Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS SCHOOL️

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_in_school — ISLAM IS SCHOOL️ I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_in_school — ISLAM IS SCHOOL️
የሰርጥ አድራሻ: @islam_in_school
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.33K
የሰርጥ መግለጫ

ኢስላም በትምህርት ቤት
ለአስተያየት @ezk24

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:41:32 ‍ እንዳልነበር ከእማ በኋላ ዳግመኛ አላገባም፡፡ እኛን ለማሳደግ በሚችለው አቅም ልክ ጣረ፤ ምናልባትም ከሚችለውም ከሚቻለውም በላይ፡፡ የተሰራ ምግብ ለራሱ አቅርቦ ለመብላት የማይፈልገው አባዬ እኛ እንድናጠና በየቀኑ ከስቶቭ እና ከክሰል ጋር ሲታገል፣ ያደፈን ጨርቅ ለማንጻት ሲዳክር ኖረ፡፡ ይሰራበት የነበረውን ቤት አከራይቶ ገቢውን አብቃቅቶ ለመጠቀም ሞከረ፤ እንደምንም ተሳካለት፡፡ ችግሮችን ሁሉ ድል ለመምታት በጣረ ቁጥር ከአንደበቱ ላይ አንድ ቃል አይጠፋም ነበር፤ "አልሀምዱሊላህ!" አሁን አባዬ አለም ላይ እውነተኛ ደስታ ካገኙ ጥቂት ሰዎች መሀከል አንዱ ነው፡፡

ከአዲሱ ክፍሌ ውስጥ ከድሮው የመጽሐፍ መደርደሪያዬ ላይ ጥቁሩን ማስታወሻዬን አነሳሁ፡፡ አለፍ አለፍ እያልኩ የጻፍኳቸውን ማንበብ ያዝኩ፡፡ ሮዟ ማስታወሻዬ ጠፍታ እንደረሳሁት ሁሉ ጥቁሩን ማስታወሻዬንም እንደምረሳው መንገሬን አነበብኩ፤ ግን አልረሳሁትም፡፡ ጥቂት ተጨማሪ ገጾችን ሳገላብጥ ግን አንተ እያልኩ አወራው የነበረውን ማስታወሻዬን "ጥቁር ማስታወሻዬ" ብዬ እየጠራሁ ውሎዬን እንደማጠራቅምበት ተራ ወረቀት መቁጠሬ ገባኝ፡፡ ይቅርታ ጥቁሩ ማስታወሻዬ ካ'ሁን ጀምረን ወደድሮው ጓደኝነታችን እንመለሳለን፤ ይቅርታ ካደረግክልኝ፡፡

