Get Mystery Box with random crypto!

Page ➌ የሙስሊም ተቋም መጅሊስ ተስተካክሏል ካልን እንደዚህ የኡማዉ አንገብጋቢ ጉዳይ ፈልፍለ | ISLAMIC SCHOOL

Page ➌
የሙስሊም ተቋም መጅሊስ ተስተካክሏል ካልን እንደዚህ የኡማዉ አንገብጋቢ ጉዳይ ፈልፍለዉ አዉጥተዉ የተቀናጀ ስራ ቢሰሩ ለዚህ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ይችሉ ነበር...መጅሊሱ ከበፊቱ የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ይሄንን ብታሳዉቋቸዉ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ



☞ አንዲት ደሴ የማቃት Hiv ያለባት የተሰቃየችዉን ስቃይ ሙሉ በሙሉ አቃለሁ በአካል ትነግረኝ ነበር ግን አልሀምዱሊላህ አዲስ አበባ እንደሷ ኬዝ ያለባት አግብታ የሶስት ልጅ እናት ሁናለች
አሁን ዘመኑ ተሻሽሏል የሚወለዱት ልጆች Hiv አይኖርባቸዉም በሀኪም ክትትል ስለሚወልዱ ..የእሷን ታሪክ ፅፎ ማቅረብ ይቻል ነበር ግን ጊዜ የለም ፅፎ ማዘጋጃ...,በጣም አሳዛኝ አስተማሪ ነዉ እኔን ትነግረኝ ነበር የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ ነበረች አብረን ስለአደግን የሚገጥማትን ትነግረኝ ነበር የአሁን ወንዶች መቼም ግማሹ ለትዳር ግማሹ ለስሜት ስጠይቃት የምታሳልፍበት ጥበብ የተለየ ነበር ግን በጣም ተሰቃይታ ነበር ግን ጀሊሉ ጋር የነበራት ቁርኝት የተለየ ነበርና አዲስ አበባ አግብታ ጥሩ ኑሮ እየኖረች ነዉ አልሀምዱላላህ እሷን ያገናኛት አዲስ አበባ የሚኖር ይሄን ኬዝ የሚያቅ አጎቷ ነዉ

Please የትችት ብቻ ሳይሆን የመፍትሄም ሀሳብ አፍላቂ እንሁን ..በፊት ፁሁፍ በማዘጋጅበት ጊዜ ከአቅም በላይ የሆነ  በጣጣጣም ትችት አስተናግድ ነበር ሰዉ የሚሰራን አያስተናግድም
የአሁን ዘመን ትዉልድ የኢንሻ አላህና የአላሁ አክበር ትዉልድ ነዉ....ለዲነል ኢስላም በቻልከዉ ስራ ሲሉት ኢንሻ አላህ ..ከዛ በጀመአ ወይ በመስጊድ ተሰብስቦ የሆነ ነገር ተሰራ ሲባል ተክብር አሏሁ አክበር ብሎ የሚሄድ እንጂ የሚሰራ 0.001% ነዉ ...የሚሰራን የሚተች ደግሞ 99.9% ነዉ፡፡
በፊት አስታዉሳለሁ ታሪክ ሳዘጋጅ ብዙ ቁርአን ሀፊዞች የአንተን ታሪክ ስናነብ ቁርአኑ እየጠፋን ነዉ እያሉኝ በጣም ግራ ገብቶኝ ነበር  እንዴት ቁርአኑ እስከምጥፋት ደረሱ?? ብየ..የአሁን ዘመን ሰዉ ሽንፈቱን የበታችነቱን የኔ
ጥፋት ነዉ ብሎ አያስብም በሰዉ ላይ መለጠፍ ይወዳል እናም የመፍትሄ ሀሳብ እንጂ ሽንፈትን ወደ ሰዉ በማላበክ ጥገኛ ባንሆን መልካም ነዉ...

