Get Mystery Box with random crypto!

🍂ISLAMIC TEAM🍂

የቴሌግራም ቻናል አርማ islllllaamic — 🍂ISLAMIC TEAM🍂 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islllllaamic — 🍂ISLAMIC TEAM🍂
የሰርጥ አድራሻ: @islllllaamic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.21K
የሰርጥ መግለጫ

For any comment👉👉 @Isllllllaam_bot

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-15 22:48:15 ለምን አላማረብሽም?ለምን ተጫዋች አትሆኚም? ብቻ ሆነ ቋንቋዬ። የቤት ስራዎቿ ላይ በማይለቅ ቀለም እየሞነጫጨረ ይበልጥ ስራ የፈጠረባት ህፃን መሆኔ ጎልቶ ታየኝ።

<<ሂድ ትላት>> የነቢሎ ድምፅ ርቄ ከተሳፈርኩበት አባነነኝ። ሀዩ ነበረች ሁነታዬን አይታ ራቅ ብላ አስሸምድዳ የላከችው፤ ሳላስበው አይኖቼ እምባ አቅርረው ኖሯል ለካ።
<<ምን ልበላት?>>
<<ኦድሻለው በላት>>
<<ነቢሎ ይወድሻል ነው የምላት?>> ደስ እንዲለው እየተሞኘሁለት
<<አደለም አጎቴ ደሞ። ሀሚድ ይወድሻል በላት። አንተ እኮ ነህ የምትወዳት። ቅድም ሀዩን እንዳደረኳት አይተሃል አደል? አይኗን ጭፍን አድልጋትና ድምፅህን ቲኒት አድልገህ ነቢሎ ነኝ በላት። እኔን ስለምወደኝ እኔ መስለሃት ትታለቅሀች።>> አለና ሁለቱንም አይኖቹን እኩል ጨፍኖ ጠቀሰኝ።

የልጆቹ አስተዋይነት እየገረመኝ እንደተባልኩት ይቅርታዋን ለመጠየቅ ወደ ማዕድ ቤቱ አመራሁ። <<ዩስሪ ነቢሎ ነኝ...በአላህ አታልቅሺ፤ ሀሚድ እኮ ይወድሻል>> አልኳት የረጠቡ አይኖቿን በመዳፎቼ ከድኜ።
<<እኔም እወደዋለሁ ሀያቲ... ድሮስ ሊጠላኝ አምሮት ነበር? ሽንኩርት አቃጥሎኝ ነው እንጂኮ ደህና ነኝ>> ለቅሶ በዘጋው ድምጿ እምባ የቀላቀለ ሳቅ እየሳቀች።
<<አየህ እኔን መስለሃት እኮ ነው። ካሁን ቡኋላ ካስለቀሰሽ እኔን ትሊኝ እሺ አክስቴ ዩስላ>> ነቢሎ ይበልጥ በራሱ ብልሃት ተጀነነ። ሁላችንንም በየዋህነቱ አሳቀን።

<<አክስቴ ዩስላ... እነዚህን ወልገይነቦች ልብላቸው?>> አለ ወደ ቆሻሻ መጣያው እየጠቆመ። ዩስራ ልትሸፋፍን ሮጠች... እኔ ቀደምኳት። ከተሰበረ ሰሃን ጋር በርከት ያለ መጠን ያላቸው ወርገይነቦች ተጥለዋል... ቀን ለምሳ ከቀረቡልን በመልክም ሆነ በጠረን ይበልጥ የሚያስጎመጁ ናቸው? የተሰበረውን የሸክላ ሰሀን አንስቼ ተመለከትኩት... ትዝ አለኝ! ጠዋት ወደ መዐድ ቤቱ እንዳስገባላት የጠየቀችኝ ሰሀን ነው። በችኮላ እየወጣሁ ከጀርባዬ የሰማሁት የሚሰበር እቃ ድምፅ ታወሰኝ። ከጠረጴዛውስ ጎን ምን ነበር?... የቆሻሻ መጣያው! ሱብሃነላህ እንዴት አላስተዋልኩም?... ለካ እኔ ነኝ። እኔ ነኝ የግማሽ ሰዐት ስራዋን የሙሉ ቀን ፍዳ የቸለስኩበት፤ እኔ ነኝ የሚጣፍጥ ሙያዋን በችኮላ የይድረስ ስራ ያስገመትኩት። እንዳግዛት ስትጠይቀኝ የጠረጴዛው ጫፍ ላይ ወርወር አድርጌው በመውጣቴ ሰሀኑ ከመሬት ወድቆ ምግሙም በቀጥታ ከፊሉ መጣያው ውስጥ ተበትኖ እንዳይሆን ሆኖ አክትሞለት ነው የሚሆነው። እሷ ግን ረሃቧን እንድትውል ለፈረድኩባት እናቴ አይን ውሃዋ እንዲሞላ ቀኗን ስትሰዋ ዋለች፤ ስድቡን ችላ የባሏን አይብ ሸሸገች። ታዲያ ማን ነው የማን ልጅ?