አንተን ማገላበጤን እንደቀጠልኩ ካ'ንደኛው ገፅህ ላይ ደርሼ ያገኘሁትን ጽሁፍ በቃሌ እስክይዘው ደግሜ ደጋግሜ አነበብኩት፤ ቆይ ልንገርህ፡
ᐸ"እማ! በአንደኛ ሴሚስተር አንደኛ የወጣውን ልጅ፤ አዩብን ታውቂዋለሽ አይደል?"
"መስጂድ ውስጥ ጫማ የሚጠርገውን ነው?"
"አዎ!"
"እኮ የዘይነብ ልጅ፤ ቅያሱ ጋር የተከራዩት?"
"እህ... እማ! አዎ እያልኩሽ፡፡"
"ምን ያስመርርሻል? ሆ! ጨምላቃ! አሁን ምን ልትነግሪኝ ነው?"
"ትናንት ከቀረ ሶስት ቀን ሆነው፤ ትምህርት ቤት መጥቶ አያውቅም፡፡"
"እና አንቺ ምን ቤት ነሽ?"
"አይ... ጓደኛውን ስጠይቀው የቤት ኪራይ ስለበዛባቸው እንዳይባረሩ ለመክፈል እየሰራ እንደሆነ ነገረኝ፡፡"
"እስኪ አባትሽን አማክረዋለሁ፤ መቼስ ዝም አይል?"
"አመሰግናለሁ እማ!" ቀና ብዬ ሳምኳት፡፡
"ዝምበይ! ሠባኪ... ዘንድሮ ግን እንዳይበልጥሽ፡፡ ተጋድመሽ መዋል አብዝተሻል፡፡ አታዪም እንዴ እንዴት እንደወፈርሽ?"
"የአራት ሠው ምግብ እያስያዝሺኝ ነዋ! ተይ ብልሽ እምቢ አልሽኝ፡፡"
"ቀኑን ሙሉ እየዋልሽ እንዳይርብሽ ብዬ ነዋ! ቁርስሽንም ስትቻኮይ ሳትበዪ ነው የምትወጪው፡፡"
"ለነገሩ ዛሬ የምበላውን በነገታው ምሣዕቃዬን እየተሸከምኩ አቃጥለው የለ?"
"ኧረግ ኧረግ ነገረኛ ሁነሽ የለ እንዴ?"
"ግን ያንቺም ሆድ ጨምሯልኮ፡፡ የሚገፋ ይሁን የሚጠፋ ግን አልገባኝም፡፡"
አሁንም ሣቀች፤ "ድርሠት አልተውሽም ማለት ነው?"
"ኧረ ለምን ብዬ"
"እና ለኔ የሚሆን ግጥም ነገር አልጻፍሽም?" አለችኝ ጸጉሬን እያሻሸች፡፡
"ቆይ በኋላ አነብልሻለሁ፡፡">
:
ያኔ ትዝ ይልኃል አይደል፤ በእማ ሞት ደንግጬ የጻፍኩላትን ግጥም ሆስፒታሉ ውስጥ ስጥለው፡፡ ምናልባትኮ ያ ግጥም አሁንም ድረስ ከቆሻሻ ውስጥ ሆኖ አሊያም ከቆሻሻዎች መሀከል ተቃጥሎ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን የጻፍኩትን አዲስ ግጥም ግን ላንብብልህ፤ ከመሳቢያው ውስጥ ነበር ያስቀመጥኩት፡
:
ᐸእዚህ ኑሮ ይኖራል፣ በገሚሱ ይገፋል፣
ገሚሱን ይገፋል
ገሚሱ ይገፋፋል፣ ገሚሱ ተገፍፎ
ሌላውን ይገፍፋል
ከሙታንስ መንደር፣ ከትቢያው ግርጌ ላይ ህይወት እንዴት ቀጥሏል?
እዚህ ሠው ይገድላል፤ የሟች ደም እንዲደርቅ ሌላ ደም ይፈሳል
ከናንተ መንደርስ ሠው ይተራረዳል፤ መጋደል አይሏል?
ከኛ ከህያዋን ከቆሞ ሂያጆቹ ከኗሪዎች መንደር
የተነሳች ንፋስ ትቢያ አለበሰችኝ ልቤን ልታሸብር
በዓይኔ ውስጥ ገባች ልቤን ልታሳውር
በጆሮዬ ገባች ልቤን ለማደንቆር
የንፋሷ አብራክ ጽንሷ ትቢያ ጎድታኝ
እኔ ልጅሽ አለሁ ትንሿን ትቢያ ሠርክ እየረገምኩኝ
ከዚያ ትቢያ ግርጌስ እማ ካንቺ መንደር
ቋጥኝ ያህሉ ትቢያ ምን ያህል ይጥራል ልብሽን ለማወር
ርግማን ከጅሎ በጆሮሽ እየገባ ልብ ሊያደነቁር
ወይስ ከናንተ ዘንድ ከሙታኖች መንደር
ርግማን ይሉት ወግ መታወር መደንቆር
ስሜትየለሽ ናቸው በዓለመቀብር
★★★
እዚህ እኛ ዓለም ላይ ካለው ትልቅ ሠማይ
ከባድ ዶፍ ይወርዳል ስቃይን የሚያሳይ
በእትትት ዜማ ዳንኪራ የሚያስመታ
እኔ ነኝ ያለውን በአቆርፋጅ ብርዱ ባንዴ የሚረታ
ይኼ ከባድ ዶፍ የሠማዩ አብራክ መሬት ውስጥ ይሰርጋል
ከሙታኖች መንደር ከትቢያውስ ግርጌ ይኼ ዶፍ ይዘልቃል?
እትትት እያስባለ እስክስታ ያስወርዳል?
ከጋቢ ከእሣት ጥግ ከቤት ያስመሽጋል?
ወይስ ከናንተ ዘንድ በሙታኖች ባህል
እትት ይሉት ዜማ መብረድ የሚሉት ቃል
ትርጉም አልባ ሆኖ ሲሰሙት ያስቃል?
★★★
እዚህ እኛ መንደር ከህያዋን መሀል
ፀሐይ ይሏት እሣት ሠውን ስታበስል
ከሠማይ ተነስታ በግዙፍ ጨረሯ መሬት ላይ ስትደርስ
ሁሌ እገረማለሁ...
አቅሟ ይችል ይሆን ያንን ትልቅ ቋጥኝ ንዶ ለመደርመስ?
እኔ ምን አውቃለሁ እስኪ አንቺ ንገሪኝ
የፀሐይዋ ንዳድ ምን እንደሚያደርግሽ በደንብ አብራሪልኝ
የፀሐይዋ አብራክ ያ ግዙፍ ጨረሯ ከናንተ ጋር ዘልቆ
ንፋስን ያሰኛል እብድስ ያስመስላል ልብስን አስወልቆ?
ወይስ በናንተ ዓለም ሙቀት ያልኩት እኔ
መፍታት የማይችሉት ሆኖብሻል ቅኔ
እስኪ ሁሉን ንገሪኝ ህይወት እዛ እንዴት ናት
እናንተ መንደር ውስጥ እማን የኔን ህይወት ማንነው የሚቀልባት
ወይስ መራብ መጥገብ ፈጽሞ አይነካካት?
★★★
እዚህ በ'ኛ መንደር እኔ ባለሁበት
ትዝታሽ ለምዶኛል ይመጣል በድንገት
ረዣዥሙ ጣትሽ ጸጉሬን ይፈትጋል
የአዘቦት ድካምሽ የኔን ሆድ ለመሙላት ዘላለም ይጥራል
የአንድ ቀን ቁጣሽ ሁሌም ያቅበኛል
የአንድ ቀን ምክርሽ ካሰብኩት ያደርሰኛል
ድምፅሽ፣ ሽታሽ መልክሽ ዛሬም ይታየኛል
ዛሬም ያውደኛል፣ ዛሬም ይሰማኛል
ካ'ንቺስ መንደር እማ ትዝታ ምን ይላል?
ያኔ እማ ያልኩሽ አሁንም ይሰማል?
መቆም ያቃተኝ ቀን አንቺን መደገፌ ሁሌም ይገርምሻል?
የያኔው ጥፋቴ ዛሬም ያስቆጣሻል?
ስኬት ደስታዬስ ያፍነከንክሻል?
ወይስ በናንተ ዓለም ትዝታ ይሉት ቃል የማስታወስ አብራክ
ትርጉምየለሽ ቃል ነው ልክ እንደ "ሶጵቺራክ"
ረስተሽኝ ይሆን ላታስታውሽ መቼም
ወይስ በናንተ ዓለም መርሳትም የሚሉት አንዳችም ቃል የለም?>

ጥቂት ቆይቶ ቤቱ ቀስበቀስ ይወካ፣ ይፈካ ጀመር፡፡ ሩቂ፣ ሰሎሜ፣ ሰባህ፣ ነዋል፣ አክስቶቼ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው... እኔ ወዳለሁበት ክፍል ይመጡ ጀመር፡፡ ጋሽ ሳላህ፣ ማሂር፣ ዛኪር፣ አጎቴ፣ የሩቂ ባል... ሳሎን ውስጥ ከአባዬና ማሜ ጋር ማውራት ያዙ፡፡" ቤቱ ይጮህ ጀመር፡፡"

የግቢው በር ተንኳኳ፤ ተነስቼ ከፈትኩ፤ ሰሙ ነበረች፡፡
.
.
.
ይቀጥላል

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
245 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:41:32 የሰሚራ ማስታወሻ
ክፍል ስምንት
Rayan Huda

...ልክ እንደአዲሱ ማስታወሻዬ ጠቆረ፡፡"