አሁንም መፍትሄ አመንጭ እንሁን  ይሄ የHiv ኬዝ ከባድ ኬዝ ነዉ በኢንሻ አላህ የሚታለፍ አይደለም ብዙዎች ሀይማኖታቸዉን እየቀሩ ነዉ.. እንቅፋት ሳንሆን በዚህኳ የመፍትሄ ሀሳብ እናመንጭ

እናንተ Hiv ቢኖርባችሁ ትዳር ብትፈልጉ ምን ታደርጋላችሁ?? አስተያየታችሁን በዚህ bot ጀባ በሉን
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

አስተያየት ስትሰጡ ለምን ፁሁፍ አታዘጋጅም --ጠፍተሀል -- ቻናሉ ሰዉ እየቀነሰ ነዉ --ወደ ሚዲያ መቼ ነዉ የምትመለሰዉ ምናምን እንቶ ፈንቶ የሆነ አስተያየት አትፃፉ አልቀበለም..ተወስኗል ወደ ሚዲያም አልመለስም ታሪክም 100% ሁኜ ልንገራችሁ አላዘጋጅም የራሴ የሆነ እኔዉ ብቻ የማቀዉ አሳማኝ ምክንያት አለኝ ...አስተያየት የምትፅፉት ዛሬ ላይ በአነሳሁት ስለ Hiv ኬዝ ላይ ብቻና ብቻ ነዉ፡፡

ስሙኝ ወገን እኛም ቢሆን ተመርምረን እራሳችንን ተመርምረን ብናቅ ጥሩ ነዉ..ቆየትም ቢል ተመርምረን የምናቅ ይኖራል ያልተመረመርንም ይኖራል
አይታወቅም የአላህ ነገር በአመት በሁለት አመት ልዩነት ምን እንደሚፈጠር አናቅም ...ይሄኔ ራስን አዉቆ የህይወት ግብ መቅረፅ ያስፈልጋል በተለይ በትዳር ዙሪያ ላይ

   አሁን አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞናል ስለዚህ Hiv ኬዝ ብቻ እናዉራ ሀሳብ አስተያየታችሁን በዚህ bot ይላኩልኝ ቀጥታ ለኔ ይደርሰኛል
እኔም ይሄን ሀሳብ ላመጣዉ ልጅ እና በሀሳብ እኔን ከሚጋሩ ቤተሰቦች የላካችሁትን አስተያየት እልከዉና ተወያይተን ሀሳብ ላይ  እንደርሳለን

በፊት ትዳር አገናኝም የምትሉም ነበራችሁ አደራ እኔ ማንንም አሁን አምኜ አግባዉ አግቢ ብየ ሀላፊነት አልወስም...እኔ  የምላችሁ ሰዉ የሚወዱትን የሚያፈቅሩትን አያገባም አርባ አራት ነጥብ ለምን አላህ ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም አላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ብሎ ነግሮን ከዱንያ ደስታን አጋኛለሁ ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ የሚወዳዱ የሚፋቀሩ  አይጋቡም ፡፡አፍቃሪ ማለት ከመጥፎ እድሉ ዉስጥ ደስታን የሚፈልግ ሰዉ ነዉ፡፡....ማፍቀር አንዱን ትዳርን ከሚከለክሉ ነገሮች ናቸዉ ..አጭተህ የሌላ ሁነህ እንኳ ፍቅሩን ልረሳዉ አችልም ልብህ ሌላ ቦታ ስሜትህ አገባሀት ጋር ሁኖ ልትቸገር ትችላለህ፡፡ አንዳንዴ ልቤን ከአሁን ቡሀላ አልሰጥም የሚሉ አሉ ልብ አንዴ በፍቅር ከተለያየዘ ያ ልብ እንዴት ተብሎ ነዉ ጡሀራ ሁኖ ለሌላ የሚሰጠዉ???
እናም አሁን የፍቅር ዝባዝንኬ አቁሞ ቀጥታ ማግባት ፍቅሩ ከዛ ቡሀላ ይመጣል ፡፡ በፍቅር ተይዘህ ተይዘሽ ያ ንፁህ ልብ ትዳርን ሊፈራ ይችላል የሚሻለዉ አግብቶ አብሮ ሁኖ የትዳር አጋርን መድሀኒት የሚወለዱ ልጆችን ያ የተጎዳን ልብ በልጆች በትዳር አጋር ፍቅር ማከም ብቻ ነዉ፡፡ ማወቅ ያለባችሁ አሁን ትዳር ሲያዝ ሴቶም ወንዱም ያሳለፈዉ ያልተሳካ የፍቅር ጉዞ ይኖረዋል ...ያለፈዉን ለወደፊቱ ችግር እንዳያመጣ አርጎ ዘግቶ
ትዳርን እርስ በርስ በመቀናጀት ህክምና ማድረግ ነዉ፡፡ ዘመኑ ገና 4 -8 ክፍል ያሉ ሴት ተማሪዎች ስለፍቅር በሚያወሩበት ዘመን ወደ ትዳር ወሬ ስጀምር ከአሁን በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ ወይ እያልክ አጠይቅ፡፡ የሚሻለዉ ያለፈዉ አልፏል ስለወደፊቱ እናዉራ ብለህ አሁን ላይ የጠፋዉ እንደ ወንድ የሆነ ወንድ እንጂ ተራ ወንድ ነፍ አለ ሀቢቢ ስለሆነም ትዳር አገናኘኝ በፊት ጀምሩ የምትሉ ይሄ ጉዳይ እንዳይነሳ