<<ሀሚ ዝም ብሎ ነገር ነው። የማይጣፍጡት ናቸው... ማለት ካልተበሉ ብዬ..>> አሁንም ከራሴ እንዳልጣላ ትሸፋፍንልኛለች። ቃላቶቼ ይቅርታን ለመጠየቅ ፈርተው እርስ በእርሳቸው እየተጠላለፉ ምላሴን አሰሩት። ዝም ብዬ ወደደረቴ እቅፍ አድርጌአት ማንባት ጀመርኩ። እሷም የሙሉ ቀኑን ብሶት፤ ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላ ሲቃ እስኪያፍናት አራገፈችው። ሀዩ ነቢሎን ይዛው ጊቢው ውስጥ ለመጫወት ወጡ። ነቢሎ በሰበቡ የናፈቀው ጨዋታ ሞላለት።
.
.
.


@islllllaamic
@islllllaamic
1.2K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 22:48:02 ልጅነት ሲመክር
(በያስ ሁዳ)
.
.
<<ሂድ ጥራት>>
<<ከዛስ>>
<<እወድሻለሁ በላት>>
<<አጎቴ ሀሚድ ይወድሻል ነው የምላት?>>
<<አይደለም። ነቢል ይወድሻል በላት>>
<<እህህ... ነቢልማ እኔ እኮ ነኝ>>
<<እኮ አንተ እኮ ነህ የምትወዳት። ታዲያ እኔ ነኝ እንዴ መታረቅ ያማረኝ?>>
<<እኔ አዎዳትማ... እኔ እንድታጫውተኝ ብቻ ነው የፈለኩት። አንተ ላስህ ሂድና <ነቢልን አጫውቺው> በላት። እኔ ስላት አትሰማም... እኔን አቶደኝም>> በሚኮላተፍ አንደበቱ እየተነጫነጨበት። ገና 5 አመቱ ነው፤ ትምህርት ቤት ምን ያህል ከጨዋታ እንደሚያቦዝን አልተረዳም። ለሱ ቤትም ሆነ ትምህርት ቤት ያው ነው፤ ጨዋታ...ምግብ... መኝታ። ለ9 አመቷ ሀናን ግን ህይወት ሌላ መስመር ይዛለች። ከትምህርት ቤት መልስ ወደ መድረሳ፤ ከደርስ ስትመጣ ወደ ጥናት... ለጨዋታ ያላት ቦታ እየደበዘዘ መጥቷል። ከማናችንም በላይ ግን ነቢል የእህቱ ጨዋታ መቀነስ ውስጡን ሰርስሮት ገብቷል፤ ሌላው ታሪክ አይመለከተውም ለእሱ ቀላሉ አማርኛ ስለማትወደው መሆኑ ብቻ ነው።

<<አሁንማ አስኮርፈሀታል እኮ። መጀመሪያ ሂድና ይቅርታ በላት። እሷ እኮ ሚሷ የቤት ስራ ስለሰጠቻት ነው። ካልሰራች ደግሞ ግርፍ ታደርጋታለች... እንጂ እኮ ትወድሀለች። ቶሎ በል ሮጥ በልና ከጀርባዋ እቅፍ አድርጋት ጎሽ... እሷ እኮ ሌላ ወንድም የላትም አታሳዝንም?>> አንጀቱን ለመብላት እየሞከርኩ። ትንሽ ካመነታ ቡኋላ እየሮጠ ሄዶ ከጀርባዋ አይኗን ያዛት።
<<እኔ ማነኝ?>> ሊሸውዳት ድምፁን ለማጎርነን እየታገለ።
<<እምም... ሀሚ ነህ?>> አውቃ ተታለለችለት፤ ሀናን። ነቢል ሙከራው የተሳካለት መስሎት ደስ አለው... ሳቁ ብፍ ብፍ ብሎ እያመለጠው <<አይደለሁም>> ጎርናናውን ቅላፄ ላለማጥፋት እየሰጋ። ትንሽ እንዲ ከተሸወደችለት ቡኋላ የራሱ ብልጠት ለራሱ አስገርሞት አይኗን ገለጠላት፤ እቅፍ አድርጋ ለደቂቃዎች እየኮረኮረች ስታስቀው ቆየች። በእህቱ ናፍቆት ተከፍተው ጠውልገው የነበሩት ጉንጮቹ የበሰለ ቲማቲም መስለው እስኪቀሉ ድረስ ሳቀ።

