጣ! ሲለካ ሲዘጋጅና ሲያጫውታት ሰባት ሳምንት አለፈ ።፡ ይሀን ሁሉ የሚያደርገው ደግሞ ፊቷን በተለያየ ጊዜ ራጅ አንስቶ ነበርና ከራጁ ያገኘውን ምስል እንደመነሻ በማድረግ የጐደለውን በማየት፣፤ የሚሟላውን በማጥናት ነበር ። የናንሲን ፊት እንደገና ለማነጽ ፎቶ ግራፉን ማግኘት ይፈልግ ይሆናል። ሆኖም የተገኘው አንድ ፎቶ ግራፍ ብቻ ነበር «ይኸውም እሷና ማይክል ርሄት በትለርና ስካርለት ኦሀራን ሆነው በባዛር ላይ የተነሱት ፎቶግራፍ ብቻ ። እሱም በደንብ አልወጣም ። ያም ሆነ ያ እሱም አያስፈልገውም ። ለመነሻ ያህልም ቢሆን ያቀደው ፊት አለ ።

«ነቃ ነቃ ማለት አለብሽ ። ትንሽ ሰመመን...ኖ... መተኛት የለብሽም ። ያ እንዳይሆን ደግሞ አነጋግሪኝ» አለ፡፡ እንቅልፍ ሲጫናት ሽፋሏ ሲሰበር ስላየ። በልቡ ደግሞ ያለዚያ ደምሽ ያንቅሻል ሲል ጨመረ ። ይህን ግን አልነገራትም ። ሊነግራትም አልፈለገም ።
«እማሆይ አግኒስ ሜሪን መሆን እንደምትፈልጊ አሁንም ርግጠኛ ነሽ ? » አላት ፤ እንዳትተኛ ለማድረግ ።
‹‹እንዴ...ሃ!ሃ!ሃ!... ቃል ፣ቃል አይደለም እንዴ» አለች ።

ሶስት ሰዓት የፈጀው ኦፕራሲዮን ሲከናወን በዚህ ሁኔታ እየተቀላለዱ አሳለፉት ። ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እጁ አንዴም አላረፈም ። ናንሲ የእጁን እንቅስቃሴ ስታይ ልክ የባሌ ተውኔት ዳንስ እንደማየት ሆኖ ነበር የተሰማት ።
«በዚህ ሁኔታ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ አዲሱን አፓርታማ እንከራይና ትገቢያለሽ ... እስኪ አስቢው ፣ደስ የሚል ነገር አይመስልሽም? . . . እንዴ እንቅልፍ መተኛትሽ ነው እንዴ! የአዲሱ አፓርታማ አቀማመጥ እንዴት ቢሆን ይሻል ይመስልሻል ? እመኝታ ቤትሽ ሆኖ በመስኮት የሳንፍራንሲስኮን ወደብ የሚያሳይ ቢሆን ይስማማሻል ? »
« አዎና ለምን አይስማማኝም››
«አዎና ብቻ ነው እምትይው ? በጣም፣ በጣም... ምናምን አይባልም ! የለም ፤ የለም ይህ ከሆስፒታሉ ላይ ሆነሽ የሚታይሽ ነገር አእምሮሽን እያሻገተው ሳይሆን አይቀርም »
«ውሸት ነው ። በጣም ነው የሚያስደስተኝ እንዲያውም»
«ደግ እንግዲያ ። አንድ ቀን አብረን ወጣ እንልና ከዚህ በጣም የተሻለ ቤት እንመርጣለን »
‹‹ጥሩ» አለች እንቅልፍ በተጫነው ድምፅ ። እንቅልፍ በተጫጫነው ድምፅ ብትናገርም ደስ መሰኘቷ ይታወቅ ነበ
«እንዴት ነው አሁን መተኛት አልችልም ማለት ነው?›› አለች ።
«ልዕልት ሆይ እንሆ የመኝታ ጊዜ ተቃርቧል ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ወዴ መኝታ ቤትዎ እናደርስዎታለን ። ከዚያም ልዕልትነትዎ የፈቀደውን ያህል ሊተኛ ይችላል »
« መልካም »
« አሃ! ሳሰለችሽ ነበር ማለት ነው የቆየሁት !» ይህን ያለበት የቀልድ ኩርፊያ ድምፅ አሳቃት ።
«እሺ ፍቅሬ... አሁን ሁሉም ዝግጁ ነው » አለና ረዳቱን ተመለከተ ። በጥቅሻ አመለካከት ። ይህን ያየችው ነርስ ናንሲን መርፌ ወጋቻት ። ይህ ሲደረግ ፒተር አላየም ። ወደናንሲ ጠጋ ብሎ ዓይን ዓይኗን ያይ ነበር ። እሱ ፤ የሷን ፤እሷም የሱን ዓይን በሚገባ ያውቃሉ ። መግባባታቸውን የሚያዩት በዓይኖቻቸው ውስጥ ነበር ።
«ዛሬ ለየት ያለቀን መሆኑን ታውቂያለሽ ?» አላት
« አዎ» አለችው ።
«አረ?... እንዴት ልታውቂ ቻልሽ ? » ምክንያቱም አለች በልቧ ፣ ምክንያቱም ዛሬ የማይክል ልደት ነው ። ማይክል ዛሬ ልክ ሃያ አምስት ዓመት ይሆነዋል ። አሁን በዚህ ሰዓት ምን እያደረገ ይሆን?

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
998 viewsTsiyon Beyene, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:48:13 #ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስራ አንድ (11)

ማይክል ማስተዛዘኛ ቃሉን ተቀብሎ መንገዱን ቀጠለ። ወደ አውራው መንገድ እየተጓዘ አሰበ ። እነማን ናቸው ? ነርሶቹ ከሆስፒታል የተላኩ ይሆኑ? ጥንብ አንሳዎች ! ጥሪት ለመለቃቀምማ ማን ብሏቸው! ምናልባት. . . ግን ምን ያገኛሉ ? ሥዕሎቿን ? እና ጥቂት ጌጣ ጌጦች እና. . . ጥንብ አንሳዎች !ምነው .. . ምነው ሲለቃቅሙ በያዝኳቸው ኖሮ ! ወይኔ ! ቀኝ እጁን ጨብጦ የግራውን መዳፍ በቦቅስ ነጠረቀውና በቡጢ በተመታው እጁ ጥብቅ እድርጐ ይዞ አሸው ። ድንገት ለቀቀውና ቡጢ የነበረውን እጁን ታክሲ ሊያስቆም ዘረጋው መጠንከሩ አይከፋም ። ምናልባት የሆነ ፍንጭ . . . ልሞክር. . . ፊቱ ላይ መጥቶ ቆመ ታክሲው… በሩን ከፍቶ ገባ ።

«በዚህ አካባቢ ያለው የጉድዊል ቅርንጫፍ የት ነው? » አለ ማይክል ።
«ጉድ ዊል ምን? .. . »
«ጉድ ዊል ዕቃ ማከማቻና መሸጫ. . . አሮጌ ልብስ... አሮጌ የቤት ዕቃ ምናምን…»
«ገባኝ »ገባኝ »

ጉድዊል ያገለገሉ ዕቃዎች ማከማቻና መሸጫ መደብር ሊገባ ሲል እውነት ምን ለማድረግ ነው የመጣሁት ? ዕቃዎቹ በጠቅላላ ቢኖሩስ ምን ለማድረግ ? አጠቃላዩን ልገዛ ? ከዚያስ ? ግራ ገባው ። ሊመለስ ከጀለ ። ግን አላደረገውም ። ወደ መደብሩ ውስጥ ስተት ብሎ ገባ ። ወጣ ወረደ ። አንድም ዕቃ ፤ የሷ የነበረ ነገር አላየም ። ግራ ገባው ። እንደገና አሰሳውን ጀመረ ወዲያው አንድ ነገር ብልጭ አለለት ። ለካ ለዕቃዎቹ ደንታ የለውም ! ለካ የሚፈልገው ዕቃ ሳይሆን ሰው ኖሯል ። እራሷን ? ናንሲን! አፓርታማውን እንዳለ ፣እንደነበረ ቢያገኘውም ለካ ጥቅም አልነበረውም ። ለካ ይኸ ሁሉ ልፋት ከንቱ ሽሽት ነበር ።

