Get Mystery Box with random crypto!

#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም                   አሚር ሰይድ       | ISLAM IS UNIVERSITY

#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም
                  አሚር ሰይድ


            
#የመጨረሻዉ_ክፍል



   #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ



ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
  ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር  ነዉ ፡፡


ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ

አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን  የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል  ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም  ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...

#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት  ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡

አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ

ከነዚህ ዉጭ  3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ

----- ጂን ሲናገር  ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡

ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ  ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ  ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡


  #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ #በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ      
         
#ምን_ማድረግ_አለበት

      ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡  ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡  ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡  

  በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት  ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡

አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ  ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ ፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡

#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...

መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።

እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
  ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።

የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።