Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን ለ1443ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን! የዒ | ISLAM IS UNIVERSITY

እንኳን ለ1443ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!
የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓልን ስናስብ ቀድሞ ወደ አዕምሯችን የሚመጣው በመንፈሳዊውም ይሁን በሥጋዊው ዓለም ታላቅነት የሚመጣው በፈተና ውስጥ በጽናት ለማለፍ በመቁረጥ እንደሆነ ነው። ነብዩ ኢብራሒም በአላህ (ሱ.ወ) ታዝዘው ልጃቸው እስማኤልን ለመሰዋት ሲነሱ አጋጣሚው ለአባትም፣ ለልጅም ቀላል አልነበረም። እጅግ ከባድ የሆነ የስሜት ፈተና ሲገጥማቸው ነበር። ከአባትነት ስሜት ከሚመነጨው ፈተና ባለፈ፣ ጠላት ሸይጣንም፣ በእርጅና እድሜያቸው ያገኙትን ልጅ ለመሰዋት መዘጋጀታቸው ጅልነት መሆኑን እየጠቀሰ ከመንገዳቸው ሊያስቀራቸው በተደጋጋሚ ፈትኗቸዋል። ነብዩ ኢብራሂምግን አልተረቱለትም። መስዕዋት የሚሆነው ልጃቸው እስማኤልም የገዛ ፍርሃቱን አሸንፎ፣ አባቱ የአላህን ትዛዝ እንዲፈጽሙ ሲያበረታቸው ነበር። በመጨረሻም ልጃቸዉን ሊያርዱ ሲዘጋጁ በምትኩ በግ አወረደላቸዉ።

تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

人 ★* 。 • ˚* ˚
. (_ _) * ዒድ * ★
. ┃口┃ * mubark *
. ┃口┃★ * ***. . *˛•
. ┃口┃★ * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛* 人 •˛˚ *
. ┃口┃ .-:'''"''''"''.-.
. ┃口┃ (_(_(_()_)_)_)
┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃. ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. 三_三三三三三
አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን !!

እንኳን አደረሳቹ !

የአረብገንዳ መስጂድ የመረጃ ዘርፍ