Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ ሀያ ሁለት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ



------መፍቱሀም አይኔን ገለጠችኝ .....ያየሁትን ማመን አቃተኝ እንደዚህ አይነት ሰርፕራይዝ በፊልም ለራሱ አይቼዉ አላቅም እንኳን በኔ ሒወት ከፊልም በላይ ነዉ የሆነብኝ

ቤቱ በዲምላይት እና በዲኩሬሽን አሸብርቋል በየመሀሉም ILOVE YOU NEWAL የሚል ወረቀቶች ተለጥፈዋል፡፡ ኬኩ ላይ ለራሱ ነዋል ሁሌም እወድሻለሁ ልታገቢኝ ፍቃደኛ ነሽ ወይ?? የሚል አፅፎበታል...ቸኮሌቱ ፍራፍሬዉ ተሰናድቷል ...በየቦታዉ ሻማ ተደርጓል  ከምነግራችሁ በላይ ቤቱ አሸብርቋል

ቤቱ ዉስጥ ከገባሁ ቡሀላ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ቁሜ ቤቱ ማሸብረቁ ድባቡ ለአይኔ አዲስ ሁኖበት ገርሞኝ እንደቆምኩኝ አየዉ ይዣለሁ ...ወላሂ ህልም ህልም ነዉ የመሰለኝ አይኔን ብገልጠዉ ብጨፍነዉ ነገሮች ሊቀየሩ አልቻሉም እዉነት ነዉ ብየ ከመቀበል ዉጭ.... ይሄ ሁሉ ለኔ ዝግጅት በጭራሽ ሊዋጥልኝ አልቻለም በጣም አጀበኝ እንዴት ቤቱ አምሯል በአላህ .....

ቁሜ እየተገረምኩኝ እየተአጀብኩኝ ካሊድ መጥቶ በጉልበቱ ተንበርክኮ
.....ነዋል የኔ ፍቅር በጣም እወድሻለሁ ግዙፍ  ሶስት አመት ያህል ታግሼ ጠብቄሻለሁ ...ወላሂ ብየ ነዉ የምነግርሽ ሶስት አመት ያህል ለሊት እየተሳሁ እየሰገድኩ ነዋልን ለኔ አድርጋት እያልኩ አልቅሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አመታትን እንኳ ይቅር አንድ ሳምንት አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም  .....ልታገቢኝ ፍቃደኛ ነሽ ወይ ???? አለኝ

......ካሊድ ተንበርክኮ እንደዚህ ሲለኝ ማመን አቃተኝ ተገረምኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ተንበርክኮ አግቢኝ ሲለኝ ____አረ ሌሎችም ወንዶች ብዙ የትዳር ጥያቄ ሲመጣ ማንም ተንበርክኮ ጠይቆኝም አያቅም የካሊድ ግን ገረመኝ

እኔ በጣም ደስ አለኝ እንደዚህ ያለ ፍቅር ወላሂ ምኞቴ ነዉ ግን በማንነቴ እፈራለሁ.....ምን እኔ ብቻ ብዙ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምኞታቸዉ ነዉ ይሄን በህልማቸዉ የሚያዩትን የፍቅር ምኞታቸዉን ለማሳካት በሀራም መንገድ በር ሲከፍቱ ይስተዋላላሉ ....ካሊድ ተንበርክኮ ሲጠይቀኝ እምባየ ቀደመኝ

እምባየ በቆምኩበት ጭንቅ ጥብብ እያለኝ እየተወዛገብኩ በጉንጮቼ በሁለት ረድፍ ኮለል እያሉ እየወረዱ ነዉ ጭንቀቴም እኔን እስከማንነቴ ይቀበለኛል ወይ ??? ይሄን ሁሉ ሰርፕራይዝ ይሄ ሁሉ ፍቅር ለኔ እየገለፀልኝ እኔም እሺ ብል ቡሀላ ስነግረዉ ካሊድ ከነማንነቴ ባይቀበለኝስ ?? ግራ ተጋባሁ ...አሁን ዉሳኔዉ ለዛሬዉ ደስታ ሳይሆን የወደፊት ደስታየን አያደፈርስም ወይ ??ነዉ......
ማንነቴን ይቀበለኛል ወይስ አይቀበለኝም ??"

