Get Mystery Box with random crypto!

'እንተዛዘብ' (ነጃት ሀሰን) ይህ ከብዙ በጥቂቱ አብዛኛዎቻችን አንደበት ላይ የማይጠ | 🍂ISLAMIC TEAM🍂

"እንተዛዘብ"
(ነጃት ሀሰን)

<ኤጭ! ጨው በዝቷል>
<ውሃ ውሃ ኮ ነው ሚለው>
<እጅ እጅ ብሏል>
<እንጀራው አይን የለውም እንዴ?>
ይህ ከብዙ በጥቂቱ አብዛኛዎቻችን አንደበት ላይ የማይጠፋው ምግብን ማነወር ነው። አመስግኖ መመገቡ ቀርቶ እሬት እንደበሉ እየተንገሸገሹ መዋጥማ አመላችን ሆነ። ብዙ አመት ወርቅ ሲያበሉን የነበሩ እጆች በቀኖች አንዱ ውስጥ ሳት ብሎ አንድ ነገረ ቢረሳ ወይ ቢያበዛ አሳሩን እናበላዋለን።
ምግብን እንድናነውር ከሚያደርገን ነገር ዋነኛው ሳይርበን መመገባችን ነው። "ርቧችሁ እንጂ አትመገቡ" የሚለውን ነብያዊ አስተምህሮ ወደ ጎን ገፍተን ከከርስ ላይ ከርስ ለመጨመር እንሮጣለን። ቢርበንማ ጨውን ለማጣጣም ጊዜ በጠፋ፤ ኧረ እንዲያውም ምን እየበላን እንደሆነ ለማወቅም ግድ የለን።
አንድ የሰማሁትን ምናልባትም እናንተም የምታውቁትን ታሪክ ላካፍላችሁ:-
ስምንት አመታትን በፍቅር በጋራ ያሳለፉ ባልና ሚስት ናቸው። ከእለታት በአንዱ ቀን ባል ከስራ ሲመለስ ሚስት ምግቡን አቀራረበች። ልክ መጉረስ ስትጀምር ግን ጨው ማድረግ እንደዘነጋች ገባት። ቀና ብላ ባሏን አየችው። እንደሌላው ጊዜ ፊቱ ሳይቀየር እየተመገበ ነው። አሁን አሁን ተቆጣኝ ብላ እንደተሳቀቀች በልተው ጨረሱና እቃውን አነሳሳች። እሱ አሁንም ምንም የተለየ እንቅስቃሴ አላደረገም። ስላላስቻላት ጠየቀችው። "ሀያቲ ስምንት አመታት ሙሉ የሚጣፍጥ ማዕድ አቅርበሽልኛል፤ የዛሬው ግን ይለያል የጫጉላ ሰሞን ጊዜያችንን እንዳስታውስ አደረግሽኝ" አለ ይባላል። አቦ እንዲህ አይነት ባል ይስጣችሁ! ( አቤት ሴቶች አሚን ለማለት ስትቀዳደሙ እንዳትሰባበሩ)
ወደ ርዕሳችን ስንመለስ ከጠገብን በዝምታ መመገብ እናቁም እንጂ የሰሩልንን አናሳቅ። ኧረ ጎበዝ ትዝብት ነው ትርፉ። ረሡላችን (ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም) በሃያታቸው አንዴም ምግብን ሲያነውሩ ተሰምተው አይታወቁም።
ታዲያ እኛ ማነን?
@islllllaamic