አይኖቼን ከነሱ ሳነሳ የኔዋ ከቅድሙ በተለየ መልኩ ታየችኝ። ፀጉሯ በሁለት ተጎንጉኖ ደረቷ ላይ አርፏል፤ ራሷንም በነጭ ጨርቅ ቢጤ ጠበቅ እድርጋ አስይዛዋለች። ፀጉሯን ለመሸፈን አልነበረም... ራሷን ስላመማት ነው። እድሜ ለኔ፤ ለትዕግስተ ቢሱ! በሰባሪ ቃላት ወርጄባት ስታለቅስ ነው የቆየችው። አይቼ የማልጠግባቸው ኮከብ መሳይ አይኖቿ ዛሬ በኔ ምክኒያት በእምባ ተሞልተዋል። እንደ አልቃሻ ህፃን ደጋግማ ጉንጮቿን በመዳፏ እያበሰች ሳያት እኔንም ሆድ ባሰኝ። አሁንም ግን እየሰራች ነው፤ በጎን እንግዶቹ የተመገቡበትን ሰሃን ታጥባለች። ዘወር ብላ ደግሞ ለልጆቹ መክሰስ የሚሆን እንቁላል ትጠብሳለች። ግን ምን ሆኜ ነው?

እለቱ እናቴና ሁለት እህቶቼን ምሳ የጠራሁበት ልዩ ቀን ነበር። እኔ ልጆቹን ትምህርት ቤት አድርሼ እስክመለስ እሷ ቤቱን ስታሰናዳና ስታበሳስል ቆየች። ለመውጣት ተዘጋጅቼ ስጠይቃት <<በ ግማሽ ሰዐት ውስጥ እጨርሳለሁ፤ አንተ ይዘሀቸው ስትመጣ ሁሉም ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል>> ነበር ያለችኝ፤ ዩስራ። እግረ መንገዴንም ወረገይነቦቹን ጠረጴዛው ላይ እንዳስቀምጥላት ጠይቃኝ አድርጌአለሁ። <ከዚህስ በላይ የሚያግዝ ባል ከወዴት ሊገኝ?> እያለ የሚፎክረውን ልቤን ገትቼ፤ በችኮላ... ያስለመድኳትን የፍቅር ስንብቴን እንኳን ሳልሰጣት ወጣሁ። ይሁን እንጂ ኡሚን፤ ዘይነብን አና ሩቀያን ይዤም ስመለስ እዛው ናት። ራሷን አትጠብቅም ብዬ ተናደድኩ፤ ግን ምናልባት ስለቸኮልንባት ይሆናል ብዬ ኡዝር ሰጠኋት።

ምሳው ደርሶ እስኪቀራርብ ድረስ ማዕድ ቤት ውስጥ መንጎዳጎዷን አላቆመችም። ኡሚ ማጉተምተም እና መከፋት ስትጀምር አየሁ... እነ ዚዚም ቢሆኑ ወጥታ እንድታጫውታቸው ከጅለዋል። በስተመጨረሻም ምሳው ቀረበ፤ እሷም ተጣጥባ እንደ ነገሩ ልብሷን ቀይራ መጣች። ምግቡ ሁሉ ማሻአላህ የሚጣፍጥ ሆኖ ሳለ ኡሚ የምትወደው ወርገይነብ ብቻ የተቸኮለበትና ያልበሰለ ነገር ሆነ። ኡሚ ካለሱ ምግብ ንክች እንደማታደርግ ታውቃለች... ከዚህ በፊት ሰርታልኝ ስቀምሰው እንዲህ ሆኖባት አያውቅም። ታዲያ የኔ ቤተሰቦች ሰለመጡ ነው ሙያው የሚጠፋት? ኡሚ ሰሀኗን ገፋ አድርጋ ተነሳች።
<<ምነው ማማ.. አልጣፈጠሽም? ወይ ሌላ ልስራልሽ በአላህ... እስከዛ ሌላውን ቀማምሺ>> ዩስሪ ነበረች።
<<አዪዪ... ፊቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ። ተይው አንቺም አትድከሚ፤ ከእናት ቤት ያልተማሩት ሙያ በአንድ ቀን ከየትም አይመጣም። ሩቂ ትሰራልኛለች።>> አኮረፈች።