በሀሳብ ዉስጥ ሁኜ ለካሊድ ...እንዲህ አልኩት...

#ግን_እኔን_ከልብህ_ትወደኛለህ ??? አልኩት
.......ካሊድም:- ነዋል ወላሂ ከልቤ እወድሻለሁ በፊት እንደዛ ፊት ስትነሽኝ ስታስቀይሚኝ ለራሱ አልጠላሁሽም ..እንኳን ልጠላሽ ፍቅርሽ ጨመረብኝ እንኳን ዛሬ ከፊለፊቴ ሁነሽ አለኝ...

እኔም የምመልሰዉ የማወራዉ ግራ ገባኝ ከዝምታ ዉጭ መልስ አጣሁ
....ካሊድም ዝም ብለሽ ቆየሽ እኮ ዉሳኔዉን ንገሪኝ??? እምቢ ልትይ ነዉ እንዴ??? አረ ተንፍሺ በሀሳብ ጨረሽኝ እያለ ሲያወራ እምባ ተናንቆታል፡፡

.......እኔም እሺ ፍቃደኛ ነኝ እንጋባለን አልኩት፡፡
ካሊድ በጣም ደስ አለዉ እህቶቹም እልልታዉን አቀለጡት ፡፡ ቀለበት ገዝቶ ይዞታል ...አንድ ቀን እንኳ ከካሊድ ጋር እጅ ለእጅ ተነካክተን አናቅም  ..ካሊድ ጋር ቀጥ ብሎ አይን ለአይን ተያየን ፡፡ ለመፍቱሀ እንኪ ቀለበቱን አድርጊላት ብሎ ሰጣት....መፍቱሀም ቀለበቱን አደረገችልኝ እህቶቹ በእልልታ ቤቱን አደመቁት

ከዛም ካሊድ ቆይ መቼ ጨረስን ...ነዋል ለኔ ቀለበት አታረግልኝም እንዴ ??? አለ
......እኔም ደንግጬ ካሊድ እኔ እኮ ምንም አልገዛሁም እዚህ ስመጣ ይሄ ይሆናል ብየ አልገመትኩም አልኩት
.....ካሊድም እየሳቀ ችግር የለዉም እኔ ገዝቻለሁ ብሎ ሰጠኝ....ከዛም ቀለበቱን እጁ ላይ ሳንነካካ አስቀመኩለት እሱም ጣቱ ላይ አደረገ

እኔ እና ካሊድ አንድ አይነት ቀለበት አደረግን፡፡ እህቶቹ በየተራ እየመጡ በደስታ ተጠመጠሙብን እንደ ህፃን ልጅ ሳሙን፡፡ ምሳ ዝግጅት በየአይነት ምግብ ተዘጋጅቶ ነበር እህቶቹ እያጎረሱኝ እየተሳሳቅን እየተጨዋወትን ምሳ በላን

ከዛም ኬኩን እኔዉ ቆርሼ በላን.... ከጁምአ ሶላት ቡሀላ የጀመርን እስከ መቅሪብ ሊደርስ አካባቢ ድረስ እህቶቹ ጋር ሁላችንም ሰንጨዋወት ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን፡፡


ከካሊድ ቤት ወደ መኖሪያ ቤቴ ተመለስኩኝ.... እቤት ስመለስ ይሄዉ በሽታየ ጀመረኝ ብቻየን መጨናነቅ ለካሊድ እንዴት ነዉ በልጅነት መደፈሬን የምነግረዉ ??? እያልኩ ብቻየን ሳስብ ሳስብ የማልገፋዉን የተራራ ቁልል ሀሳብ ብቻየን በአእምሮየ ሳመላልሰዉ አደርኩ

ጭንቀት ሳበዛ ጨጓራየን ያመኛል ምግብም አልወስድም ሲያስታዉከኝ አደረ.....