አሁንም ከአልጋዬ አልወረድኩም፤ ዛሬ መቼም ጉድ ነው፤ ምሣ ሰዓት ተቃርቧል፤ የዝሁር ሰዓትም እየደረሰ ነው፡፡ 'ማንበብ የማይወደው የሰሚራ ባል ካልጋው ላይ እንደተንጋለለ አንድ ጥቁር ማስታወሻ ሲያገላብጥ ዋለ፤ ያውም የሚያውቀውን ከዚህ ቀደም የሰማውን ታሪክ፤ ያውም ከገጽ ገጽ እየጓጓ፤ በሚስቱ የቃላት አደራደር እየተደመመ'፣ ይህ የአመቱ ምርጥ ቀልድ መሆን አለበት፡፡ እኔ እኮ ሰሙ በሚያባብሉ የዋህ ዓይኖቿ እንድትጽፍ የሚያነሳሳትን የጥሞና ጊዜ እንድሰጣት ስትማጸነኝ ሳላንገራገር እስማማለሁ፡፡ ከዚያ ግን የጻፈችው ምን እንደሆነ ሳልጠይቃት ጊዜያት ይነጉዳሉ፡፡ ዝምታዬ በጨመረ ቁጥር መንጨርጨሯ ይግልና አፌን ምን እንደለጎመው ትጠይቀኛለች፤ ዝም እላለሁ፡፡ ከጊዜ በኋላ ሰለቻት መሰለኝ ምን እንደጻፈች አለመጠየቄን ከመጤፍም አለመቁጠር ያዘች፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ከመደርደሪያዋ ላይ አንዱን መጽሐፍ መዥርጣ ልትተርክልኝ ትጀምራለች፣ እኔ ሆዬ በእንቅልፍ እጦት እንደምንገላታ ሁሉ ረስቼ ጭል...ጥ እላለሁ፤ ሰሙ ከእንቅልፌ ትቀሰቅሰኝና ድጋሚ ልትተርክልኝ ትሞክራለች፤ እኔ አሁንም ወደእንቅልፍ ዓለም ለመመለስ አኮበኩባለሁ፡፡ ዛሬ የሚታተመውን የመጀመሪያ መጽሐፏን እንኳ አልጨረስኩትም፡፡ ትናንት ማታ ለዛሬ የሚሆን ምሳ እያዘጋጀን የመጽሐፏን ታሪክ እንደዋዛ ጠየቀችኝ፡፡
"ያው አንድ ንጉስ ነበር፤ ሚስቱ ታመመችበት..."
"ይህንንማ ህጻን ልጅም ይፅፈዋል፡፡ በታሪኩ ውስጥ ያለውን ሀሳብና የሚያስተላልፈውን መልዕክት ነው እንድትነግረኝ የፈለግኩት" ቆጣ ትላለች፤ እኔ አይኖቼን በየዋህነት እያቁለጨለጭኩ ዝም እላለሁ፡፡ ዛሬ ወደመጽሀፍ ምረቃው የሄዱት በርከት ብለው ነው፡፡ ትናንት ማታ ለሁላችንም የሚሆን ምሳ ስንሰራ ነበር ያመሸነው፡፡ አሁን ከመምጣታቸው በፊት ሁሉን አዘጋጅቼ ብጠብቃቸው ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ቢሆንም ጥቂት ጊዜ አለኝ፡፡ ማስታወሻዉን ዘግቼ በርካታ ገፆችን ዘልዬ እጄ ወደመራኝ ገጽ ገለጥኩ፤ የማስታወሻው መሀከለኛ ገጾች ላይ ጉብ አልኩ፡፡

"በአዲሱ ቤታችን፣ አዲሱ ክፍሌ፣ አዲሱ ባለመስታወት መስኮት ላይ አፍጥጬ ደጁን እያማተርኩ ነው፡፡ ከሳምንት በኋላ ደግሞ ወደሌላኛው አዲሱ ቤቴ፤ አዲሱ ክፍሌ አቅንቼ በአዲሱ መስኮት ድሮንም፣ አሁንንም፣ ወደፊትንም እመለከት ይሆናል፡፡ የወደፊቱን ማን ያውቃል? ደጅ ላይ ማቲዎች እግር ኳስ ይጫወታሉ፡፡ ከማሜ ጋር በእድሜ የሚስተካከሉ በለቀያይ ጢማም ታዳጊዎችም ከህጻናቱ ጋር ይጫወታሉ፤ ማሜ ግን አብሯቸው የለም፤ እያጠና ነው፡፡ ለቀጣይ አመት የማትሪክ ፈተና ዘንድሮ የ11ኛ ክፍል ትምህርትን እያጠና ነው፡፡ እንደኔ ከስድስት መቶ በላይ ለማምጣት ይሻል፡፡ በተለይ አስረኛ ክፍል ላይ "ስትሬይት ኤ" አምጥቶ ካለፈ በኋላ ሞራሉ ተነሳስቷል፡፡ ማቲዎቹ ከሚጫወቱበት አቧራማ ሜዳ ትይዩ ጸሐይ በደመናዎች ተሸብባ ትታያለች፡፡ ጸሀይዋ ራሷ የበረዳት ነው የምትመስለው፡፡ የወትሮው አቃጣይነቷ ዛሬ የለም፡፡ ማቲዎቹ የሚጫዎቱበትን ሜዳ ንፋሱ ትቢያውን እያነሳ ከማቲዎቹ ላይ ያራግፍለታል፡፡ ጋቢዬን እንደተከናነብኩ አዲሱን ሰፈር ማስተዋሌን ቀጠልኩ፡፡ ዓሊ፣ ከንቱዎች ያከነተቷት ድንጋይ፣ ቅያሷ ጋር የተከራዩት እነዘይነብ፣ ታመው የሚጠየቁ ዒማም፣ በሠንጢ የወጋ ዱርዬና በሠንጢ የተወጋን ልጅ በመኪናው ሆስፒታል የሚያደርስ ሽማግሌ... የሌሉባት ሰፈር፡፡ ከጸሀይዋና እንደጋቢ ከጠቀለላት ሸበቷም ደመና ገለል ብሎ ያደፈ የጥጥ ባዘቶ የመሰለ ዝናብ አዘል ደመና ይታያል፡፡ ንፋሱ አሁንም አሁንም ትቢያውን እያነሳ ከህፃናቱ ፊትና ልብስ ላይ ይከምረዋል፡፡ በጸሀይዋ ወበቅም ትቢያ ባዘለው ንፋስም ሊበገሩ ባለመቻላቸው ስደነቅ ጥቁሩ ደመና ድንገት እዬዬውን ይለቀው ጀመር፤ ምናልባትም በህጻናቱ ስቃይ አዝኖ እያነባ ይሆን እንዴ? ማዘኑ ግን ይበልጥ ጎዳቸው እንጅ አንዳንች ነገር አልፈየደላቸውም፡፡

ስልኬ ድንገት ጠራ፤ ሰሎሜ ናት፤ ሲስተር ሰሎሜ፡፡
"ሄሎ ዶክተር!"
"ሰሎሜ! እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ፡፡ ዛሬ ሆስፒታል ውስጥ ሳጣሽ ነው'ኮ"
"አዎ ፍቃድ ወሰድኩ፡፡"
"ለሰርገሽ እንዳይሆን?" ድምጿ መደነቋን ያስተጋባል፡፡
"አዎ ለሰርጉ ነው፤ ረፍት ወስጄም አላውቅም፡፡ በዚያ ላይ የምከታተላቸው ፔሸንቶች የሉኝም፡፡ ባለፈው ፓራላይዝድ ሆነው የመጡት ፔሸንት በፊዚዮቴራፒ እያገገሙ ነው፡፡ የኤፒለፕሲ ታማሚ ወጣቱም ቢሆን መድኃኒቱን እየወሰደ ነው፡፡ ከሁለቱም ጋር በስልክ ኮንታክት እያደረግን ነው በዚያ ላይ አዳዲስ ፔሸንቶች መጥተው እኔ ካስፈለግኩ እንዲደወለልኝ ተነጋግሪያለሁ፡፡"
"አለቃሽ መሰልኩሽ እንዴ? ሪፖርት ነው'ኮ የሚመስለው፡፡"
"ማወቅ ከፈለግሽ ብዬ ነው፤ ደግሞም ጠይቀሽኛል፡፡"
"እኔ ስለሰርጉ ነው ማወቅ የምፈልገው፡፡"
"ለምን ዛሬ አትመጪም?"
"በቃ ከሆስፒታል እንደወጣሁ እመጣለሁ፡፡"
"ጥሩ"፤ ስልኩን ዘጋችው፡፡