   ወደ ላይ የተወረወረ ሁሉ ተመልሶ መምጣቱ እንደማይቀር ሁሉ በሰዉ ልጅ የህይወት ሂደትም ዉስጥ መሄድና መመለስ ያለ ነገር ነዉ..ወደ ሰማይ የወረወርከዉ ዲንጋይ ተመልሶ መጥቶ ከምድር ላይ በማረፉ መጨረሻዉ ነዉ ብለህ አትሰብ ብትፈልግ ዳግም አንስተህ ልትወረዉረዉ የምትችለዉ ነገር ነዉና ወደ ላይ መዉጫዉ ሆነ ወደ ታች መዉረጃዉ መንገድ አንድ ነዉ
እናም ህይወት ቋሚ አይደለችም ፍቅር ቋሚ አይደለም ሄድ መለስ ነዉ የሚለዉ እናም ህይወትህን ትዳርህን ማስተካክል የምችለዉ አንተ በእጂህ እንጂ በእድል በቁዘማና በማይለቅ ትዝታ አይደለም፡፡የሞተን ፍቅር ማቀፍ የዛሬን የነገን ህይወት ማበላሸት ነዉ
እናም ትዳር የአንቺ ወይ የእሱ ከዛ አንድ ላይ ስትሆኑ የእናንተ የእጅ ስራ ዉጤት እንጂ አንዴ ሳይሳካ ሲቀር የመጨረሻ ነዉ ብለን አንሰብ ፈጣሪ የተሻለ አለዉና

>>>>ግን Hiv ያለባችሁ የእናንተን ኬዝ ስራየ ብየ እስከመጨረሻዉ ድረስ በስልክ በtg የአቅሜን ከአቅሜም ለመስራት ወስኛለሁ ሌሎችም Hiv ያለባቸዉ ታማኝ  group ያላቸዉ ዲነኞች አንድ ወንድሜ እና እህቴ ጋር ለመስራት ስለወሰንኩ በአላህ ፍቃድ በቻልነዉ አቅም እንሰራለን
አደራ በአላህ ስም ይዣችሆለሁ አንብባችሁ እንዳታልፉ አስተያየት ስጡ አደራ ይሄ ሀሳብ ልፓስተዉ ስል በአገራችን ጉዳይ Data ሲቋረጥ ተዉኩት ሙሉ በሙሉ ሰዉም ባይገባ በSafaricom እና በpispon
እየተጠቀመ ስለሆነ ነዉ የፓሰትኩት

እናም አስተያየት ለመስጠት
አስተያየት ለመስጠት
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot