Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ዳዕዋ

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_best_profile_pics — ኢትዮ ዳዕዋ
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_best_profile_pics — ኢትዮ ዳዕዋ
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_best_profile_pics
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.40K
የሰርጥ መግለጫ

😍እንኳን ወደ ማሒር ቦንዳ ቻናላችን በሰላም መጡ 😍
→ዘመን ተሻጋሪ ውበት አናጋሪ ልብሶችን እንልበስ
አድራሻችን (ባቲ ) ነጃሺ መካከለኛ ክሊኒክ 2ፎቅ ላይ ያገኙናል
ለበለጠ መረጃ
☎ 0910597402
☎ 0994011759
☎ 0953747424
በመደወል ያናግሩን።
inbox me 👇
@AbuMahir7984

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 22:12:13 ኢማነኘው ገበሬ ክፍል ሁለት


አፍንጫህ ስረ ሁነው አብረውህ የኖሩትን "እጅግ ብዙ አውነቶችን ማየት አልቻልክም አንተን ጨምሮ ተቆጥረው የማያልቁትን ሌሎች ነገሮች ሁሉ ትተህ ይቺን ፀሀይ እና ምሽት ላይ ብርሀን የምትሆነንን ጨረቃ እንዲሁም እነዚህ ከፊትህ የምትመለከታቸው ውብ አበቦችና ዛፎች የፈጠራቸው አንድ ሀይል መኖሩን መቀበል ግን ተሳነህ በማለት ተናገረ እንግዳውም ከገበሬው የሰማቸውን ቃላት እያሰላሰለ ላፍታ ያህል ከቆየ ቡሀላ በጣም የሚገርም ነው በአሁኗ ቅፅበት ቅንጣት ታህል ማየት እና ማሰብ የተሳነኝ ደደብ የሆንኩ ያህል ነው የተሰማኝ በዚች አፍታ ግዜ ውስጥ የተገለፀልኝ እጅግ የገዘፈ ማወቅ የሚሹና
ዝግጁ ከሆኑት ግን ከምንም በላይ የቀለለ እውነት ነው ከአንደበትህ የወጡት ቃላት ሁሉ ትክክል ናቸው ሀያሉን ፈጣሪ በአይናችን ማየት ባንችልም የርሱን መኖር ለማረጋገጥ የትም መሄድ አያሻንም
ራሳችንን እና ዙሪያችንን ብቻ መመልከት ከበቂ በላይ ነው አለ ስለ አላህ መኖር ለሚጠይቁኝ እና ስለ ጌታ መኖር አለመኖር ለሚከራከሩ ሰዎች መልስ የለኝም እንዲህም እላቸዋለሁኝ እኔ መሀይም ነኝ እና ከኔ መልስ አትጠብቁ ባይሆን ሂዱና ኤሊን ጠይቁ ድንጋይ ማን አሸከመሽ ለምንስ ተሸከምሽ በሏት ከእባቡ ጎራ በሉና መርዝ