ዩስሪ ንግግሩን ወደ ውስጧ ላለማስገባት ብላ ተነስታ ቡናውን ማቀራረብ ጀመረች፤ እነ ኡሚ ግን ካልሄድን ብለው ወጠሩን። ብንለምናቸው እምቢ አሉን፤ ሳምንታት የጠበቅነው ቀን ተበላሸ። ከሁሉም ግን ኡሚ ልትሄድ እየለባበሰች የተናገረቻት አንድ ቃል ጭንቅላቴን በጠበጠችው።
<<የአብራኬን ክፋይ ከሃዋው ጋር ሲደሰት ላየው እንጂ የተዘፈዘፈ ፊት ሊገርፈኝ አልመጣሁም። አንዴ እንኳን ተቀምጣ ልታጫውተኝ አላሰበች፤ አትምጡብኝ ማንን ገደለ ልጄ..>> አለችና አፉታዋን ሳትሰጠን ሄደች።

እነሱን ሸኝቼ ስመለስ ዩስሪ የቀራረበውን ቡና ስታነሳሳ አገኘኋት። አንድ ሁለት እያልን ብዙ ተናገርኳት፤ <<በእናትሽ ላይ የማታደርጊውን በኔ እናት ለምን?>> ብዬ ብዙ ወቀስኳት። ቤተሰቦቼን ስለማትወዳቸው ያመጣቸው ቸልተኝነት መስሎ ታየኝ። ዩስሪ ግን አሁንም ለቸልተኝነቷ ማብራሪያ መከራከሪያ ለማቅረብ አልፈቀደችም። እኔም እንደተበሳጨሁ ልጆቹን ከ ትምህርት ቤት ይዣቸው ተመለስኩ። ነቢልና ሀያት አላህ ይማረውና የወንድሜ ሰፍዋን ማስታወሻዎቼ ናቸው። ዩስሪን ሳገባ ጀምሮ አብረውን እየኖሩ 2 አመታትን አስቆጥረናል። እነሱን አሳታርቄ በተረጋጋ መንፈስ ሳያት ነበር ቀን የለበሰችውን አውልቃ ሀዘን ቤት መስላ መቀመጧን የተገነዘብኩት።

ቆይ ግን ምን ሆኜ ነው? ለምን የሷ ብቻ ጥፋት ታየኝ? አስር የምግብ አይነት ቀርቦ አንዱ መበላሸቱን አይታ የምትወቅሰውን እናቴን ብቻ ማዳመጤስ ለምን? እሷ እንደ እናቷ አላየቻትም የምለው... ኡሚስ በእርግጥ እንደ ልጇ አይታታለች? ለነገር ፍለጋ እንጂ ሩቂ ከሁቢ የተሻለ በተአምር እንደማታበስል አውቃለሁ፤ በሷ እጆች ለአመታት በልቻለኋ! ዩስሪ ሀናንን ሆና ሁላችንም ትንሹን ነቢል የሆንባት መሰለኝ። እኛ ያየነው ቀርባ አለማጫወቷን... ከኛ ጋር ሳቅ አለማድመቋን ብቻ ነው። ግን የተሰጣት የቤት ስራስ? የሚስትነት ሀቁንስ የት ጣልነው? ዱንያ ትምህርት ቤት ናት፤ ነገ ዓዲሉ ይፋረደናል... እሷንም ባጎደለችው ሀቅ እንዳይቀጣት መልፋቷ ጥፋቱ ምን ላይ ነው?