አሁንም ከመስኮቱ ፊትለፊት የቆመችው እናቷ በሞተች ቀን ራሷን ስትስት የዓሊ ድምፅ "ህይወትሽ ሶጵቺራክ ሆናለች፡፡" እያለ ያቃጨለባት ሴት አይደለችም፡፡ የሱረት አል ኢሻራህን የመጨረሻ አንቀጾች ሰምታ ተስፋ የሰነቀችው እንጅ፡፡ ከዓመታት በፊት የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማትሪክን ጥሩ ውጤት አምጥታ አለፈች፣ ብዙዎች የማይደፍሩትን የህክምና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ገብታ አጠናች፣ እንደአባቷ ላሉ ህሙማን የመዳኛ ሰበብ ትሆን ዘንድ በኒውሮልጂ ስፔሻላይዝ አደረገች፣ በራሷ ጥረት ቁርዓንን ሐፈዘች... ይህችው ከመስታወቱ መስኮት ፊት የቆመች ሴት፡፡ አሁን ደግሞ ልታገባ ነው፤ አዩብን ልታገባ፡፡"

ስልኬ ጠራ፤ ንባቤን ገታ አድርጌ ተመለከትኩ ሰሙ ናት፤ መምጫቸው ደረሰ ማለት ነው፤ ስልኩን አነሳሁት፡፡
"አሰላሙዓለይኩም አዩቤ!"
"ወዓለይኩም አስሠላም ሰሙ! ዝግጅቱ እንዴት ነበር? ብዙ ነገር አለፈኝ?"
"አሪፍ ነበር፡፡ ሲያንዛዙት እየተመለስኩ ነው?"
"እንዴ? የገዛ መጽሐፍሽን ምርቃት ትተሽ?"
"ታውቃለህ፤ አዘጋጆቹን እንዲያሳጥሩት ነግሪያቸው ነበር፤ እምቢ አሉ፤ ትቻቸው መጣሁ፡፡"
"እነማሜስ?"
"ብቻዬን ነኝ፤ ልሎቹ እዚያው ናቸው፡፡"
"ዝግጅቱን ግን ማቋረጥ አልነበረብሽም፡፡"
"ለምን ሲባል? አንብበህ አልጨረስክም እንዴ?"
"ምኑን?" ግራ ገባኝ፡፡
"ጥቁሩን ማስታወሻዬን ነዋ!"፤ ሣቀች፡፡
"በምን አወቅሽ?"
"የባሌ ጸባይ እንዴት ይጠፋኛል?"
"አዎ አልጨረስኩም" የእፍረት ሳቅ ሳቅኩ፡፡
"በቃ መጣሁ፤ እንቅልፍ የማይወስድህ ከሆነ እኔ አነብልሀለሁ፡፡" ሣቀች፤ ሣቅኩ፡፡
"እሺ!" ስልኩን ዘግቼ፤ ወደንባቤ ተመለስኩ፡፡

"አዎ ይህኛው አዩብ፤ የዚያኛውን አዩብ ስሙን ብቻ ይያዝ ወይስ ግብሩን ጭምር በመጠኑ ብቻ ነው የማውቀው፡፡ የአባዬንም የራሴንም ብዙ ህልሞች ማሳካት ችያለሁ፡፡ የቀረኝ ነገር ቢኖር የራሴን ህይወት መጀመር ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የእናቱን ህልም ለማሳካት የቋመጠን ወጣት ለማግባት ወስኛለሁ፤ ከአባዬ ጋር ተማክረን፡፡ ይህኛው አዩብ መስጂድ ውስጥ ጫማ የሚጠርገው፣ የዘይነብ ልጅ ቅያሷ ጋር የተከራዩት አይደለም፡፡ ያ አዩብ ላይመለስ አሸልቧል፤ ይህኛው ልላ ነው፡፡

እማ ከሞተች በኋላ አባዬ በምንም ነገር ላይ ተስፋ እንዳልቆርጥ ይመክረኝ ነበር፡፡ መንገር ብቻ አይደለም፤ በተግባር አድርጎ አሳየኝ፡፡ እማን እኔ ከሞትኩ እንድታገባ ምከሪያት ሲለኝ
229 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:27:35 ሁለት ጓደኛሞች በጫካ ዉስጥ ሲጓዙ ድብ ያገኛሉ። አንደኛው በፍጥነት ዛፍ ላይ ለመውጣት ሲችል ሌላኛው ግን እንደዚያ ለማድረግ ባለመቻሉ መሬት ላይ የሞተ በመምሰል ይተኛል።

ድቡ ጆሮዉ ስር ያሸተዉና ትቶት ይሄዳል በዚህ ጊዜ ዛፍ ላይ የወጣው ሰው ወደመሬት ይወርድና <<ድቡ ምን አለህ?>> ብሎ ሲጠይቀው እሱም <<በአደጋ ጊዜ ትቶህ የሚሄድ ጓደኛ እንዳታምን ብሎ ነገረኝ!>> ይለዋል።

"በመከራ ጊዜም ቢሆን ታማኝ ጓደኛ በመሆን መልካም ስብእናችንን እንገንባ!"

☞አንድ ቀን ይመጣል አንተ ራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያወልቁልህ ቀን

☞የተከፈተ አፍ እና አይንህን ሰዎች የሚዘጉልህ ቀን

☞ተራምደህ ከሄድክበት ቦታ ሰዎች: ተሸክመው የሚያስወጡህ ቀን

☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን

☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ ወልቆ ሌላ ሰው የሚወርስበት ቀን ይህ ቀን ሳይመጣ በፊት በመልካም ስራ ልይ እንትጋ

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
596 viewsғʟᴏʀᴇɴᴄᴇ, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:04:11 ንዴት የትኛውንም ችግር አይፈታም፤ ምንም ነገር አይገነባም፤ ነገር ግን የተገነባውን በሙሉ ያፈርሳል!

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
385 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:04:11 የፈለግነውን ነገር በሙሉ ማግኘት ጥሩ አይደለም፤ ህመም ጤንነትን ጣፋጭ ያደርገዋል፤ ረሃብ በመጥገብ ለማመስገን ይረዳል፤ ድካም በማረፍ መዝናናትን ይፈጥራል!