ያህል ነገር በአፍ ይዞ መዞር ለቴና ጥሩ ነው ወይ በሉት አጭር ዱላ ብቻ ከሚንቀሳቀስ ከአይነ ስውር ተጠጉና ማን እንደሚመራው ጠይቁት ከበረንዳ አዳሪው ድረሱና መኖሪያህ የት ነው ከቆሻሻ ገንዳ እየበላህ በብርዱና ከሌጣው መሬት ላይ እየተኛህ በሽታ እንዴት ሳያገኝህ በሉት ጭው ካለው በረሀ ውጡና እዛ የሚገኘው እንስሳት እና እፅዋት ምን በልተው ምን ጠጥተው እንዳደጉ ጠይቋቸው በሰማይ ላይ የሚበርን አሞራ ማን ይይዝሀል በሉት ከመንገድ ዳር የሚተኛውን የኔ በጤ ማነው ጠባኪህ በሉት እኔን አትጠይቁ እኔ ለማስረዳት ቃላት ያጥረኛል እና ሂዱና በቅሎን ጠይቁት ምነው በሴትነትሽ አለመውለድሽ በሏት አዲሱንም ህፃን አነጋግሩ ከናትህ ማህፀን ስትወጣ ማን አስለቀሰህ ምንስ አስለቀሰህ የናትህን ጡት ማን አሳየህ ወተት መያዙን ማን አሳወቀህ በሉት ንቢቱንም አትለፉ በምን አቅምና ጉልበትሽ ነው እሄንን ጣፋጭ ማር የጋገርሺው በሏት ላሚቷንም በደምና በፈርስ መሀከል ሁኖ ሳለ ጡቷን ቢቆርጡት ደም እንደሚወጣ እየታየ ነጩ ወተት ከየት መጣ በሏት ቫይክቴሪያ ቻይረስ በአይን የማይታይ እረቂቅ ሁኖ ሳለ በምን አቅሙ ሰውን ፈጀ አሳውስ በውሀ ውስጥ ሳይታፈን ኖረ እነፀ ለማስረዳት ብቃት የለኝም ጥያቄውን ለራሳቹህ አቅርቡ ደኘናውን ማን ያንቀሳቅሰዋል ዝናቡንስ ማን ይመጥናል ባህሩንስ ማን አገራው ከአፈር በታች ያዋለውን ስፍሪ ማን አበቃለት ጥቅጥቅ ካለው ደን ውስጥ ጎጆዋን የቀለሰች ወፍ ልጇ የሚገኝበትን ዛፍ በምን መልኩ ልታውቅ ቻለች ንብንስ እረጅም እርቀት ከተጓዘች ማን ወደቀፎዋ ማን መራት ሸንበቆ እረዝሞ እረዝሞ ምነው ፍሬ አለማፍራቱ ሚዳቋዋስ በሂወት ዘመኖ ላንዴማ ወልዳ መብከኗ እኔ በቂ መልስ የለኝም በአፈጣጠራቹህ አስተውሉ እራሳቹሁንም ጠይቁ አላህ ሱ·ወ እንዲህ አለ ወፊፊ አንፉሲኩም አፈላ ቱብሲሩን
በነፍሶቻቹሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ ታዲያ አትመለከቱምን ሱረቱል ዛሪያት አንቀፅ 21
ወገኖቼ እስቲ እንጠይቅ ምን ነበርን የት ነበርን በምን ውስጥ አለፍን የት ነን እንዴት ነን መጠየቅ ለፈለገ ለማመንም ፍቃደኛ ለሆነ ሰው አምላክን የማግኛ ጥያቄዎች ብዙ ናቸው እንጠይቅ ለምን እንሰፋለን ከምንም ተነስተን ከደካማ ፈሳሽ ተነስተን ከአጥንት ተሰካክተን ስጋ ቆዳ ለብሰን እሩህ ተነፍቶብን ከጠባቧ ከጨለማ አለም ወደዚ አለ የመጣን በሂደትም ሰው የሆንን ፉጡራን ነን እራሳችንን እንዳልፈጠርን እናውቃለን የሰዎች ስሪት የፋብሪካም ውጤት እንዳልሆንን አይጠፋንም አላህ ሱ,ወ እንዲህ አለ
አምም ኩሊቆ ሚን ገይሪ ሸይኢን አም ሁሙል ካሊቁን

ወይስ ያለ አንዳች ፈጣሪ ጠፈጠሩ ወይስ እነርሱ ፈጣሪዎች ናቸውን ስረቱል ጡር አንቀፅ 35
ታዲያ ምነው ማመኑ ከበደን መቀበሉ ቆረቆረን
አላህ ማነው እንበል ጠይቀንም እንመን
አላህ ሱ,ወ እንዲህ ይላል

አላሁለዚ ከለቀኩም ሚን ጧዋፊን ሱመ ጀአላ ሚንባአዲን ጧዋፊን ቁወህ ሱመ ጀአለ ሚን ባእዲን ቁወቲን ዷአፈን ወሸይበህ የቅሉቁ ማየሻኡ ወሁወል አሊሙል ቀዲር

አላህ ያ ከደካማ ፍትወት ጠብታ የፈጠራቹህ ነውከዚያም ከደካማነት ቡሀላ ሀይልን አደረገ
ከዚያም ከብርቱነት ቡሀላ ደካማነትን እና ሽበትን አደረገ የሚሸውን ይፈጥራል አሱም አዋቂው ቻይ ነው ሱረቱ ኑም አንቀፅ 54

ሰማይ ያለ ሙሶሶ መቆሙ ምድርም ያለ ችካል አለመወጠሯ ፀሀይ ያለ ገመድ መርጋቷ አላህ ስለ መኖሩ ምንም ፍንጭ አይሰጥም ትላላቹህን የሰው ልጅ ሁለቴ ህፃን መሆኑ ንብረትና ሀብት ኑሮት ሳለ ባዶ እጁን እቺን አለም መሰናበቱ ብቻውን ወደ መቃብር ጉድ ጓድ መወርወሩ የሰው ልጅ መድረሻ እንዳለው አያመለክትምን የሂወት ትርጉም እና ይቺ አለም የመገኘት ሚስጥሩ መቶ መሄድ ኑሮ መሞት ሞቶ መበስበስ በስብሶ አፈር መሆንና በዚያው መቅረት ብቻ የሚል ካለ በርግጥም ትልቅ ስህተት ላይ ነው
ክፍል ሶስት የመጨረሸው ክፍል ይቀጥላል•••••••
136 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, edited  19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:44:14 《 አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ 》
በጥንት ዘመን„ በመልካም ስብእናው የሚታወቅ አንድ ገበሬ ነበር ገበሬው ብዙኡን ግዜ, የሚያሳልፈው በእርሻ ማሳውስጥ ተጠምዶ ነው
ፀሀይ ወታ እስክት ጠልቅ ድረስ ያለምንም ድካም በከፈተኛ ትጋት የግብርና ተግባሩን ያከናውናል በስራው መካከል ግን የዘወትር ሰላቶቹን ያላንዳች ዝንጋታና ቸለተኝነት ወቅቱን ጠብቆ ነበር የሚያከናው ነው ከለታት አንድ ቀን ማምሻ ላይ እንደተለመደው በልምላሜ ካማረው ይዞታው ውስጥ ከሚገኘው ማሳው ላይ በትጋት እየሰራ ሳለ
ከማሳው እራቅ ብሎ መንገድ ዳር የወደቀ ሰው ተመለከተ ሰውየው በህመም እየተሰቃየ እራሱን መቆጣጠር ተስኖት ነበር እሄንን የተገነዘበው ገበሬ
ሰውየውን ከወደቀበት አቅፎ በማንሳት ትካሻው ላይ ተሸክሞ ወደ ቤት ወሰደው አስፈላጊውን እርዳታና እንክብካቤ አደረገለት ከህመም ስቃዩ እፎይታን ያገኘው ሰው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰደው ገበሬው የሱብሂ ሶላት ለመስገድ ከእንቅልፉ ሲነቃ እንግዳውን አብሮት ሊሰግድ ዘንድ ቀሰቀሰው እንግዳው ግን እንደማይሰግድ ተናገረ ገበሬውም ምክንያቱን ምን እንደሆነ ጠየቀው በዚህ ግዜ እንግዳው የምሰግድለትን አላህ አልችልም በመሆኑም በማላየው አካል መስገድ ለኔ ምንም ትርጉም የለውም በማለት ተናገረ አጂብ ገበሬው በእንግዳው ንግግር ውስጡ እየተገረመ ሌላ ምላሽ ሳይሰጥ ሰላቱን ሰግዶ ወደተለመደው ተግባሩ አመራ በቀጣይ ቀን እንግዳው ከህመሙ እያገገመ መምጣቱ እና ጤንነቱ እየተመለሰ መሆኑን በመግለፅ ወደ ቤቱ መሄድ እንደሚፈልግ ተናገረ ገበሬዉም እስከ መንገድ ድረስ ሊሸኘው አብሮት ከቤቱ ወጣ
ሁለቱም በዝምታ ተውጠው ጥቂት እንደተራመዱ
የእንስሳ ዱካ ተመለከቱ በዚህ ግዜ እንግዳው ይህ ዱካ የነብር ነው ሲል ተናገረ ገበሬውም ይህ ዱካ የነበር ነው ብሎ ለመቀበል ያስቸግረኛል ምክንያቱም በዚህ መንገድ ምንም አይነት ነብር ሲያልፍ አላየሁም አለ እንግዳው ሰው በገበሬው ንግግር ተገርሞ ምን ማለትህ ነው በዚህ መንገድ ነብር አላለፈም እያልክ ነው በዚህ መንገድ ነብር ማለፉን ለመናገር እነዚህ ዱካዎቹ በቂ ማስረጃ አደሉም የሚል እምነት አለህ ሲል ገበሬውን ጠየቀው ገበሬውም ልቡ እርካታ የሞላው በሚመስል ድምቀት የተወደድከው ወንድሜ ገና አይኖቹህ እነዚህ ዱካዎች ላይ እንዳረፉ በዚህ መንገድ ነብር ማለፉን የተናገርከው በፍፁም እርግጠኝነት ነበር እስካሁን ድረስ ባሳለፍከው እድሜ አፍንጫህ ስር

ክፍል ሁለት ይቀጥላል••••••••
449 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:34:16 ኢማነኛው ገበሬ
ልብ የሚነካ አሳዛኝ ታሪክ
ዛሬ ማታ 1 ሰአት ላይ ይጠብቁን
533 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 09:33:41
ኢማነኛው ገበሬ
ልብ የሚነካ አስተማሪ ታሪክ
ዛሬ ማታ 1 ሰአት ላይ ይጠብቁን
557 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, edited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:35:14 ጭንቀት
ሁሉ
አላህን
በማውሳት
ይለቃል
544 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:01:04 አላህ የወሰነለትን የወደደ ሰው
ከሰዎች ሁሉ ሀብታም ነው
653 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:18:28
870 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:18:28
810 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:18:27
736 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 22:18:15
720 viewsኢዘዲን ሰይድ Ezedin seyid, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