Get Mystery Box with random crypto!

የኢሻ ሰላት ወቅት ነው እስልምናን የተቀበለው። ሻወር ከወሰደና ሸሃዳን ከያዘ በኋላ ዒሻ ሰላቱን ሰ | ISLAM IS UNIVERSITY

የኢሻ ሰላት ወቅት ነው እስልምናን የተቀበለው። ሻወር ከወሰደና ሸሃዳን ከያዘ በኋላ ዒሻ ሰላቱን ሰግዶ ስለ እስልምና ለማወቅ ኮምፒተሩን ከፍቶ እያነበበ ለሊቱን አሳለፈ።


ቅርብ ጓደኛሞች ስለነበርን የሱብሒን ሰላት ሰግጄ ልዘይረው ወደ ቤቱ አቀናሁ። ከመንደራቸው አቅራቢያ ስደርስ የለቅሶ ድምፅ ሰማሁ። ስሙን እየጠሩ ያለቅሳሉ። አደጋ መከሰቱን አስተዋልኩ ድንጋጤ ወረረኝ። ተብረከረኩ፡፡ ክፍቱን በር አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ።

አባቱን ፊት ለፊት አገኘኋቸው፡፡ ጓደኛዬ ምን ሆነ በማለት ጠየቅኳቸው። ከዓይናቸው ዕንባ ዱብ ዱብ እያለ ጓደኛህ ሞቷል አሉኝ። ማልቀስ ጀመርኩ ያሳለፍናቸው ጊዜያት ታወሱኝ። ወዳለበት ክፍል አመራሁ፡፡ በሩን ከፍቼ ስገባ ለሱጁድ በግንባሩ እንደተደፋ ነው የሞተው:: ክፍት ወደነበረው ኮምፒውተር ዓይኖቼን ስወረውር ስለ ሑረል ዐይን ቁንጅና የሚገልፅ ጽሑፍን ተመለከትኩ። ስለ ጀነት ፀጋ በውስጧ ለሙዕሚኖች መደሰቻ አላህ ስላዘጋጃቸው እንስቶች እያነበበ ሳለ ነበር የሱብሂ ወቅት ደርሶ እየሰገደ ሱጁድ ላይ ሆኖ ሞተ፡፡

ጌታዬ ሆይ ባልሰራበት እንኳ ወደ መልካም ነገር የጠቆመ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