Get Mystery Box with random crypto!

ለአንዲት ሴት በተለይ “ቆንጆ ሴት” ነን ብለን ለምናስብ ሴቶች ፣ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤ | ISLAMIC SCHOOL

ለአንዲት ሴት በተለይ “ቆንጆ ሴት” ነን ብለን ለምናስብ ሴቶች ፣ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን የራሳችን ቁንጅና ነው፡፡ የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው፡፡
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  ‘ሴትነት እና ቁንጅና’ የሚባል እስር ቤት ፍርግርጋችንን እያስዋብን ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል፡፡ ሁሉም እስር ሰንሰለቱ ፈጦ አይታይም….. እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ለራሱ ጭምር አይታይም፡፡ ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት “የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም፡፡ ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሯዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከሕፃንነቷ  ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል ”
”እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነጽሑፉ፣ በፊለሙ አእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል፡፡ ከመራመዷ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራልች፡፡ ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኙአት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸውን ከለሰለሰ በኃላ፣ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡
እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መሥራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽን እና ዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ ’ዘመናዊ’ ሴቶች፣ እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽ እና እጃቸው እንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡ በልስላሴ ሳይሆን በንጽሕናና ራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?! ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ ሀገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠመ የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀምጡ በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሰሩ….. ማደፋፈር….እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት፡፡
                                                                                                                                                                                            
ከእለታት ግማሽ ቀን; ገጽ 182-183