ከመደብሩ ወጣ…. ባዶ ሆኖ ሙት ሆኖ እንደህያው የሚንቀሳቀስ ሙት ሆኖ ወጣ። ታክሲ አልያዘም ። እንዲያ እሚባል ነገር ከነመኖሩም ለማስታወስ የሚችልበት አእምሮ አልነበረውም ። በዘፈቀደ መንገዱን ተያያዘው ። ግን ይህም ይባል ዘንድ ልክ አይመስልም ። ምክንያቱም በእግር ለመጓዝ ኃይል ያስፈልጋል ። አካል ፤ ሥጋ ፣ ኃይል ይፈልጋል ። ። አካሉ አጥንት አልባ የሆነ ለስላሳ ሆኖ ተሰማው ። ነፍሱ ግን ጠንካራ ነበረች ። ቆመ ግን ድንገት አልነበረም ። መንገድ ማቋረጥ ነበረበትና አረንጓዴው መብራት ጠፍቶ ቆዩ መብራት እስኪበራ ለመጠበቅ ቆመ ፤ ግን እስኪበራ አልጠበቀም ። የመጣው ይምጣ ብሎ ለመራመድ ሲሞክር ሰማይ ምድሩ ጨለመበት… ባዶ ።

ሲነቃ ሰዎች ከበውታል ። ከመንገድ አለፍ ብሎ በሚገኘው ሰው ሠራሽ መስክ ላይ ነበር የተንጋለለው ። ሰዎች ከበውታል ። ዓይኑን እንደገለጠ ፣
« ተሻለህ ፤ የኔ ልጅ» አለ አንዱ ፖሊስ
"ፖሊሱ ልጁን በደንብ ሲያጤነው ቆይቷአል ። ጠጥቶ እንዳልሰከረ ወይም አደንዛዥ እፅ እንዳልወሰደ ፤ ወይም ተደባድቦ አደጋ እንዳልደረሰበት ተረድቷል ። ህመም መሆኑን አውቆታል።
“ደና ነኝ» አለ ማይክል ረሀብ ይሆን? አለ ፖሊሱ በሀሳቡ ። ደግሞ ይህን ሀሳብ ለመቀበል አስቸጋሪ ሆነበት። ልጁ በደህና እንክብካቤ ያደገ ይመስላል ። የተጎሳቆለ ነገር አይታይበትም ።
«ያውቅሀል ፤ ከዚህ በፊት?»
«አይ ፤ ትንሽ ስላመመኝ... ዛሬ ነው ከሆስፒታል የወጣሁት። እኔም ትንሽ አበዛሁት መሰለኝ » ማይክል እዚያው እንደተጋደመ የከበቡትን ሰዎች አየ ። ሙሉ ክብ ሰው። ቀና ሊል ሲሞክር ከሰዎች የተሰራው ክብ እንደመንኮራኩር መሽከርከር ጀመረ ። ተመልሶ ተዘረጋ ይህን የተመለከተው ፖሊስ ሰዉን በተነና ተመልሶ
«መኪና ይመጣልሀል ። ለጥበቃ የተሰማሩ መኪናዎች አሉ፤ እናደርስሀለን» አለ ።
«አይ ይህን ያህልም… »
«ግዴለም» ፖሊሱ ይህን ብሎ ባጭር ርቀት መነጋገሪያ ሬድዮው መልእክቱን አስተላለፈ ። መኪናው ካካባቢው አልራቆ ኖሮ ወዲያውኑ ከች አለ።
ማይክል ተሳፈረ። ከሆቴሉ አንድ ምዕራፍ ያህል መለስ ያለ አድራሻ ሰጣቸው ። የተባለው ቦታ እንደደረሱ አወረዱት።
«አይዞህ» አለው ፖሊሱ ።
«እግዜር ይስጥልኝ » ሆቴሉ ሲደርስ ማንም አልነበረም ። ቀድመውት አልደረሱም ማለት ነው ። ልብሱን አወላልቆ አልጋው ላይ ወጥቶ ሊተኛና ሊጠብቃቸው አሰበ ። ግን ወዲያው ሐሳቡን ሰረዘው ምን ዋጋ አለው? ምን ድብብቆሽ መጫወት ያስፈልጋል ? ሊያደርገው ያሰበውን እንደሆነ አድርጓል ። ምንም እንኳ ከእውነቱ ፈቀቅ ሊያደርገው ባይችል ቁርጥ ማወቅም ደግ ነው ። ናንሲን ነበር የሚፈልገው ። ናንሲን አላገኛትም ። ሊያገኛት እንደማይችል ቀድሞውኑ መገንዘብ ነበረበት ። ዛሬም ፣ ወደፊትም ፤ የትም የት ሄዶ መፈለግ የለበትም ። ፍለጋው ፋይዳ ቢስ ነው። ግን ናንሲ ሁልጊዜም አለች። ያለችውም አንዲት ቦታ ነው ። ልቡ ውስጥ ፤ እራሱ ማይክል ውስጥ… በቃ!