የሚገርማችሁ ነገር እኔ ካሊድን እወደዋለሁ ግን ልቤ ሰፍ አይልለትም....በጣም እንደሚወደኝ እንደሚያፈቅረኝ አዉቃለሁ .....እኔ ደግሞ ይናፍቀኛል እወደዋለሁ ከእሱ የሆነ ነገር እጠብቃለሁ ግን አላፈቅረዉም ፡፡ እንዴት እንደምገልፀዉ ግራ ይገባኛል አንዳንድ ሴቶች ይሄን ልጅ ሳየዉ ልቤ ሰፍ ይላል ልቤ ይርገበገባል ይላሉ ..እኔ ደግሞ ለካሊድ እንደዚሁ ነኝ ሁሌም እወደዋለሁ ግን ለእሱ  ልቤ ሰፍ አይልም፡፡ እኔ ይሄን ፍቅር ስተረጉመዉ ካሊድን የወደድኩት በአእምሮየ ነዉ እንጂ በልቤ አይደለም ይመስለኛል፡፡እናንተ እንደዚሀ አይነት ፍቅር ገጥሟችሁ ያቃል ??? የገጠመዉ የሚያቀዉ ሊረዳኝ ይችላል

  ሁሌ ጁምአ ከአሱር ቡሀላ እዛ እገጠሩ ቦታ ሰዉ የሌለበት እየሄድን እናወራለን ይሄ ፕሮግራማችን ሆነ  ፡፡ እንደ ዘንድሮ ፍቅር ጎን ለጎን ሁኖ እወድሻለሁ አበድኩልሽ..ልሳምሽ ልንካሽ በጭራሽ የለም፡፡
 ቁም ነገር ነዉ የምናወራዉ ካሊድ ደስታዉ እኔን ማየቱ ብቻ ነዉ

    ቀለበት ካረገልኝ ቡሀላ ካሊድ ፍቅሩ ከበፊቱ ባሰበት፡፡ ጠዋት ማታ መደወል ስለትዳር ማዉራት ሁኗል ወሬዉ እስከምንገባ በጣም ቸኮለ
..እኔ ደግሞ ማንነቴ አስጨነቀኝ በጣም በስቃይ በለቅሶ በዱአ ላይ ነኝ ...ካሊድ ሲደዉል እስቃለሁ ደህና ነኝ እላለሁ ..ግን ስልኩን ሲዘጋዉ የማይጠፋ እሳት ሆዴ ዉሴጥ ተለኩሶ በእንባየ የሚጠፋ ይመስል አለቅስ ይዣለሁ፡፡ ደግሞ ትምህርት ቤት እና በየመንገዱ ደስተኛ ነኝ ፊቴ ዘና ብሎ ጥርሴ መሳቅ አመሉ ነዉ....አይ ጥርሴ የልቤን ብታየዉ እንኳን መሳቅ ከነጭነት ወደ ጥቁርነት በተቀየርኩ ባልከኝ እንኳን እኔን ከፍቶኝ አይኔ ሲያለቅስ ጥርሴ ግን በልቤና በእምባየ እየቀለደ ይመስል ፈገግ ይለዋል፡፡

  ወላሂ ብየ ነዉ የምነግራችሁ ሰዉ ሁላ ዘመድ ጎረቤት ጓደኞቼ ቀለበቴን ሲያዩት በደስታ ፣ መቼ ነዉ ሰርግሽ ??? የማይለኝ የለም ፡፡ ታዋቂ መሆን አንዳንዴም አስቸጋሪ ነዉ....በየመንገዱ ያገኘኝ ሁሉ መቼ ነዉ ንገሪኝ የማይለኝ የለም....

የለበስኩትን ቀለበት ብቻ አይተዉ ነዋል ልታገባ ነዉ የሚል ወሬ በእኛ ሰፈርና በኮሌጅ ሳይቀር በአንዴ ተናፈሰ...


#ክፍል
ይ..........ቀ...............,
.......ጥ.........ላ..............ል


     Join     `·. t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
•════••• •••════•