Get Mystery Box with random crypto!

ካልጠፋ ያጠፋሻል : መቼም በዚህ ዘመን smart phone ያልያዘ ሰው ማግኘት እየከበደ ነው… | ISLAM IS UNIVERSITY

ካልጠፋ ያጠፋሻል

:
መቼም በዚህ ዘመን smart phone ያልያዘ ሰው ማግኘት እየከበደ ነው… ታዲያ በነዚህ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በታጨቁት ዘመናዊ ስልኮች ውስጥ ያለው ብቸኛ አገልግሎት ፎቶ ማንሻ ካሜራ ብቻ ይመስል ሁሉም ሰው በውቡ ካሜራ ቀንና ማታ እራሱን ሲቀርፅ እራሱን ሲያይ ታያቸዋለሽ… በዚህ በፎቶ

ጉዳይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽና በታማኝነት ለራስሽ መልሱን መልሺ… በስልክሽ ካሜራ በአንድ ጊዜ ስንት ፎቶ ተነተሽ ስንቱ ፎቶ አስጠልቶሽ ታጠፊዋለሽ? መልሱ አንቺ ጋ ይቆይ… እኔ በራሴ ልምድ አስር ፎቶ ብትነሺ ሶስቱን ብትወስጂው ነው ሰባቱ አስጠልቶሽ ይጠፋል Delete

… አስቢው የራስሽን አካል የራስሽን ፊት እሱንም በውብ ቴክኖሎጂ አሳምሮ አስወቦ አንስቶሽ ያስጠላሻል አያምርም ብለሽ Delete ታደርጊዋለሽ

አንዳዱን ደሞ Edit ታደርጊዋለሽ ፎቶሽ ውስጥ የገባውን የማትፈልጊው ቆርጠሽ ታወጫለሽ ቆንጆዋን ፓርት ብቻ መርጠሽ ታስቀምጫለሽ… ይሄ ሁሉ ልፋት ቆንጆ ፎቶዎች እንዲኖረን ነው ሌላ ምንም የተለየ ጉዳይ የለውም… በቃ

በወረደ ቋንቋ ሲገለፅ የራስሽን የተዋበ ፎቶ ለራስሽም ሆነ ለሌሎች እያሳየሽ ልትፅናኚ ነው

ካሜራው ደሞ ቦታውን አስተካክለሽ አንሳ ካልሺው ያነሳል ይሄ ጥሩ አይደለም ይሄ ጥሩ ነው እያለ አስተያየት አይሰጥም ያየውን ያነሳል በቃ ያ ስራው ነው።

አንድ ነገር ግልፅ ነው አንቺ ከኖርሽ በህይዎት ካለሽ ከተነፈስሽ ከተራመድሽ ብዙ ነገር ያጋጥምሻል… ህይዎት ደሞ ብዙ ጉዳዮችን በካሜራዋ ትቀርፃለች እና ይቺ የህይዎት ካሜራ ስራዋ ያየችውን ማንሳት ነው ።

ለህይዎትሽ ይጠቅማል ያምራል አስተያየት አትሰጥም ማንሳት መቅረፅ በአእምሮሽ gallery ማስቀመጥ ስራዋ ነው።
ታዲያ አንቺ የራስሽን ህይዎት መርምሪው እስኪ በማትፈልገው ነገር ተሞልቶዋል?

ያልመረጥሽው ያልወደድሽው ነገር ከቦሻል? አዎ ከሆነ መልስሽ… በቃ አንቺ ህይዎት በውብ በካሜራዋ አንስታ የሰጠችሽን ሁሉ ተቀብለሽ በኑሮ galleryሽ ውስጥ አስቀምጠሻል ማለት ነው… መርጠሽ አላውጣሽም

አላጠፋሽም Delete አላደረግሽም የአእምሮሽ storage በትርኪ ሚርኪ ጉዳይ ሞልቶ storage full የሚለውን notification እየላከልሽ ነው ማለት ነው።

ይሄ ቀላል አካሄድ ነው ህይዎትሽን እንደካሜራ ቁጠሪያት የአንቺ እግር የደረሰበትን ሁሉ ልቅም አድርጋ አንስታ ወደ አእምሮሽ ታስቀምጣለች

ህይዎት ለአንቺ አትመርጥልሽም አንቺ ነሽ ህይዎትሽን መምረጥ ያለብሽ… የህይዎት ካሜራ ከመቅረፅ ውጪ ስራ የለውም ይሄ ጥሩ ይሄ መጥፎ ነው እያለ አይመርጥልሽም።
ህይዎትሽ ቆንጆ gallery እንዲሆን ከፈለግሽ ምርጥ ምርጡን መርጠሽ አስቀምጭ።

ብዙ ሰው ህይዎቱን ባልመረጠው ባልወደደው ቦታ ያገኛዋል… ለምን? ብሎ አይጠይቅም እድሌ ነው ብሎ ማማረር የባሰ አዘቅጥ ውስጥ መግባቱን ይቀጥላል… ለምን እዚህ ተገኘው? ይሄ ቦታዬ ነው? ከማን ጋር ነው ያለሁት? ኑሮዬ እኔን ይመስላል? እኔስ ኑሮዬን እመስላለው? ብለሽ መጠየቅ አለብሽ

አለበለዚያ የህይወት ካሜራ ቀርፃ የሰጠችሽን ብቻ ተቀብለሽ እየኖርሽ ነው።
እንደዚያ ከኖርሽ ደሞ ህይወት ምሬት ለቅሶ ነው የምትሆንብሽ።

ቀላሉ መንገድ Delete ማድረግ ነው በቃ የማይሆን የማያዋጣ የመሰለሽን ያላማረሽን Delete አድርጊ ቆንጆ ህይዎት ይኖርሻል።

አንዳዱ ደሞ ሳትፈልጊው ና ሳትይው ወደ ህይወትሽ ይገባል እሱን ቆርጠሽ Edit አድርገሽ ማውጣት አለብሽ አለበለዚያ galleryሽ ውስጥ ውጥንቅጥ ይበዛዋል virus ያጠቃዋል… ከሁሉም ከሁሉም መፍራት ያለብሽ

የህይዎት storageሽን በማያምር በማትፈልጊው ነገር ሞልተሽ

የሚያምር የምትፈልጊው ነገር ወደ ህይዎትሽ ሲመጣ ቦታ ይሞላብሻል ማስቀመጫ ታጫለሽ ያኔ አዪዪዪ እፈልገው ነበር ግን ትያለሽ…
ለአንቺም ለሰሚውም ግልፅ አይደለም ወይ ደሞ ለመግለፅ ይከብዳል ከአፍሽ (ከግን) ውጪ ማውጣት ሳይከብድሽ በፊት Delete አድርጊ አለበለዚያ ህይዎት እራሷ Delete ታደርግሻለች…

Eku Abdellah ወሎየዋ


Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group