► #ቁርአንን_ለመሀፈዝ_የሚጠቅሙ_6_ምክሮች ① ►ኢኽላስ የሁሉም ነገር ቁልፍ ነው ስራ ላይ ኢማን እና ኢኽላስን ማጣት ትልቅ ክስረት ውስጥ ያስገባል ። የለፋህበትን የደከምክበት ሁሉ በአንዴ ያወድምብሃል ። ስለዚህ ልብህን ተጫንና በውስጥህ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ‥ ኢኽላስ እያልክ ወደ 2ተኛው ምክር‥ ②► አላማ አንድን ነገር ለመስራት አላማዬ ብለህ ከያዝክ ምንም ነገር አላማህን ከማሳካት አያግድህም ። ብቻ አንተ ውስጥህ ላይ ያለውን ፍላጎት ፣ ቆራጥነት ፣ ሀይልን እና ምኞትህን ቀስቅሰህ እችላለሁ በልና ወደ 3ተኛው ምክር‥ ③ ►ትኩረት ዛሬ ላይ መለኩል መውት መጥቶ በእርግጠኝነት ከ2 ወር በኋላ ትሞታለህ ቢልህ ምን ታደርጋለህ?? - አንዱ በ2 ወር ቁርአን ሀፍዜ እጨርሳለሁ ይላል ። ሌላው ደግሞ በ1 ወር ሀፍዤ እጨርስና ቀሪውን ኢባዳ ብቻ አደርጋለሁ ይላል‥ ይህ ሁሉ ችሎታ እና ሀይል አሁን የት አለ? ๏ ሰው በተሰጥኦ ምናምን ይለያል ብለህ አታስብ ። በተወሰነ % ቢኖርም ግን ሁላችንም ውስጥ ምኞት ፣ ፍላጎትና ጉጉት አለ ። እያንዳንዳችንም ፍላጎታችን ላይ መድረስ እንችላለን ብለህ እራስህን አሳምነህ ወደ 4ተኛው ምክር‥ ④ ►የምትሀፍዝበትን ጊዜ ወስነህ ለየው አብዛኛውን ጊዜ ቁርአን ለመሀፈዝ የተሻለ ጊዜ ነው የሚባለው ሱሁር የሚበላበት ጊዜ ነው ። ከዛ ቀጥሎ ከፈጅር ሰላት በኋላ ነው ። ሱሁር ላይ የተሻለበት ምክኒያት : የሰው ልጅ በዛ ሰአት ከእንቅልፉ ሲነቃ አእምሮው ለመቀበል ክፍትና ዝግጁ ስለሚሆን ነው ። ⑤ ►አንድ አይነት ሙስሀፍ/ቁርአን ብቻ መጠቀም የአንድ አንድ ሙስሀፎች ገፅ አቀማመጥ ይለያያል ። እዚህኛው ሙስሀፍ ገፅ ላይ ያየኸው አንቀፅ በዛኛው ሙስሀፍ ገፅ ለይ ደግሞ ሌላ አንቀፅ ሊኖር ይችላል እና ሁሌም የምትቀራበትን ሙስሀፍ አዘጋጅ ። ⑥ ►ወንጀሎችን መራቅ የወንጀል ፅልመት እና የእውቀት ብርሃን በአንድ ቦታ ላይ ሊሰበሰቡ አይችሉም ። - የሰው ልጅ ወንጀል ሲሰራ ወንጀሉ ሀዘን ፣ ጭንቀት እና የመሰሰሉ ነገሮች ስለሚያመጣበት ሀሳቡ ሁሉ ይቀየርና ከበጎ ነገራቶች ያርቁታል ። ስለዚህም በተቻለን አቅም ወንጀል ከሚባሉ ነገሮች መራቅ ይኖርብናል ። ጥቆም : በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ @FurqanOnlineQuran ◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈ ጆይን : ሼር ፣ ሼር ፣ ሼር بـــارك الـلــه فـــــيــــــكـــم ... https://t.me/furqan_school https://t.me/furqan_school 2.3K viewsFurqan Online Quran, 08:46