እንደ እናት አክብራ ቡናውን እያቀራረበችላት፤ ተራምዳ ለስድብ እመር ስትል ለምን እናቴን <ተይ> ማለት ተሳነኝ? ለምን ለነቢሎ እንዳልኩት <ስራ በዝቶባት ነው እንጂ ትወድሻለች> ብዬ አልተከላከልኩላትም? ዩስሪ ከኔ ውጪ ባል አላት እንዴ? ያኔ ከጋሼ አንገቴን አጎንብሼ ከወላጆቿ እቅፍ ሳወጣት እንደ አባት መከታ፤ እንደ ወንድም ጋሻ ልሆንላት አልነበረም? በወላጆቿ ቤት... እሷም እኮ እናት ነበራት - ስታለቅስ የምታባብላት። እሷም እኮ አባት ነበራት - ዝምቧን እሽ እንኳን ለማለት የማያስደፍር። እሷም እኮ ወንድም ነበራት- እንኳን ስድብ ሊወርድባት ፥ ቀልዳችን እንኳን ካልተመቻት አብሮ የሚከፋ። ታዲያ ላግባ ብዬ ስወስዳት እነሱን ሆኜ ልሞላላት አልነበረም? እኔ ግን አምጥቼ ለቤተሰቦቼ አጫዋችና ገረድ አደረግኳት። እንደ ህፃን...
918 views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 07:50:48 'በራስ መተማመን'
.
በአንድ ወቅት፣ በሙስሊሙ አለም አንድ የዳኝነትን ሹመት የተሰጠው
መሃይም ሰው ነበር። እና አንድ ቀን ሁለት ሰዎች ተጣሉና ለፍርድ ወደዚህ
ሰው ይመጣሉ። በመጀመሪያ ከሳሹ ክሱን ለዳኛው አቀረበለት። የተናገረው ሁሉ ዳኛውን አሳምኖት ነበርና አምኖ ተቀበለው። “ማሻ አላህ! ሐሳብህ ጥሩ ነው። ወላሂ አንተስ እውነትም ተበድለሃል። እውነቱ ያለው አንተ ጋር ነው!” አለው።

አሁን ተከሳሹ ተራ ደረሰውና ራሱን ለመከላከል፣ ንጽህናውን ለማረጋገጥና
ክሱን ውድቅ ለማድረግ ንግግሩን አቀረበ። አሁንም የዚህ ሰዉየ ንግግር
ዳኛውን አሳመነው። ሃሳቡ ተዋጠለት። ስለዚህ ለዚህኛውም ሰውየ፣ “ትክክል
ነህ፣ ሀቁ ያለው ካንተ ጋ ነው።” አለው።
እውነቱ ያለው ከተበዳዩ ወይም ከበዳዩ ሆኖ ሳለ ለሁለቱም ፍርድ ሰጠ።

ይህን የፍርድ ሂደት ከመጋረጃው ጀርባ ሆና ትክታተል የነበረችው የዳኛው
ሚስት፦ “አንቱ ሰውየ! ምን አይነት ፍርድ ነው የምትሰጡት፣ የመጀመሪያውን አንተ ነህ ትክክል አልኩ፣ ሁለተኛውንም እንደዛው። ይህ እዴት ይሆናል?” አለች። ሰውየውም፣ “ወላሂ፣ አንችም ትክክል ነሽ። የተናገርሽው በጣም ልክ ነው።” አላት።

ግፍ የተሰራበትም ትክክል ነው፣ በዳዩም ትክክል ነው፣ ፍርዱን የነቀፈችውም
ሴት ትክክል ናት። ሌላም አራተኛ ሰው መጥቶ ቢናገር ትክክል ነው። እንዲህ
አይነቱ ሰው እንግዲህ በራሱ ውሳኔ የማይተማመን እና በሰዎች ሃሳብ ብቻ
የሚመራ ሰው ይባላል። በራሱ ሀሳብ የማይመራ እና የራሱ ጠንካራ እምነት
የሌለው ሰው እንዲህ ነው። በሰው ሀሳብ ይመራል፣ ወደነፈሰበት ይነፍሳል።
ዝም ብሎ ማንኛውንም ሰው በጭፍን መከተል ስኬታማ አያደርግም፣ በራስ
መተማመንንም ይገድላል።