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
386 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:04:11 :አንዱ ቀደምት እንዳለው ~

:በየቀኑ ሁለት ሰዎችን ብቻ ብናማቸው እና ለአቅመ አዳም ከደረስን በኋላ በዱንያ ላይ 60 አመት ብንቆይ
በእለተ ትንሳኤ የሚከራከሩን ሰዎች ብዛት ስንት እንደሚደርስ ታውቃለህ

32,000 ሰዎች የተበድለናል ክስ ያቀርቡብናል።

አያስደነግጥም

[አላህ ሰውን ከማማት ይጠብቀን አሚን!]

•━━━ ✽ • ✽ ━━━•

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
348 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:04:07 አላህ(ሱ፡ወ)እንዲህ ይላል፦የሰዉ ልጅ ሆይ መከራ ባጋጠመህ ጊዜ ወዲያውኑ ከታገስክና(ከእኔ)ምንዳ ከፈለግክ(ላንተ)ኀላ ምንዳ አልመርጥልክም-ጀነት ሲቀር።
<ኢብን ማጆህ ዘግበውታል>

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
374 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 07:04:07 ዱንያን ችላ በል ወይም ፍቅሯን ከልብህ አስወጣ አሏህ ይወድሃል ፣ ሰዎች ዘንድ ያለውን ( ዱንያቸውን ) ችላ በል ሰዎች ይወዱሀል
ውዱ ነቢያችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም

SHARE SHARE
╔════════════╗
JOIN: @islam_in_school
JOIN: @islam_in_school     ╚════════════╝
353 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:12:50 በር ላይ ስንደርስ ጋሽ ሳላህ በሩን አንኳኩ፡፡ የሚከፍት ጠፋ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጸጉራቸው እንደወተት የነጣ ሽማግሌ በበሩ ሲርሲርታ ታጅበው እያቃሰቱ ከፈቱ፡፡
"አቤት?" አሉ አንገታቸውን አስግገው፡፡
"ደህና ዋሉ አባት? አዩብን ፈልገን ነበር?" አሏቸው ጋሽ ሳላህ፡፡
"አይ ልጄ! ተሳስታችኋል! እዚህ ያለችው ባልተቤቴ ናት፡፡ እንደው ምን እንደነካት አላውቅም ትናንት ማታ ጀምሮ..."
"ፈጣሪ ያሽርልዎት፡፡" ጋሽ ሳላህ ራቅ ብለው የክፍሉን ቁጥር ተመለከቱት፤ እኔም አየሁት፡፡ ትክክል ነው፤ ቁጥር 201፡፡ ደረጃዎቹን ቁልቁል ወርደን ወደእንግዳ ተቀባይዋ ሄድን፡፡
"ይቅርታ እናት! አዩብ የተባለ ታካሚ የተኛበትን ክፍል ትፈልጊልን?" አለ ማሂር፡፡
"እሺ! አዩብ አይደል ያልከኝ፤ መቼ ነው የገባው?" ወፍራሙን መዝገብ ማገላበጥ ያዘች፡፡
"ሳምንት ሆነው፤ ቅዳሜ ምሽት፡፡"
"እሺ!" አቀርቅራ ጥቂት ከቆየች በኋላ "ይቅርታ አዩብ የሚባል ታካሚ እኛ ጋር የለም፡፡"
"ምን? ምንድን ነው የምትይው? በደንብ ፈልጊ ባክሽ!" ጋሽ ሳላህ ተቆጡ፡፡
ድጋሚ አቀርቅራ ከቆየች በኋላ "እውነቴን ነው፤ ካለመናችሁ እናንተ እዩት!" ብላ ወፍራሙን መዝገብ ገፋችልን፡፡ እውነቷን ነው ከመዝገቡ ላይ የአዩብ ስም የለም፡፡
"በስለት ተወግቶ ከገባ ሳምንት ሆነው እኮ፤ 18 ዓመቱ ቢሆን ነው፡፡" አሉ ጋሽ ሳላህ፡፡
የልጅቱ ፊት ጨገገ፤ "በጣም አዝናለሁ፤ ሣምንት የገባ የ17 ዓመት ታዳጊ ዛሬ ጧት አርፏል፡፡" የማደርገው ጠፋኝ፤ ተደናገጥኩ፡፡ ጧት ጀምሮ ሲከተለኝ የነበረው፤ ስም ያጣሁለት ስሜት ተስፋ መቁረጥ እንደነበር ገባኝ፡፡ ስልኬ ጠራ፤ አባዬ ነው፤ አነሳሁት፤ ድምፁ ይቆራረጣል፡፡
"ሄሎ ሰሙ አሠ... ላሙዓለይኩም"
"ወዓለይኩም አስሠላም አባዬ ምነው ድምፅህ ይቆራረጣል?"
"የት ነው ያለሽው ልጄ?"
"አዩብ የተኛበት ሆስፒታል ነኝ፡፡ የማሂር አባት፣ ማሂር እኔ'ና ማሜ ሆነን ልንጠይቀው ሂደን ነው፡፡ አንተ ምን ሆነህ ነው?"
"ሠምሙ! ሱ... ምመያን እናትሽን አጣናት!"
ሞባይሉም ግጥሙም ከእጄ አመለጡኝ፡፡ የጸነስኩት ተስፋ እንግዴ ልጁ ተቆርጦ ሲጨናገፍ ታወቀኝ፡፡ ነገሮች ሁሉ ደበዘዙ፤ ተርገፈገፉ፤ በመጨረሻም ጠፉ፤ ጨለማ ሆነ፡፡