የክፍሉ በር ሲከፈት ይህን እያሰበ እመስኮቱ አጠገብ ቆሞ ወዲያን ይመለከት ነበር ። ወደ ውጭ። ወዲያ በጣም ወዲያ።
«ምን ትሰራለህ እዚያ ጋ ማይክል?» አለች ማሪዮን ሂልያርድ። ሁልጌዜ እንደ ሕጻን!ሃያ አምስት አመቴን ልደፍን እንደሆነ አንድም ቀን አትገነዘብም አለ በሐሳቡ ።
‹‹ከእንግዲህማ ይብቃኝ ፤ ማሚ» አለ ማይክል ። «ቀና ፤ ቀና እያልኩ ካልተለማመድኩኮ ተኝቼ መባጀቱ ነው። እንዲያውም ዛሬውኑ ኒውዮርክ ሄጄ ለማደር አስቤአለሁ »
«ምን አልክ?»
«ኒውዮርክ ለመሄድ አስቤአለሁ»
«ግን… እዚህ ትንሽ ቀን ለማሳለፍ እፈልጋለሁ ብለህ ነበረ ኮ!» ግራ የመጋባት ሁኔታ ይታይባት ነበር።
«ምን አደርጋለሁ!? በዚያም ላይ አንችም ስብሰባሽን ጨርሰሻል» አለና በልቡ ደግሞ እኔም ጉዳዬን ፈጽሜአለሁ ሲል ጨመረ ። ቀጥሎም «ስለዚህም መሄዱ ይሻላል ። እንዲያውም ነገውኑ በጧት ሥራ መጀመር አለብኝ። አይመስልህም ጆርጅ?» ብሎ ጆርጅን አየው ።

ጆርጅ ማይክልን በደንብ ካጠናው በኋላ ፣ ልጁ በሀዘን ተሰብሯል ። ምናልባት ሥራው ያፅናናው ፤ ያረሳሳው ይሆናል ሲል አሰበና
«ወርቅ ሀሳብ ነው» ሲል መለሰ። « ግን እስክትጠና ድረስ ግማሽ ቀን ብትሰራ በቂ ነው»
«አልገባኝም ። አበዳችሁ ልበል ወይስ..." ትናንት ከሆስፒታል ወጥቶ ሥራ…!» አለች ማሪዮን ።
«አቤት! አቤት!» አለ ማይክል ነገሩን ወደቀልድ እየለወጠ «አሁን እንዲህ ሲሉ እሳቸው ይረፉ ቢሏቸው በጄ እሚሉ አይመስሉም!» ይህን ብሎ «በያ መልስ ስጪ !» በሚል አስተያየት አያት። ቀስ ብላ እሶፋው ላይ አረፈችና ተደግፋ ተቀመጠች። «እሺ በቃ ይሁን ፤ አታፍጥብኝ» አለች ቀልዱ ደስ ብሏት ፈገግ እያለች ። ይኸኔ የንግግሩን ፈር እየቀየረ ፤ «ስብሰባው እንዴት ነበር?» ሲል ጠየቀ ። ፈር መቀየሩ ብቻ ሳይሆን ካቀዳቸው ነገሮች መካከል ዋናውን መጀመሩ መሆኑን ወዲያው ተገንዘበ ። ዛሬ ለማይክል በአለም ላይ የቀረው ነገር ቢኖር ይኸው ነው ። ለመኖር ከፈለገ አሁን ሊሄድበት በጀመረው መንገድ ጭልጥ ብሎ መሄድ አለበት። ወሬው ሐሳቡ ሁሉ እድርጅቱና እሥራው ላይ መሆን አለበት። ጉልበቱ ፤ፍቅሩ ለድርጅቹና ለሥራው መሆን አለበት ። ሕይወቱ እሱ ብቻ ነው። ምን ቀረው? ከሥራው ውጭ ያለ ሕይወቴማ አበቃ ። አለቀ ። ከናንሲ ጋር ተቀበረ ።
925 viewsTsiyon Beyene, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