በራሱ የሚተማመን ሰው በሰዎች አስተያየትም ሆነ አመለካከት በቀላሉ
አይሸወድም፣ የራሱ የሆነ ጠንቃራ አመለካከት አለው። የሰዎችን ጭብጨባና ማዳመቂያ አይፈልግም። እያንዳንዱን ርምጃ በራሱ ተነሳሽነት ነው የሚወስደው። የሚያደርገው ነገር በሙሉ ትክክል ለመሆኑ ደግሞ የሰዎችን ማረጋገጫና ይሁንታ አይፈልግም፤ ምክንያቱም የሚያደርገውን ያውቃል።
ያመነበትን ነገር ያለ ምንም መሸማቀቅና እፍረት ይሰራል፣ መናገር ያለበትን ይናገራል። ሰዎች ያዘዙትን ነገር ሁሉ እሽ ብሎ አይቀበልም፣ “አይሆንም፣ የራሴ የምሰራው ስራ አለኝ፣ እንደዚህ አላደርግም።” ብሎ የሰዎችን ሃሳብ
ውድቅ ማድረግ ይችላል። “ኖ” ማለቱን ይችልበታል።

በራሱ የሚተማመን ሰው ራሱን ያውቃል። ስለራሱ ጥሩ ግንዛቤ አለው። ጥንካሬውንና ደካማ ጎኑን ለይቶ ያውቃል። ስለራሱም በጎ ምልከታ አለው። ራሱን ይወዳል፣ ራሱን ያከብራል። ለመሻሻል ይጥራል። ተጨባጭ ግቦችን ያስቀምጣል፣ ተጨባጭ ውጤቶችን ይጠብቃል። እንዲሁም የሰዎችን ትችት
በቀላሉ ተቋቁሞ ያልፋል። በራሱ የሚተማመን ሰው እንግዲህ እንዲህ ነው። የሚያወራውንም ሆነ የሚሰራውን ነገር ያውቃል።

በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች፣ ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ ከፍ ያለ ነው።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ህይወትን በደስታ ይኖራሉ። ሁሌም ለህይወት ጥሩ የተነሳስሽነት ስሜትም አላቸው። በራስ መተማመን የሌለው ሰው ደግሞ በተቃራኒው ነው። ለራሱ ክብር የሌለው ወይም በራሱ የማይተማመን ሰው
በሌሎችም ዘንድ ዋጋ እንደሌለው ያስባል።
.
.

@islllllaamic
1.1K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:20:43 ከሙሉነት ጥቂቱን...4
(Team Huda)
:
#የማህበራዊ_ህይዎት_አመላካች
የኛ ነቢ ሙሉ ናቸው ስንል የምናወጣባቸው አይብ ስለሌለ ነው። በምላሳቸው የወጣን በተግባር ለመከወን የሚቀድማቸው አልነበረም። ማህበራዊ ህይዎት...መተዛዘንና መተሳሰብ ካስማዎቹ ናቸው። ይህ የሚታየው ደግሞ 'የኔ' ከምንለው ስብስብ ውጪ ካለ ሰው ጋር ባለን መስተጋብር ነው። ከኔ ሀይማኖት...ብሔር...ቀለም...ሌላም ሌላም።
የኛ ረሱል አይሁድን ጀናዛ ቁመው አላሳለፉምን? ሲነገራቸውስ <ፍጡራንን ለፈጣሪያቸው ስትል ውደድ> የሚል ዘመን አይሽሬ አብረቅራቂ መርህን አልነገሩምን?

ደግሞ ሰሃባዎች ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም ቢጠናባቸው... እነሱን እንዲረግሙላቸው ወደ ነብያችን ያቀናሉ። ብለው ያሏቸው ግን ከሳቸው ሙሉነት የሚጠበቅ...ለኛዋ ነፍስ የሚከብደውን ነው... <እኔ ለእርግማን አልመጣሁም ለእዝነት እንጂ። ጌታዬ ሆይ እነርሱ አያውቁምና አቅናቸው።>

ከዚህ ጣፍጭ ባህር አንድ እናክል:
የምናውቀው አብደላህ ኢብን ኡበይ ሙናፊቅ ነበር። መሪያቸውም ጭምር። ያጠፋውን የመፅሀፍ ገፆች ላይ አናጣውም። በተቃራኒው ልጁ እጅግ ታሚኝና ዓቢድ ነበር። አብደሏህ በሚሞትበት ወቅት ልጅዬው ነብያችን ጋር መጥቶ ቀሚሳቸውን ጠየቀ-ለአባቱ መገነዣነት። የልጁን ቀልብ ላለመስበር ...የተወዳጅ ባለቤታቸውን የእናታችን ዓኢሻን ስም ያጎደፈውን ሰው እንዲገነዝበት ሳያቅማሙ ሰጡ። ዓጂብ!!

@islllllaamic
1.4K views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