Get Mystery Box with random crypto!

ግዙፉ የቻይና ኩባንያ ለሠራተኞቹ በአዞ በተሞላው ሀይቅ ላይ ጉዞ አሰናዳ። እየዋኘ አቋርጦ ከአንደኛ | ISLAM IS UNIVERSITY

ግዙፉ የቻይና ኩባንያ ለሠራተኞቹ በአዞ በተሞላው ሀይቅ ላይ ጉዞ አሰናዳ። እየዋኘ አቋርጦ ከአንደኛው ጫፍ አዞዎችን ተሻግሮ ወደሌላኛው ጫፍ በህይወት ለሚደርስ ሰው አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚሸልም ካምፓኒው ተናገረ።


ሁሉም ሠራተኞች ወደ ሐይቁ መዝለልን ፈሩ። "ውድ ነፍሳችን ዓይናችን እያየ በአዞ ከሚበላ ሺህ ጊዜ ድህነታችን" እያሉ ባሉበት ቆመው ቀሩ።

በድንገት ከመሐላቸው አንዱ ሸሚዙን ከነከረባቱ እንዳጠለቀ ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሐይቁ ዘለቀ። በእጆቹ ውሀውን እየቀዘፈ በአዞዎች መሐል ያለ ምንም ፍርሀት መዋኘቱን ቀጠለ። የስራ ባልደረቦቹ በድንጋጤ ዓይናቸውን አፈጠጡ። ሀይቁን ሲሻገር እየተመለከቱ በአግራሞቱ አንገታቸውን ነቀነቁ።

በዚህ ቅፅበት ያ ምስኪን ሰው ሚሊየነር ሆነ። በቤተሰቡም በመንደራቸውም ነዋሪዎች ዘንድ ዝናው ናኘ።

ምን እንደገፋፋው ሀይቁ ውስጥ ያለ ፍርሀት እንዲጠልቅ ምን እንዳነሳሰሰው ሲጣራ ሚስቱ ሆና ተገኘች። በጭቅጭቋ በግኖ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ራሱን ለማጥፋት አስቦ ኖሯል ዘሎ የገባው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
"ከስኬታማ ወንድ ጀርባ አንዲት ሴት አለች" የሚለው ታዋቂ አባባል የተሰማው የዛኔ ነው ይላሉ።

Join
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  @IslamisUniverstiy_public_group