Get Mystery Box with random crypto!

በፊት ሴት ልጅ ሰነፍ ከሆነች አትማር ማንበብ መፃፍ ካወቀች ይበቃል እስከ 8 ከተማሩ በቂ ነዉ የት | ISLAMIC SCHOOL


በፊት ሴት ልጅ ሰነፍ ከሆነች አትማር ማንበብ መፃፍ ካወቀች ይበቃል እስከ 8 ከተማሩ በቂ ነዉ የትምህርት ቤት እና የቤት ዉስጥ ባህሪያቸዉ የተለያየ ነዉ ...ሰነፍ ከሆነች አትማር መማሯ ጉዳት ያመጣል በዲን አሳድጎ በልጅነቷ መዳር ይሻላል....
ወንድም ያዉ ነዉ ግን ጉዳቱ ለሴት በጣም ያመዝናል ስል..... በተደጋጋሚ አንተ የድሮ ሰዉ ነህ ለሴት መጥፎ የተጣመመ አመለካከት አለህ ተብየ ነበር

እድሜ ለትምህርት ሚኒስራችን ለዶክተር ብርሀኑ ነጋ እንኳን ሰነፍ ሴት ተማሪ ወንድም ቢሆን ሰነፍ ከሆነ መማር እንደሌለበት ትክክል መሆኑን ዘንድሮ በ12 ክፍል ፈተና ዉጤት አሳይቶናል

በጣምም ብዙ ትምህርት ቤቶች አንድ እንኳ ተማሪ ያላሳለፉ እንዳሉ መቼም ሰሞታችሆል...ለወደፊት የትምህርት ጥራትን በአሁኑ አጀማመሩ ጥርት ያለ ትዉልድ እንደሚፈጥር ባለሙሉ ተስፋ ነኝ...

መቼም መምህሮቹ ማሰቢያቸዉ ከሰራ  ከአሁን ቡሀላ ትምህርት ቤቶች እንዳይወቀሱ እንዳይተቹ እየጓፈፉ የሚያሳልፉ አይመስለኝም ለምን በአሁኑ የትምህርት ሚኒስተር አያያዝ ስወድቁ ትምህርትቤቱን እንደሚገመግም ባለሙሉ ተስፋ ነኝ...
ለማንኛዉም በተለይ ለሴቶች ሰነፍ ተማሪ ከሆነ ይሄኔ በሀላሉ ጥግ ቢይዙ ኸይር ነዉ ባይ ነኝ

ለወደቃችሁ ተማሪዎች የስራ ዉጤት ነዉ ምንም ማለት አይቻልም ያለፋችሁ ግን ከእናንተ ጀምሮ ያለዉ ተማሪ ምርጥ ትዉልድ እንደሆነ አርጋችሁ አስባችሁ ጥሩ ደረጃ እንየምደርሱ ባለሙሉተስፋ ነኝ ለምን ዝምብሎ ግቢ ገብቶ ላይፍ እንቅጭ;boy frind ..girl frind እያለ ከሚያለቃቅስ ስራፈት እና
በዘር በፓለቲካ ዝባዝንኬ እያነሳ የሚበጠብጠዉን ቦዘኔ የማይጠቅም የማይጎዳን የአፈር ገንፎን ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ደህና አድርጎ አበጥሮታልና አሁን ዩኒቨርስቲ የሙህራን ህልም ያለዉ ለሀገር ለወገን የሚበቁ ትዉልዶች ማፍሪያ ይሆናል፡፡



ደግሞ በፊት ያልኳቸዉ ሙነሾዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ ተጠንቀቁ ስል ነበር...የዛን ጊዜም እተች ነበር ግን ይሄዉ ሁሉም ነገር ይፋ እየወጣ ነዉ

የእነሱም ጉድ ሚዲያ ላይ እያያችሁ ነዉ ሲያገቡም ሲፈቱም በአዳራሽ  ሰብስበዉ ሲጨፍሩ ሲያስጨፍሩ....
እኔ የምመኘዉ ቦዘኔ ተማሪን ዶክተር ብርሀኑ ነጋ አደብ እንዳሲያዘልን ..በዲን የሚያላግጡ ሙነሺዶችን ቁርአን መቅራት ሀዲስ ማዳመጥ ትተዉ አብረዉ እያንጎራገሩ የሚዉሉ የሙነሺድ ተከታይ አድናቂዎች 80% በላይ የሚሆን ሴቱን ከነሺዳ አዉጥቶ በቁርአን በተዉሂድ የሚያረጥብ አንድ ጀግና እንደሚፈጠር ኢንሻ አላህ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ጀሊሉ ሆይ ለሰነፍ ለቦዘኔ ተማሪ ዶክተር ብርሀኑ ነጋን እንደላክልን በዲን ለሚቀልዱና እነሱን ለሚከተሉ ሁሉ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራን የማንም ፊርቃ አባል ያልሆነ ከዚህ ትዉልድ አዉጣልን ያረብ

ለማንኛዉም ለዶክተር ብርሀኑ ነጋ ትልቅ ክብር አለን
ይህን ፁሁፍ ለመፃፍ የዘገየሁት ያዉ ከሚዲያ ራሴን ሳላገለልኩ ነዉ ያለፋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ

የወደፊት የሚፈጠረዉን ደግሞ አብረን እናያለን
መልካም ጥሩ የህይወት ዘመን ተመኘሁ



اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته
Amir  seid dena neh?
Abshr hulum neger yalfal bcha ante tegstegna hun ALLAH kante ga new,ALLAH SUBHANEHU WETEALA ytebkh,enam bekrbu wede telegram alem endemtmeles  tesfa aregalehugn
ALLAH Imanh ychemrlh ...

ye mekelle lij negn

Channelhn befit awkow neber  abzagnawochu  tarikoch anbibyachaw nebere enam bzu tmrt kante Channel aggnichalow جزاك الله خيرا but 2 amet yakl  internet alneberem....
Be gugt yante channel etebk neber
Alhamdulilah ahun tekefto egna sngeba ante tefahbn ALLAH be kheyr ymelsh...

Yetefahbet mknyat balekewm انشاء الله tmelesaleh biye tesfa argalehugn...
Ende mitaweqew egnam betam bekebad chgr lay new yenebernew bihunm hulum neger alfo  negerochn be ALLAH fkad eyetestekakelu ygegnalu...
Slehonem yedunya musibawoch ena fetenawoch ayalkum ena hulum neger lekheyr new bleh dua arg انشاء الله
ALLAH SUBHANEHU WETEALA kalehbet chgrh yawtah...جزاك الله خيرا

ትግራይ ክልል ያሉ በፊት የኔን ቻናል ሲከታተሉ የነበሩ ብዙዎች በአስተያየት ከመቀሌ ከአድዋ ወዘተ እየላኩልኝ ነዉ ይሄ የአንዱ ቤተሰብ አስተያየት ነዉ፡፡ አልሀምዱሊላህ ያ ቀን አልፎ ለመገናኘት በቃን አልሀምዱሊላህ
ከትግራይ ክልል ኢንተርኔት እንደተከፈተ የኔ ደህንነት አስስቧችሁ ለጠየቃችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ


አሚር ሰይድ