Get Mystery Box with random crypto!

አላገባም ነገር ግን ከዕውቀት ጋር ጎጆ ቀልሶ 450 መጻሕፍትን ወልዷል። ከ937 በላይ ጽሑፎችን በ | ISLAM IS UNIVERSITY

አላገባም ነገር ግን ከዕውቀት ጋር ጎጆ ቀልሶ 450 መጻሕፍትን ወልዷል። ከ937 በላይ ጽሑፎችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ፅፎ ለንባብ አብቅቷል።

እጅግ ሲበዛ ራሱን ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ምሁር ነው። በሀገረ ፈረንሳይ ከ40,000 በላይ ሰዎችን አስልሟል። 22 ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ይናገራል።

ከፓኪስታኑ ፕሬዝዳንት ከሙሐመድ ዚያኡልሐቅ ከከፍተኛ ክብር ጋር ለመልካም ስራዎቹ ልዩ ስጦታ ተበረከተለት እሱ ግን
"ጠፊ በሆነችው በዚህች የዱንያ ዓለም ሽልማትና ስጦታ ከተቀበልኩማ በዘላለማዊው መኖሪያ በአኺራ ምን አተርፋለሁ" በማለት የተበረከተለትን ስጦታ አንድ ሚሊዮን ሩፒ የሚያወጣውን ሽልማት በኢስላማባድ ለሚገኘው የእስልምና ጥናት ተቋም አበረከተ።

በ1994 ንጉሥ ፈይሰል ሽልማት ቢልኩለት
"የሰራሁት መልካም ስራ ለብቸኛው አምላክ ለአላህ ብዬ ነው ኢኽላሴን በሽልማት ስም አታበላሹብኝ" ሲል ተናገረ።

እርሱ በእርግጥም ለአኼራው ሰንቆ በ94 ዓመቱ ከጌታው ጋር የተገናኘው ሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዱላህ አል-ሀይድራባዲ አል ሂንዲ ነው።