"ልጅ...ት ህይወትሽ ሶጵቺራክ ሆናለች፡፡" ዓሊ ይጮኻል፤ ቀይ ድዱን ገልጦ እየሳቀ፡፡

ነቃሁ፤ ጩኸት ይሰማኛል፡፡ "ጓደኛዬ ጓደኛዬ፤ መካሪዬ መካሪዬ፤ ሱመያ፣ ሱመያ..." ሰው ሁሉ ያለቅሳል፤ ከአልቃሾች መሀል ብዙ ጫኺዎች አሉ፤ ከጯኺዎቹ ውስጥ ግን አንድም አንቢ የለም፡፡ የዓሊ ግጥም ትዝ አለኝ
ᐸበጥረትህ ጊዜ የሚያውቅህ አያውቅህም
ልክ የስኬትህ ቀን የማያውቅህ አይኖርም
ከተንሸራተትክ ግን ማንም አይሰማህም">፤
ውሸት ነው፤ ዓሊም ጤነኛ መሆን ሳይጀምር አይቀርም፡፡ ይኼው የእማን መሞት ሲሰማ አይደል ይኼ ሁሉ ህዝብ ከንፈሩን እየመጠጠ በቁስላችን እንጨት ሊሰድ የመጣው፤ የእነሱ መመጻመጽ ለእኛ ምን ይረባናል?
"ውጡልኝ፤ ከቤቴ ውጡ!" አምባረቅኩባቸው፡፡
ሩቂና አባዬ እየጎተቱ መኝታ ክፍሌ ውስጥ አስገቡኝ፡፡ የአባዬ አይኖች ደፍርሰዋል፤ እምባ የወረደባቸው ጉንጮቹም መስመር አበጅተዋል፡፡
"ዒሻ አዛን ብሏል፤ መግሪብንም አልሰገድሽም፤ እኔና ማሜ መስጂድ ልንሄድ ነው፡፡" ቆጣ ያለ ይመስላል፤ ከሩቂ ጋር ውዱዕ ልናደርግ ከክፍሌ ወጣን፡፡ ውዱዕ እየደረግኩ ከመስጂድ የአባዬ ድምፅ ይሰመኛል፤ ኢማሙ ስለታመሙ ነው እሱ የሚያሰግደው፡፡ ከአል-ፋቲሐ (ከመክፈቻው ምዕራፍ) ቀጥሎ ሱራ አል-ኢሻራሕ (የልብ መስፋት ምዕራፍ)ን አስከተለ፡፡ የመጨረሻዎቹ አያዎች (አናቅፅ) ላይ ሲደርስ ሲቃ ተናነቀው፡፡
فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡
إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
فَإِذَا فَرَغْتَ فَانصَبْ
በጨረስክም ጊዜ ልፋ፡፡ (ቀጥል)፡፡
وَإِلَىٰ رَبِّكَ فَارْغَب
ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል፡፡
:
መግሪብና ዒሻን አከታትዬ እንደሰገድኩ አባዬ የክፍሌን በር ከፍቶ ገባ፡፡ ሩቂ ወጣች፡፡ አባዬ ከተኛሁበት አልጋ ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡
"ሰሙ..." ግንባሬን በቀኝ እጁ መዳፍ ደባበሰኝ፡፡ "ሱመያ የታመመች ሰሞን ምን ብለሽኝ እንደነበር ታስታውሻለሽ? አንተ ጤነኛ ሁነህ ለኖርክባቸው፤ ከእማ ጋር በፍቅር ለኖርንባቸው፣ በምቾትና በተድላ ለኖርንባቸው እያንዳንዱ እለት አላህን አመስግኜ አውቃለሁ? በፍጹም! እና እነዚህን ሁሉ ሳጣ በየእለቱ ለምን አማርራለሁ? አስታወሽ?"
ጭንቅላቴን በአዎንታ ነቀነቅኩለት፡፡
"አየሽ ሱመያ ተስፋ ቆራጭ የሆነች ደካማ ልጅ አላሳደገችም" በጉንጮቹ ላይ የሚንኳለሉ የእምባ ዘለላዎችን በመዳፉ ሞዠቃቸው፡፡ "እሷ ጠንካራ እንድትሆኚ ነው የለፋችው፤ ልፋቷን ከንቱ አታድርጊው፤ ደካማ እንድትሆኚ እንዳደረገችም አታስቆጥሪያት፡፡ አየሽ ከብረት የጠነከረ ልብ ያስፈልገናል፡፡ በፍርሃት ውስጥ ጥንካሬ የለም፡፡ ተስፋ ቢስነት ደግሞ የፈሪዎች ባህሪ ነው፡፡ ጀግና ችግርን ሁሉ ይጋፈጣል፡፡ የሚጋፈጠውም በትዕግስት ነው፡፡"
"አባዬ የምትለው'ኮ እውነት ነው፤ እስኪ ግን በደንብ ተመልከተው አያቴ ሞተች፤ አንተ ታመምክ፤ አዩብ በእኔ ምክንያት ተወግቶ ተገደለ፤ እማ ሞተች... ይኽ ሁሉ ለመሆን አምስት ወር ብቻ ነው የፈጀበት፡፡"
"እስካሁን የጠቀስሽው በሙሉ የገጠሙንን ችግር ነው፡፡ ያላመሰገንኩትን ፈጣሪ ለምን አማርረዋለሁ አላልሽም? ነገር ግን ስለእኔ መዳን አላወራሽም፤ ስለማሜ የባህሪ ለውጥ አላወራሽም፤ አላመሰገንሽም? ለምን!? አንድ አባት ለልጆቹ አንድ ፈተና ያዘጋጅላቸዋል፤ ከሁለቱ ልጆቹ ይበልጥ ጠንካራውን ለማወቅ ሩቅ ከነበረው ወንዝ ውኃ እየጨለፉ ካዘጋጀላቸው ጉድጓድ ውስጥ እንዲጨምሩ ያዛቸዋል፤ የመጀመሪያው ልጅ ትልቅ ስለነበር አምስት ሜትር ጉድጓድ ሁለተኛው ደግሞ በእድሜ ስለሚያንስ ሶስት ሜትር ጉድጓድ ያዘጋጅላቸዋል፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ ከደከሙ በኋላ ትልቁ አራት ሜትሩን እንደሞላ ደከመ፡፡ ትንሹ ግን የተሰጠውን ጉድጓድ ከሞላ በኋላም ተጨማሪ ኃይል ነበረው፤ ግን ጉድጓድ የለውም፡፡ አየሽ ሰሙ ትልቁ ልጅ ምን ትልቅ ጉድጓድ ቢሰጠው ሊጠቀምበት አልቻለም፤ ትንሹ ልጅ ደግሞ የተሰጠችው ጉድጓድ አልበቃችውም፡፡ እኛ ትዕግስት በማድረግ ጥንካሬያችንን የምናሳይባቸው፤ በትዕግስት ምንዳ የምናገኝባቸው አያሌ ችግሮች ተሰጥተውናል፤ ጸጋዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሌሎች በተድላ እየኖሩ በትዕግስት ጥንካሬያቸውን ማሳየት፤ ምንዳ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ካልተጠቀምንበት ግን ጸጋነቱ ቀርቶ ችግር ብቻ ይሆናል፡፡ ልጄ እውነትም ጎበዝ ተማሪ፤ እውነትም ጠንካራ ልጅ ከሆነች እስካሁን ነገሮች ሁሉ ተመቻችተውላት ባገኘችው ሳይሆን አሁን በምታሳዬኝ ነገር ነው የምትለካው" ከተቀመጠበት ተነስቶ ግንባሬን ሳመኝና ሞባይሌን አነሳ፤ ምን ሊያደርግ እንደሆነ አልገባኝም፡፡
"ለፈጅር ቀድመሽ እንደምትነሽ እያወቅሽ ሁልጊዜ አላርም እንደምትሞዪ አውቃለሁ፡፡ አየሽ ስለወደድን ብቻ ሳይሆን አለማድረግ ስለማንችልም ጭምር ነው ተስፋ የምናደርገው፡፡ ጧት በህይወት መንቃታችንን እንኳ ሳናውቅ አላርም እንሞላለን፤ ደህና እደሪ" ግንባሬን ድጋሚ ስሞኝ፤ የክፍሉን መብራት አጠፋው፤ ጨለማ ሆነ፤ ልክ እንደአዲሱ ማስታወሻዬ ጠቆረ፡፡"
#ይ......
#ቀ......
#ጥ........
#ላ......
#ል.........
448 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:12:49 የሰሚራ ማስታወሻ
ክፍል ሰባት
Rayan Huda

""ሰሙ!" ሀቢባ ከዓሊ ዓለም ወደእውነታው ዓለም መለሰችኝ፡፡ ቁርስ እንደነገሩ ቀማምሼ ለእነአባዬም ይዤላቸው ወደሆስፒታል ሄድኩ፡፡ ሆስፒታሉ ጋር እንደደረስኩ ዶክተሩ አባዬን ድጋሚ ሊያናግረው ጠራው፡፡ አባዬ እንድከተለው ምልክት ሰጠኝ፡፡ ዶክተሩ ዛሬም እንድንቀመጥ ጋብዞን
"እእእ ሱመያ ነፍሰጡር ናት እንዴ?" መነጽሩን እየወለወለ አባዬን ጠየቀው፡፡
"አዎ!" አባዬ አንገቱን ደፍቶ በዓይኖቹ አናት ሽቅብ ተመለከተው፡፡ እኔ የእማ ሆድ መጨመር የሚገፋ ሳይሆን የሚጠፋ አይነት መሆኑ ገባኝ፡፡
"ሰሞኑን አንዳንድ ጥናቶች ወጥተው ነበር፡፡..." ዶክተሩ መነጽሩን ወደቦታው መልሶ ዓይኖቹ ላይ ከደረበው በኋላ ንግግሩን ቀጠለ፡፡ "እእእ ለወ/ሮ ሱመያ ያዘዝኩላቸው ኢንጀክሽን በነፍሰጡሮች ላይ ከበድ ያለ ችግር ይፈጥራል፡፡ አሜሪካ ውስጥ ኢንጀክሽኑን ሙሉበሙሉ የጨረሱ ነፍሰጡሮች በመላ ህይወታቸው አልፏል፤ ጥቂት ብቻ ከወሰዱለትም ሃምሳ ከመቶዎቹ ብቻ ናቸው የተረፉት፡፡ መድኃኒቱ አዲስ ከመሆኑም አንጻር ከላብራቶሪ ሙከራዎች በተጨማሪ እንደዚህ በገሀድ ችግሮች ሊታዩበት ይችላሉ፡፡ አሁን አምራቾቹ ጉዳቱን ለማሳወቅ እየጣሩ፤ በአዳዲስ ምርቶቻቸውም ላይ ለነፍሰጡሮች እንዳይሰጡ ጥብቅ ማሳሰቢያዎችን እየጻፉ ነው፡፡ ወ/ሮ ሱመያ የመጀመሪያውን ኢንጀክሽን ብቻ ስለሆነ የወሰዱት ብዙ የመትረፍ እድል አላቸው፡፡" ተናግሮ ሲጨረስ በረዥሙ ተነፈሰ፡፡
"ሌላ አማራጭ የለም?" ጠየቅኩት፤ አባዬ እንደበርበሬ በቀሉ ዓይኖቹ አፈጠጠብኝ፡፡
"በጣም አዝናለሁ፤ ፅንሱ ስድስት ወር አልፎታል፡፡ እሱን ማድረግ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡"
የአባዬ እጆች ሲንቀጠቀጡ ይታየኛል፤ የጸነስኩት ተስፋ እንግዴ ልጁ እንዳይቆረጥ ሲፈራገጥ ተሰማኝ፡፡"

ገለጥኩ፤ አዲስ ገጽ፣ አዲስ መስመር፣ አዲስ ቀን... እሁድ!

"እሁድ ነው፤ የፈጅር ሰዓት፤ ከሌሊቱ 11 ሠዓት፡፡ ውዱዕ ለማድረግ ወደግቢ ወጥቻለሁ፡፡ የሆነ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ ልቤ የሰውነቴን ክብደት አጠራቅማ ለብቻዋ የያዘችው ያህል ተሰማኝ፤ የሆነ ስም ያልወጣለት፤ ስምየለሽ ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡ ዓሊ ያለወትሮው በጊዜ ተነስቷል፡፡ ምንም ኮሽታ በማይሰማበት ቀዝቃዛ ጥቁር ምሽት ውስጥ የ'ሱ ድምፅ ብቻ ያስተጋባል፡፡ ዓሊን የመጣለትን እንደሚለፈልፍ አንድ ተራ እብድ ቆጥረው ወደውስጥ ብቻ እንዲያደምጡ ጆሮዎቼን አዘዝኳቸው፤ ጆሮዎቼ ትዕዛዝ ማክበር አቁመው ይሁን ወይም የዓሊን ንግግር እንደ"ውስጤ" ቆጥረው ባይገባኝም ልባቸውን አቁመው ከዓሊ ጉሮሮ ላይ የድምፅ ሞገድ ማጥመድ ያዙ፡፡

"ጤነኞች ሆይ ወደዬት ናችሁ? ቀን ሲጮህ የዋለው ምላሳችሁ፣ እዚህም እዚያም ሲቃብዙ የዋሉት ዓይኖቻችሁ አሁን ወደዬት ገቡ? እንቅልፍ ወሰዳቸው?" ከት ብሎ ሳቀ፡፡ "የጤነኛ ምልክቱ ደካማ መሆኑን አለማመኑ ነው፡፡ ቀን ሲለፈልፍባት የዋለች ምላሱ ደክማ መለፍለፍ እንደምታቆም አያምንም፡፡ እየለፈለፈች እየደከመች የኖረች ምላሱ እንደምትሞት አንዳች እውቀት የለውም፡፡ መናገሯን እንጂ በተናገረችው ምክንያት ያስከተለችውን አያስብም፡፡ አንዴ ከሞተች በኋላ የተናገረችውን ሰርዛ ደልዛ የምታስተካክልበት ዕድል እንደሌላት አያምንም፡፡ ጤነኞች ሆይ ወደዬት ናችሁ? አይ የናንተ ነገር ዳሽ ሙላ ትወዳላችሁ አሉ፤ ጥቂት እውነት ከያዛችሁ ክፍተቱን ሁሉ በመሰለኝ ትሞሉታላችሁ አሉ፡፡ እንቶኔ እንዲህ የሆነው እንዲህ ሰለሆነ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያደረገው እንዲህ አስቦ ነው፤ እገሌ ይህን የተናገረው ይህን ፈልጎ ነው... እያሉ ይዘላብዱልሃል፡፡ አፍንጫቸውን ይዘህ በምን እንዳወቁ ስትጠይቃቸው የተናገሩትን ዳግም አይውጡት ነገር ዓይናቸውን እያጉረጠረጡ ዝም ይላሉ፡፡ ጤነኞች ሆይ ወደዬት ናችሁ? ሰላማዊ ሰልፍን ለማውገዝ፤ እንዲቀር እንዲጠፋ ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ የወጣችሁ ሆይ ወደዬት ናችሁ? እንቅልፍ ይሉት ጉልበተኛ አሸነፋችሁ? ደግሞ ይህ ሁሉ መከራ የመጣው በኃጢኣቴ ነው ትላላችሁ አሉ፡፡ እይውልህ የከንቱነት ጥግ፤ ልብሱን ያላወለቀ ጤነኛ ይሉሃል ይሄንን ነው፡፡ እሺ ዓለም በኃጢኣታችን ብዛት በስቃይ ታመሰች፤ እስከዛሬ በሰላም የኖርነው፤ አያሌ ጸጋ የተቸረን በጽድቅናችን ሳቢያ ነው? ምድረ ጤነኛ ሁላ!
<ዓለምን በቁጣ መባርቅት አረሷት
ያልጠገበች ሆዷን ቸነፈራት ወጓት
ያላደገች ነፍሷን ወራርሽኝ ነጠቋት
የምትለው አጥታ ብልሃት ቢጠፋት
ኃጢያት ነው አለች...
ጽድቋ ያኖራት መስሏት>"

ምሳ ሰዓት ሆኗል፡፡ አዩብ ሆስፒታል ከገባ ሳምንት ሆኖታል፤ እማ ከሳምንትም በለጣት፡፡ ሁለቱንም ልጠይቃቸው በዚያው የሚበላ ነገር ላደርስላቸው ከቤት ወጣሁ፤ ማሜም ተከትሎኛል፡፡ ባለፈው ሳምንት የሆነውን ከሰማ ጀምሮ ተረብሿል፤ መስጋት ጀምራል፡፡ እነሳንቾ መታሰራቸውን ሰምቶ'ንኳ ስጋቱ አለቀቀውም፡፡ እኔም እንደሰጋሁ ነው፤ የዛሬው ስሜቴ ግን ለየት ይላል፤ በቃ አለ አይደል የሆነ መግለጽ የሚከብድ ስም የሌለው ስሜት.... አዎ እንደሱ ነው የሚሰማኝ፡፡ ከግቢው ራቅ ብሎ ዓሊ እየጮኸ ይሮጣል፡፡ ከቀኝ ወደ ግራ፤ ከግራ ወደ ቀኝ፡፡ ሰዎች "በቃ ተነሳበት" እያሉ ዙሪያውን ከበው ይመለከቱታል፡፡ "ሶጵቺራክ፣ አምቡራክ፣ ናምቤላክ..." ዓሊ ይጮሃል፡፡
"ምን ማለት ነው?" አለው ማሜ፤ ዓሊን ልብ ብሎ ማድመጡ ገረመኝ፡፡
"ልጅ...ት ከልጁ ጋር መጥታለች፡፡ ሶጵቺራክ? ምን ማለት ነበር?" አሰበ፤ "ትርጉም የሌለው ቃል ነዋ! ትርጉሙ ትርጉም አለመኖሩ ነው፡፡ እኛ እብዶች ትርጉም የሌለውን ነገር ትርጉም የለውም እንላለን፤ ጊዜያችንን ትርጉም በመፈለግ አናባክንም፡፡ ተበተን አንተ የለየልህ ጤነኛ ሁላ፤ ሶጵቺራክ የሆነው መሰባሰብህ አንዳች ፋይዳ የለውም፤ ተበተን!"

ታመው ቤታቸው የተኙትን የመስጂዱን ኢማም ጠይቀን ስንወጣ የማሂር አባት መኪናቸው ውስጥ ሆነው ጠሩን፡፡ ወደአዩብ ጋር እየሄድን እንደሆነ ጠይቀውን አነሱም ወደዚያው እንደሆኑ ነግረውን በሩን ከፈቱልን፡፡ ማሂር ጋቢና ተቀምጧል፡፡ እኔና ማሜ ከኋላ ተቀመጥን፡፡ የማሂር አባት፤ ጋሽ ሳላህ ስለአዩብ፣ ስለእነሣንቾ እና ስለእማ እያወሩን ወደሆስፒታል መሄድ ያዝን፤ በመሃል ስለአዩብ አጎት ጠየቁን፡፡

አዩብንና እናቱን እትዬ ዘይነብን አይቷቸው፤ ጠይቋቸው የሚያውቅ አልነበረም፡፡ የዚያን ቀን አዩብ በእነሣንቾ ከመወጋቱ ጥቂት ቀናት በፊት ግን የአዩብ አጎት ነው የተባለ ሰው ይጠይቃቸው ጀመር፡፡ አዩብ አጎቱ መሆኑንን እንደነገረው ማሂር ነግሮናል፡፡ የዚያን ቀን ሆስፒታል ስናስገባው አጎቱ ተከትሎን መጣ፡፡ አዩብን ቀጥታ ወደድንገተኛ ክፍል ነበር ያስገባነው፡፡ ተጨንቀን ስለነበር ካርድ ማውጣቱን ሁሉ ዘንግተን ነበር፤ በኋላ ላይ ግን የአዩብ አጎት የካርዱን እንደከፈለ ነገረን፡፡
"ሆስፒታል ደርሰናል!" ማሜ ከኃሣቤ አባነነኝ፡፡ የቀፈፈኝን አንዳች ስሜት እንደተሸከምኩ ከመኪናው ወረድኩ፡፡ አዩብን ከጠየቅን በኋላ ከማሂርና ጋሽ ሳላህ ጋር እማ ወደተኛችበት ሆስፒታል ለመሄድ አስበናል፡፡ እስካሁን ጽፌ ያላነበብኩላትን ግጥም አነብላታለሁ፡፡ ግን ምን ልላት? ከአምስት ወር በፊት በኋላ አነብልሻለሁ ያልኩሽ ግጥም ነው አይባል ነገር፡፡ አባዬንስ ከአምስት ወር በፊት የአዩብን የቤት ኪራይ ስለከፈልክለት አመሰግናለሁ ይባላል? አምስት ወር ነው'ኮ እንደውም ብዙ ነገሮች የተቀየሩበት፡፡
ማሜ ምግቦቹን አንጠልጥሎ እኔ ባለሁለት ገጹን ግጥም አጣጥፌ በቀኝ እጄ ይዤ አራታችንም ወደሆስፒታሉ ገባን፡፡ አዩብ ከድንገተኛ ክፍል ወጥቷል፤ የተኛበት ክፈል ቁጥር "201" ነው፡፡ ከቁጥር 201
402 views𝓱𝓪𝔂𝓪𝓽𝓲𝓲𝓲, 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